ሂጃብ ለባሿ የሕግ ብቃት መመዘኛ ፈተና ላይ እንዳትቀመጥ ተከለከለች

የሕግ ምሩቅ የሆነችው ናይጃሪያዊት ሕጋዊ ጠበቃ ሆኖ ለመሥራት የሚያስፈልገውን ፈተና ላይ ሂጃቧን አላወልቅም በማለቷ እንዳትቀመጥ ተደረገች። Image copyright Alamy

የሕግ ምሩቅ የሆነችው ናይጄሪያዊት ሕጋዊ ጠበቃ ሆኖ ለመሥራት የሚያስፈልገውን ፈተና ላይ ሂጃቧን አላወልቅም በማለቷ እንዳትቀመጥ ተደረገች።

የኦሎን ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ የሆነችው አማሳ ፊርደኡስ በአለባበሷ ምክንያት በአቡጃ ፈተናው ወደሚሰጥበት አዳራሽ ከመግባት ታግዳለች።

አማሳ ሂጃቧን ከማወልቀው ይልቅ ከላይ ሰው ሠራሽ ጸጉር(ዊግ) ማጠለቅ እንደፈቅድላት ስትጠይቅ እንደነበረ የሀገረቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ይህ ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የሕግ ክፍል የወጣውን የአለባበስ ሥርዓት እንደመቃወም ተደርጎ ነው በየኒቨርሲቲው የተወሰደው።

እርሷ ግን እርምጃውን "ሰብዓዊ መብቴን የጣሰ" ብላዋለች።

ጉዳዩ በማህበራዊ ሚዲያም ከፍተኛ ትኩረት ስቧል።