በሞቃዲሾ አጥፍቶ ጠፊው 18 ፖሊሶች ገደለ

አጥፍቶ አጥፊው 18 ፖሊሶች ገደለ Image copyright AFP

በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በአንድ የፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም እየተካሄድ ባለ ስልጠና ላይ አንድ አጥፍቶ ጠፊ ባደረሰው አደጋ ቢያንስ 18 ፖሊሶች ተገድለዋል።

ሌሎች 15 ሰዎች ደግሞ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ለማወቅም ተችሏል።

የፖሊስ ልብስ ለብሶ ወደ ዝግጅቱ ያመራው አጥፍቶ ጠፊ የኔ አባል ነው ሲል አል-ሸባብ ከአደጋው በኋላ አስታውቋል።

የዓይን እማኞች እንደተናገሩት ፖሊሶቹ የማሰልጠኛ ሜዳው ላይ በንጋት ተሰብሰበው ሰልፍ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ሳሉ ነው ፍንዳታው የተከሰተው።

ኢብራሂም ሁሴን የተባለ እንደ ፖሊስ እንደሚናገረው አጥፍቶ ጠፊው በርካታ ሰዎች ወደ ተሰበሰቡበት ሥፍራ ቢሄድ ኖሮ ከዚህም የከፋ አደጋ ይደርስ ነበር።

የሶማሊያ ፖሊስ ቃል አቀባይ ሞሐመድ ሁሴን እንዳስታወቁት ፖሊሶቹ ለብሔራዊ የፖሊስ ቀን በዓል ልምምድ እያደረጉ ነበር።

አልሸባብ ጥቃቱን አስመልክቶ በበይነ መረብ (ኢንተርኔት) በሰጠው መግለጫ "በእኛ እምነት የሌላቸው የማጥፋት ተልዕኮ" ሲል ሁኔታውን ገልፆታል።

ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚታመነው አል-ሸባብ በተባበሩት መንግሥታት በሚመራው ኃይል ከሞቃዲሾ ሙሉ በሙሉ ተጠራርጎ ቢወጣም አሁንም ጥቃት ማድረሱን አላቆመም።

በያዝነው ዓመት ወርሃ ጥቅምት ላይ ሞቃዲሾ ውስት በሚገኝ አንድ ሆቴል ባደረሰው ጥቃት በማድረስ የ20 ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉም አይዘነጋም።

ነገር ግን በተመሳሳይ ወር መኪና ላይ የተጠመደ ፈንጂ ፈንድቶ 500 የሚሆኑ ሰዎች የሞቱበት አደጋ እኔ አላቀነበርኩም ሲል ቡድኑ አሳውቋል።

22 ሺህ ያህል ወታደሮችን ያቀፈው የአፍሪካ ሕብረት ኃይል (አሚሶም) ሶማሊያን መልሶ በማቋቋም ለመደገፍ አሁንም በሃገሪቱ ይገኛል።

ተያያዥ ርዕሶች