ያልተጠበቀው የተመድ ባለሥልጣን የሰሜን ኮሪያ ጉብኝት

Image copyright AFP/Getty Images

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ ጄፍሪ ፌልትማን ያልተጠቀ ጉብኝት በፒዮንግያንግ ማድረግ ጀመሩ።

ጉብኝታቸው ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ በከፍተኛ የተመድ ባለስልጣን የተደረገ የመጀመሪያ ጉበኝት ነው።

ሰሜን ኮሪያ "ለፖሊሲ ውይይት" በሚል ለተመድ የጉብኝት ግብዣ መስከረም ላይ አቅርባ ነበር።

ይህ ጉብኝት ግን ሰሜን ኮሪያ አሜሪካን መምታት ይችል ነበር ያለችውና ባለፈው ሳምንት ያደረገችውን "በጣም ኃይለኛ" አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳኤል መወንጨፍን ተከትሎ የተደረገ ነው።

የአሜሪካው የቀድሞ ዲፕሎማትና በተመድ ከፍተኛ አሜሪካዊ ባለስልጣን የሆኑት የፌልተማን የፒዯንግያንግ ጉበኝት ከማከሰኞ እስከ አርብ የሚቆይ ነው።

ጉብኝቱ ሁለቱ አገራት ከመቼውም በበለጠ የአየር ላይ ጥቃት የመፈፀም አቅማቸውን መፈታተሻቸውን ተከትሎ የተደረገም ነው።

የተመድ ቃል አቀባይ ለጋዜጠኞች እንደገለፁት ፌልትማን የአገሪቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪ ዮንግ ሆን ጨምሮ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተገናኘተው በፖሊሲና የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ።

ነገር ግን የሰሜን ኮሪያውን መሪ ኪም ጆንግ ኡንን የማግኘት ፕሮግራም አልተያዘም።

መስከረም ላይ የተላከው የጉብኝት ግብዣ አዎንታዊ ምላሽ ያገኘው ህዳር ወር ላይ ሰሜን ኮሪያ ሚሳይል ባስወነጨፈች ማግስት ነው።

ፌልትማን ወደ ሰሜን ኮሪያ ከማቅናታቸው በፊት የፒዮንግያንግ ዋንኛ የኢኮኖሚና የዲፕሎማሲ አጋር ወደሆነችወ ቻይና ተጉዘው ነበር። ባለፈው ወር ቻይናም ለውይይት ከፍተኛ ባለስልጣናቷን ልካ ነበር።

የቢቢሲው ፖል አዳምስ ምንም አይነት ትርጉም የሚሰጥ የዲፕሎማሲ መስመር በሌለበት ሁኔታ የተገኘውን ማንኛውንም የውይይ እድል መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ ይናገራል።

ተመድ እንዳስታወቀው ከዚህ ቀደም በሰሜን ኮሪያ ቀውስ የማደራደር ፍላጎት ያሳዩት የተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ግን በአሁኑ ወቀት ፒዮንግያንግን የመጎብኘት እቅድ የላቸውም።

ከዚህ ቀደም የተደረገው የመጨረሻው የተመድ ከፍተኛ ባለስልጣን ጉብኝት ጥቅምት 2011 በቀድሞው የተመድ ሃላፊ ቫለሪ ባለሥልጣን ነበር።

የፌልትማን ቀዳሚ ሊን ፓስኮይም ሰሜን ኮሪያን 2010 ላይ ጎብኝተው ነበር።

የፌልትማን ጉብኝት ግን የሰሜን ኮሪያ ሚሳይል ማስወንጨፍን ተከትሎ ውጥረት በነገሰበት አለም አቀፍ ሁኔታ የተደረገ ነው።

በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር ኒኪ ሃሊ ባለፈው ሳምንት ጦርነት ተቀስቅሶ ቢሆን ኖሮ የሰሜን ኮሪያ መንግሥት ድራሹ ጠፍቶ አንደነበር ተናግረዋል።

ሰኞ ዕለት ደቡብ ኮሪያና አሜሪካ የአምስት ቀን የአየር ላይ ውጊያ ልምምድ የጀመሩ ሲሆን ይህ ከ200 በላይ አውሮፕላኖች እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች የተሳተፉበት ልምምድ እስከዛሬ ከታየው ትልቁ እንደሆነ ተነግሮለታል።

የዚህ ዓይነቱን ልምምድ የምትኮንነው ሰሜን ኮሪያ የአሜሪካን እርምጃ "ትንኮሳ" ብላዋለች።.