ያለዕድሜ ራሰ በራ የሆኑ ሰዎች ለልብ በሽታ ተጋላጭ ናቸው ተባለ

A bald man Image copyright Getty Images

ያለ ዕድሜያቸው ራሰ በራ የሚሆኑ እና ሽበት የሚያበቅሉ ከአርባ ዓመት በታች የሆናቸው ወንዶች ከመጠን ያለፈ ውፍረት ከሚያስከትለው በላይ ለልብ በሽታ ተጋላጭ ናቸው ሲል አዲስ ምርምር ይፋ አደረገ።

በህንድ በሚገኙ 200 ወጣት ወንዶች ላይ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳው ልብ በሽታ ያለባቸው ወጣቶች ከሌሎቹ በበለጠ ያለዕድሜያቸው ራሰ በራ የሆኑ ወይም ሽበት ያበቀሉ ናቸው ተብሏል።

የአውሮፓ ካርዲዮሎጂ ማህበር ጥናት ህንድ ባዘጋጀችው ዓመታዊ የካርዲዮሎጂ ማህበር ኮንፈረንስ ላይ ይቀርባል ተብሏል።

እንግሊዝ የልብ ፋውንዴሽን ግን ሌሎች ምክንያቶች የበለጠ አጋላጭ ናቸው ብሏል።

የቢ ኤች ኤፍ ሜዲካል ዳይሬክተር ሆኑት ዶ/ር ማይክ ክናፕተን "ጥናቱ ያለዕድሜያቸው ራሰ በራ የሆኑ ወይም ሽበት ያበቀሉ ወንዶችን መለየት ለልብ በሽታ ከፍ ያላ ተጋላጭነት ያላቸውን ለመሌት ያስችላል" ብለዋል።

"ይህ ግን ሰዎች ሊቀይሩት የማይችሉት ነገር ቢሆንም የአኗኗር ዘይቤን መቀየር እና እንደ ከፍተኛ ኮሌስትሮል እና ደም ግፊት የዓሉትን መንስኤዎች ማስቀረት ይቻላል" ሲሉ ይገልጻሉ።

ያለዕድሜ መሸበት

በ69ኛው የኮልኮታ ኮንፈረንስ ላይ የሚቀርበው ጥናት ከአርባ ዓመት በታች የሆናቸው እና የልብ ችግር ያለባቸው 790 ወንዶችን 1270 ከሆኑ እና በተመሳሳይ የዕድሜ ክልል ካሉ ጤነኛ ወንዶች ጋር አነጻጽሯል።

የሁሉም የጥናቱ አካላት የጤና ታሪክ ተጠንቷል። በዚህም ያላቸውን የራሰ በራነት እና የጸጉር ሽበት ሂደት እንዲያሰፍሩ ተደርጓል።

ተማራማሪዎቹ የጥናቱን ውጤት ከልብ በሽታው ከባድነትደረጃ ጋር አያይዘውታል።

የልብ በሽታ ችግር ያለባቸው ወንዶች ያለዕድሜያቸው ሽበት የማብቀላቸው መጠን 50 በመቶ ሲሆን ጤነኛ የሆኑት ደግሞ 30 በመቶ ብቻ ያለዕድሜያቸው ሽበት አብቅለዋል። እነዚህ ወጣቶች በልብ በሽታ የመያዝ ዕድላቸው በአምስት እጥፍ ከፍ ያለ ሆኖ ተገኝቷል።

በተመሳሳይ ልብ ችግር ያለባቸው ወንዶች ያለዕድሜያቸው ራሰ በራ የመሆናቸው ዕድል 49 በመቶ ሲሆን ጤነኞቹ ግን 27 በመቶ ብቻ ነው ተብሏል። እነዚህ ወጣቶች በልብ በሽታ የመያዝ ዕድላቸው ከአምስት ነጥብ ስድት እጥፍ በላይ ከፍ ያለ ነው።

ከመተን ያለፈ ውፍረት ግን ለልብ ችግር የማጋለጥ ዕድሉ በአራት ዕጥፍ ከፍ ያለ ነው።

የጥናቱ መሪ ዶ/ር ካማል ሻርማን እንደሚሉት "ምክንያቱ ሊሆን የሚችለው ተፈጥሮአዊ ማርጀት ሲሆን በአንዳንድ ህመምተኞች ላይ ግን ሊፍጥን ይችላል። ይህም በጸጉራቸው የቀለም ለውጥ ይታያል።"

በለንደን የልብ ህክምና ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሮፌሰር ሆኑት አሉን ሂውዝ ም ተመሳሳይ ነገር ይላሉ።

"አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ሁኔታው በዕድሜ ምክንያት የዘረመል መጎዳት የሚያስከትለው ምልክት እንደሆነ ይገምታሉ" ሲሉ ይገልጻሉ።

"ወንዶች ላይ በብዛት የራሰ በራነት የሚታየው አንድሮጅን ለተባለው ሆርሞን ሰውነታቸው በሚሰጠው ምላሽ ምክንያት ነው። ይህ ደግሞ ለልብ ችግር የመጋለጥ አዝማሚያን ሊጨምር ይችላል።"

እ.አ.አ በ2013 በጃፓን 37 ሺህ ሰዎች ላይ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳው ራሰ በራ ከሆኑ ወንዶች 32 በመቶ የሚሆኑት ለልብ ህመም ይጋለጣሉ።

በ2014 የተደረገ ጥናትን በመጥቀስ ፕሮፌሰር ሂውዝ ሽበት በቀጣይ ለልብ ህመም የ መጋለጥ ዕድልን እንደሚያመለክት ተናግረዋል። ነገር ግን ይህ ሌሎች ለልብ ህመም የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን እንዳለበት ያብራራሉ።

የልብዎን ጤንንት እንዴት ይጠብቃሉ

Image copyright PA
  • በቀን አምስት ጊዜ አ5ትክልትና ፍራፍሬ መመገብ
  • አለማጨስ
  • የአካል ብወቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
  • ክብደትን መቆጣጠር
  • ፋይበር ያላቸውን ምግቦች በብዛት መመገብ
  • ቅባትነት ያላቸውን ምግቦች መቀነስ
  • ጨው መቀነስ
  • አሳ መመገብ
  • አነስተኛ አልኮል መጠጣት
  • የታሸጉ ምግቦች እና መጠጦች ላይ ያሉ ይዘቶችን መመልከት

ምንጭ: ኤን ኤች ኤስ ቾይስስ

የምርምሩ መሪ የሆኑት ዶ/ር ድሃምዲፕ ሁማኔ ያለዕድሜያቸው ራሰ በራ የሚሆኑ ወይም ሸበት የሚያበቅሉ ወጣት ወንዶች "የልባቸውን ሁኔታ መከታተል እና ጤናማ የህይወት ዘይቤን መከተል አለባቸው" ብለዋ

የምርምር ቡድኑ አባል ሆኑት ዶ/ር ሳሺን ፓቲል በተለመደው የልብ በሽታ መንስኤዎች በማይገለጹ መልኩ በወጣት ወንዶች ላይ የለብ ችግር እየጨመረ ሲሆን ከጸጉር ጋር የተያያዘው ምክንያት "የታመነ መንስኤ ሊሆን ይችላል" ብለዋል።

በጄኔቫ ዩንቨርሲቲ ለልብ ህክምና ኃላፊ የሆኑት ፕሮፌሰር ማርኮ ሮፊ እንደሚሉት "መንስኤዎቹን ማጥናት ልብ ህመምን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ያስችላል።"

"ለልብ ህመም በአብዛኛው እንደመንስኤ የሚወሰዱት የስኳር በሽታ፣ በቤተሰብ ውስጥ ያለ ልብ ችግር፣ ሲጋራ አጫሽነት፣ ጤናማ ያልሆነ አኗኗር ዘይቤ፥ ከፍተኛ ኮሌስትሮል መጠን እና ከፍተና ደም ግፊት ናቸው።"

"ከላይ የተገለጹት ምክንያቶች ጨምሮ አዳዲስ መስኤዎች ለልብ ህመም መጋለጥ ዕድልን ሊጨምር ይችላል" ብለዋል። ል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ

በቢቢሲ ዙሪያ