የቀይ ሽብር ተከሳሹ በሄግ የዕድሜ ልክ እስራት ተወሰነበት

የቀይ ሽብር ሰለባዎች ፎቶ Image copyright Getty Images

የቀይ ሽብር ተከሳሹ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት።

በኔዘርላንድስ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረው እሸቱ ዓለሙ 75 ሰዎችን በመግደል በጦር ወንጀለኝነት በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ ተብሏል።

የቀድሞው ኮሚኒስት መሪ መንግሥቱ ኃይለማሪያም ረዳት ነበር የተባለው ይህ ግለሰብ በሰዎች ላይ ሰቆቃን በመፈፀምና በከፋ አያያዝ ውስጥ እንዲቆዩ በማድረግ ጭምር ተከሶ ነበር።

የቀይ ሽብር ተከሳሹ ሄግ ፍርድ ቤት ቀረበ

ኢትዮጵያ ውስጥም በሌለበት በቀረበበት ክስ ሞት ተፈርዶበታል።

አቃቤ ሕግ ባቀረበው ክስ ''በአንድ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ 75 የሚሆኑ እስረኞች እንዲገደሉ ትዕዛዝ ሰጥቷል'' ብሏል።

የሟቾቹም አስከሬን በአንድ የጅምላ መቃብር ውስጥ እንዲቀበር ማድረጉንም አትቶ ነበር።

እስረኞች እጅና እግራቸው ታስሮ እንዲንጠለጠሉ በማድረግ የውስጥ እግራቸው በዱላ እንዲገረፉ አድረጓልም ተብሏል።

እርሱ ግን ችሎት ሲቀርብ "ወንጀለኛ አይደለሁም፤ ከዚህ በኋላ መኖርም አልፈለግም" ሲልም ተናግሮ ነበር።

ፍርድ ቤት የቀረበው የቀይ ሽብር ተከሳሽ ምስክሮችን ተማፀነ

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ