በኒውዮርክ አውደ-ርዕይ ላይ ስዕላቸው ከቀረቡ የጓንታናሞ እስረኞች መካከል እስካሁን ፍርድ ያላገኙም አሉበት

በኒውዮርክ አውደ-ርዕይ ላይ ስዕላቸው ከቀረቡ የጓንታናሞ እስረኞች መካከል እስካሁን ፍርድ ያላገኙም አሉበት

'ለባህሩ መዝሙር' በሚል ስም የቀረበው ኪነጥበባዊ ስራ በርካታ ተቃውሞዎችን አስተናግዷል። ስዕሎቹ በጓንታናሞ ታስረው የሚገኙ እና ከዚህ ቀደም ታስረው የነበሩ ታራሚዎች ነው። ስራቸው በአውደ-ርዕዩ ላይ ከቀረቡ ታራሚዎች መካከል እስካሁን ድረስ ፍርድ ያላገኙ ታራሚዎች አሉበት። ነገር ግን የኒው ዮርክ ጥቃት ሰለባ ቤተሰቦች ስራዎቹ መቅረብ አልነበረባቸውም ሲሉ ተቃውመዋል። አውደ-ርዕዩ ኒው ዮርክ በሚገኘው ጆን ጄይ የወንጀል ፍትህ ኮሌጅ የታየ ሲሆን ሰብስበው ያቀረቡት ደግሞ የወንጀል ህግ ፕሮፌሰሯ ኢሪን ቶምፕሰን ናቸው።