ቶተንሃም ማንቸስተር ሲቲን ያስቆመው ይሆን?

ቶተንሃም ማንቸስተር ሲቲን ያስቆመው ይሆን? Image copyright Clive Brunskill

በአምናው የውድድር ዘመን ቶተንሃም ከሲቲ ጋር በነበረው ጨዋታ በአንዱ ሲያሸንፍ በሌላኛው አቻ መውጣቱ ይታወሳል። በዚህ ዓመትስ ሲቲን ለማስቆም አቅሙ ይኖረው ይሆን?

የቢቢሲ ስፖርቱ ማርክ ላውረንሰን ይህን ጨዋታ ጨምሮ ሌሎች የፕረሚዬር ሊጉን ፍልሚያዎች ግምት እንዲህ አስቀምጧል።

በዚህ ሳምንት ውጤት ግምት ከላውሮ ጋር የሚፎካከረው ዝነኛው ተዋናይና የጡጫ ተፋላሚ ጆን ሴና ነው። ሴና ለቢቢሲ ስፖርት ሲናገር "ታዋቂ ተጫዋች ጥራ ብትሉኝ አንድ የማውቀው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ብቻ ነው" ይላል።

ዕለተ ቅዳሜ

ሌይስተር ከክሪስታል ፓላስ

Image copyright BBC Sport

ክሪስታል ፓላስ መልካም የሚባል አቋም ላይ ይገኛል፤ በስድስት ጨዋታዎች ሽንፈት አላስተናገደም። ሌይስተርም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጣም የሚገርም እንቅስቃሴ ማሳየት የቻለ ቡድን ነው።

ወደቀድሞ ክለባቸው ሳውዝሃምፕተን በመጓዝ ሶስት ነጥብ የተመለሱት የሌይስተር ሲቲው ፒዮል በዚህ ጨዋታም ጥሩ ነገር እንደሚያስመዘግቡ አስባለሁ።

ላውሮ፡ 2 - 0

ሴና፡ 0 - 1

አርሴናል ከኒውካስል

Image copyright BBC Sport

ራፋ ቤኒቴዝ ነገሮችን ለመቀየር እየታገሉ ቢሆንም ምንም ስኬታማ ሊሆኑ አልቻሉም። ካለፉት ስምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ ነው ማግኘት የቻሉት።

አርሴናልም ቢሆን ካለፉት ሶስት ጨዋታዎች ሁለት ነጥብ ብቻ ነው የሰበሰበው።

ነገር ግን አሁን ለአርሴናል እንደ ኒውካስል ያለ ቀውስ ውስጥ የሚገኝ ቡድን እጅግ ተመራጭ ነው። መድፈኞቹ እንደሚያሸንፉም ተስፋዬ ነው።

ላውሮ፡ 3 - 0

ሴና፡ 0 - 1

ብራይተን ከበርንሌይ

Image copyright BBC Sport

ብራይተን አጀማመሩ ጥሩ የነበረ ቢሆንም አሁን አሁን ግን እጅግ እየደከመ መጥቷል።

በርንሌይ ደግሞ በተቃራኒው በጣም የሚያስደምም ጉዞ ላይ ይገኛል።

ላውሮ፡ 1 - 1

ሴና፡ 0 - 0

ቼልሲ ከሳውዝሃምፕተን

Image copyright BBC Sport

ቼልሲ በዌስትሃም ከደረሰባቸው የ1 - 0 ሽንፈት በኋላ ሃደርስፊልድን 3 - 1 በማሸነፍ ማገገም ችለዋል።

ሳውዝሃምፕተን ከአርሴናል ጋር በነበረው ጨዋታ አንድ ነጥብ ማግኘት ቢችልም በሳምንቱ አጋማሽ ግን በገዛ ሜዳው በሌይስተር 4 - 1 ተሸንፏል።

ሳውዝሃምፕተን ስታንፎርድ ብሪጅ ላይ ውጤታማ ይሆናል ብዬ አላምንም።

ላውሮ፡ 2 - 0

ሴና፡ 0 - 2

ስቶክ ከዌስትሃም

Image copyright BBC Sport

ከሁለት ሃያል ቡድኖች ጋር ተከታታይ ጨዋታ ያደረገው የዳቪድ ሞዬሱ ዌስትሃም ቼልሲን ሲያሸንፍ ከአርሴናል ጋር አቻ ተለያይቷል።

ስቶክ ደግሞ ካለፉት አምስት ጨዋታዎች በአንዱ ብቻ ድል ቀንቶታል። ማርክ ሁጌስ ስቶክ ከያዙ ጀምሮ እንዲህ ያለ ጫና ውስጥ ገብተው የሚያቁም አይመስለኝም።

ላውሮ፡ 1 - 1

ሴና፡ 0 - 1

ዋትፎርድ ከሃደርስፊልድ

Image copyright BBC Sport

ምንም እንኳ ዋትፎርድ ባለፉት ጨዋታዎች ሸንፈትን ቢያስተናግድም ከሃደርስፊልድ ጋር በሚኖረው ፍልሚያ ይሸነፋል ብዬ አልገምትም።

ሃደርስፊልድ በበኩሉ ወደ ወራጅ ቀጣናው እየተንሸራተተ ነው።

ላውሮ፡ 2 - 0

ሴና፡ 1 - 0

ማንቸስተር ሲቲ ከቶተንሃም

Image copyright BBC Sport

በአምናው የውድድር ዘመን ቶተንሃም ከሲቲ ጋር በነበረው ጨዋታ በአንዱ ሲያሸንፍ በሌላኛው አቻ መውጣቱ ይታወሳል። ፖቸቲኖ ከትላልቅ ቡድኖች ጋር በተለይ ከሜዳቸው ውጭ በሚኖራቸው ፍልሚያ ረገድ ጥሩ ታሪክ የላቸውም። ይህንን ጨዋታ በጣሙን ሊያስቡበት እንደሚገባም እምነቴ ነው።

እጅግ አስገራሚ አቋም ላይ የሚገኘውን ሲቲን ለመቋቋም ቶተንሃም ሁሉንም ነገር ማድረግ አለበት።

ላውሮ፡ 1 - 1

ሴና፡ 0 - 1

እሁድ

ዌስትብሮም ከዩናይትድ

Image copyright BBC Sport

አዲሱ የዌስት ብሮም አሰልጣኝ አለን ፓርዲው የመጀመሪያ ሶስት ነጥባቸውን ለማግኘት አሁንም እየታገሉ ነው።

በሜዳውቸው በሚጫወቱት በዚህ ጨዋታ ተጭነው ለመጫወት በሞከሩ ቁጥር ግን ለዩናይትድ ክፍተት እንዳይፈጥሩ ስጋት አለኝ።

ላውሮ፡ 0 - 1

ሴና፡ 0 - 1

ቦርንማውዝ ከሊቨርፑል

Image copyright BBC Sport

ሊቨርፑል ከኤቨርተንና ዌስትብሮም ጋር ከነበሯቸው ጨዋታዎች ሁለት ነጥብ ብቻ አግኝተዋል።

ይህ ጨዋታ ለሊቨርፑል አሪፍ የሚሆን ይመስለኛል። ቦርንማውዝ ተጭነው ከመጫወት ወደኋላ የሚሉ አይደሉም። ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሞ የዩርገን ክሎፑ ሊቨርፑል እንደሚያሸንፍ አስባለሁ።

ላውሮ፡ 0 - 2

ሴና፡ 0 - 1

ሰኞ

ኤቨርተን ከስዋንሲ

Image copyright BBC Sport

ኤቨርተን ሌላኛው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጣም የሚያስደንቅ ውጤት እያመጣ ያለ ቡድን ነው፤ ስዋንሲ ደግሞ በተቃራኒው ወደ ታች እየገሰገሰ ይገኛል።

ዋይኒ ሩኒ ለኤቨርተን ጎል ሲያስቆጥር ማየት እጅግ ያስደስታል። ከስዋንሲ የተገዛው ሲጉርድሰን በዚህ ጨዋታ ምን ዓይነት አቋም እንደሚያሳይም ይጠበቃል።

ላውሮ፡ 2 - 0

ሴና፡ 0 - 1