የሱዳን ሴቶች ሱሪ በመልበሳቸው 'በነውረኛ አለባበስ' የተነሳባቸው ክስ ውድቅ ሆነ

Sudanese women in Khartoum Image copyright Getty Images

በሱዳን መዲና ካርቱም አንድ ዝግጅት ላይ 24 ሴቶች ሱሪ በመልበሳቸው 'ነውረኛ አለባበስ' በሚል የተነሳባቸው ክስ ተጥሏል።

ይህንን ዝግጅት ረቡዕ ዕለት የሞራል ፖሊስ ወረውት ነበር።

ጥፋተኛ ሆነው ቢገኙ 40 የጂራፍ መገረፍና ቅጣት ይጠብቃቸው ነበር።

የመብት አቀንቃኞች አስር ሺ የሚሆኑ ሴቶች በየዓመቱ 'ነውረኛ አለባበስ' በሚል ምክንያት ህግን ያልተከተለ መታሰር ተፈፃሚ ይሆንባቸዋል ይላሉ።

ይህ ህግም ከፍተኛ የሙስሊም ነዋሪ ላለባት ሱዳን ሱሪ፣አጭር ቀሚስ መልበስን መከልከል ክርስትና እምነት ተከታዮች ለሆኑት ታሳቢ ያላደረገ ነው ተብሏል።

በባህሉ መሰረት የሱዳን ሴቶች ሰፋ ያለ ቀሚስ ነው የሚለብሱት።

የመብት አቀንቃኟ አሚራ ኦስማን ኔዘርላንድሰ ለሚገኝ ሬድዮ ዳባንጋ እንደተናገሩት ይህ 'ፐብሊክ ኦርደር አክት' የሚባለው የሴቶችን መብት ይጥሳል ብለዋል።

"ይህ ዝግጅት የተደረገው በደቡባዊ ካርቱም በሚገኝ ዝግ ህንፃ ኤል ማሙራ ሲሆን ምንም እንኳን ከባለስልጣናቱ ፍቃድ ቢያገኙም ሱሪ ስለለበሱ ብቻ ታስረዋል" ብለዋል።

የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ አንቀፅ 152 የሚተገበረው በአደባባይ ላይ "ነውረኛ ፣ የተጋለጠ ወይንም ብዙዎችን ሊያበሳጭ የሚችል አለባበስ ሲለብሱ ነው።

ተያያዥ ርዕሶች