ጉግል ስለእርስዎ የያዘውን መረጃ መሰረዝ እንደሚችሉ ያውቃሉ?

ዓይን Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ጉግል ስለተጠቃሚዎቹ ብዙ ነገሮችን ያውቃል

ወደ በይነ-መረብ (ኢንትርኔት) ገብተን ስለአንድ ነገር ለመፈለግ በዓለም ታዋቂውን የበይነ-መረብ ጉግልን እንጠቀማለን።

በዚህም ስለምን ጉዳይ እንደፈለግን፣ ፍላጎታችን ምን እንደሆነ፣ የትኞቹን ድረ-ገፆች እንደጎበኘን እና ሌሎችም ነገሮች ተመዝግበው ይታወቃሉ።

"የጉግልን አገልግሎት ሲጠቀሙ ስለግል መረጃዎ እምነት ይጥሉብናል"

ይህንን ጉግል በአጠቃቀም ደንቦችና ሁኔታዎችን በመጀመሪያ መስመር ላይ በማስፈር የተጠቃሚዎች መረጃ በአስተማማኝ ሁኔታ እንደሚያዙ በግልፅ ያሰፈረበት ነው።

ነገር ግን ጉግል ከዚህ አንፃር ምናልባትም የማናውቀው ነገር ቢኖር ስለአጠቃቀማችን ተሰብስቦ የተያዘውን ማንኛውንም መረጃ ''ማይ አክቲቪቲ'' ወደሚለው ክፍል በመሄድ እስከጨረሻው መደምሰስ የሚያስችል መንገድ አለው።

ቀጥሎ ይህንን ለማድረግ የሚያስችሉ በርካታ ቀላል መንገዶችን ይመልከቱ።

1. የተጠቀምኩትን ሰርዝ

ምንግዜም ጉግልን ተጠቅመው ስለአንድ ነገር ሲፈልጉ፤ ጉግል ከአካውንትዎ ጋር አያይዞ ያስቀምጠዋል።

እያንዳንዱን በበይነ-መረብ ላይ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ፣ ማለትም ስለሞሏቸው ሰነዶች ወይም የተመለከቷቸውን ኢሜይሎች በሙሉ ምንም ሳያስቀር መዝግቦ ይይዛል።

ይህ ሁሉ መረጃ ''ማይ አክቲቪቲ'' በተባለ ስፍራ ላይ ተደራጅቶ ይቀመጣል። ስለዚህ የትም ሳይሆን ወደዚህ ቦታ ቀጥታ ይሂዱ።

Image copyright Captura de pantalla

ከዚያም የተለየ ርዕስን ወይም ገፅን የሚፈልጉ ከሆነ የመፈለጊያ መንገዱን በመጠቀም መሰረዝ፣ አሊያም ደግሞ ሁሉንም የተመዘገበ መረጃ ወይም በተወሰነ የቀን ገደብ ውስጥ ያሉትን መሰረዝ ይቻላል።

በዚህ ውስጥ ''ኑክሌር ኦፕሽን'' የሚለውን ከመረጥን ሁሉንም መረጃ እስከ ወዲያኛው ለመሰረዝ ያስችላል።

ሲሰርዙ ከጉግል በኩል ሊገጥምዎ ስለሚችል እርምጃ ማስጠንቀቂያ ያገኛሉ። ቢሆንም ግን በተጨባጭ የጉግል አጠቃቀምዎን የኋላ ታሪክ በመሰረዝዎ በሚጠቀሙበት የጉግል አካውንትም ሆነ መተግበሪያዎች ላይ የሚፈጠር ችግር አይኖርም።

2. በዩቲዩብ ላይ የተጠቀሙትን በሙሉ ለመሰረዝ

ጉግል ዩቲዩብን በመጠቀም ስለፈለጓቸው እና ስለተመለከቷቸው ምስሎች በሙሉ መዝግቦ ይይዛል።

Image copyright YouTube

ነገር ግን ይህም በቀላሉ ልንሰርዘው የምንችለው ነው። መጀመሪያ በግራ በኩል ካሉት ዝርዝሮች መካከል ''ሂስትሪ'' የሚለውን ይጫኑ፤ ከዚያም ''ክሊር ኦል ሰርች ሂስትሪ'' እና ''ክሊር ዋች ሂስትሪ'' የሚሉትን ይጫኑ። ወይም ፍለጋ ካደረጉባቸው ርዕሶች ወይም ከተመለከቷቸው መካከል የሚፈልጉትን መርጠው መሰረዝ ይችላሉ።

3. ማስታወቂያ አስነጋሪዎች ስለእርስዎ የሚያውቁትን ለመሰረዝ

ጉግል ስለእርስዎ ሁሉንም ነገር ከማወቁም በላይ የሚያውቀውንም መረጃ ለማስታወቂያ አስነጋሪዎች አሳልፎ ይሰጣል።

ለዚህም ነው ከእርስዎ በጉግል አማካኝነት ፍለጋ ካደረጉባቸው ነገሮች ጋር የሚመሳሰሉ ማስታወቂያዎች በተደጋጋሚ የሚያዩት።

ቢሆንም ግን አያስቡ፤ ስለእርስዎ ምን አይነት መረጃዎች ለማስታወቂያ አስነጋሪዎች እንደተሰጠ ለማወቅ ይችላሉ።

ይህንንም ለማድረግ ወደ ጉግል አካውንትዎ ይግቡና ''ፐርሰናል ኢንፎ ኤንድ ፕራይቬሲ'' ወደሚለውን ክፍል ይሂዱ።

Image copyright Google - Mark Shea

እዚያም ''አድስ ሴቲንግስ'' የሚለውን አማራጭ በመጫን ''ማኔጅ አድስ ሴቲንግስ'' ወደሚለው ይሂዱ።

ከዚያም ''አድስ ፐርሰናላይዜሽን'' የሚል አማራጭ ያገኛሉ። እናም በስተቀኝ በኩል ያለችውን ቁልፍ በማንሸራተት ከጉግል የተገኘውን መረጃዎትን መሰረት ያደረጉ ማስታወቂያዎች እንዳይደርስዎ ማድረግ ይችላሉ።

Image copyright Google - Mark Shea

ፈፅሞ ማስታወቂያ እንዳንቀበል የምናግድበት አማራጭ ግን የለንም።

Image copyright Google - Mark Shea

ይህን ሲያደርጉ ጉግል እርስዎ ካለዎት ፍላጎት አንፃር ተመሳሳይ ማስታወቂያዎችን እንደማያዩ ያስጠነቅቅዎታል ነገር ግን የመምረጥ ውሳኔው የእርስዎ ነው የሚሆነው።

4. የነበሩባቸውን የጉግል ቦታ ጠቋሚን ለመሰረዝ

የሞባይል ስልክን የመሳሰሉ ዘመናዊ የመገልገያ መሳሪያዎችን የሚጠቀሙ ከሆነ የተጓዙባቸውን ቦታዎች በሙሉ መዝግቦ ይይዛል።

በጉግል ቦታ ጠቋሚ በኩል የተመዘገቡትን የእርስዎን መረጃ ለመሰረዝ ይህንን ገፅ መመልከት ያስፈልግዎታል።

የቦታ ጠቋሚውን መዝጋት የሚችሉ ሲሆን ቀን ወይም ሰዓት ለይተው የተመዘገቡ ቦታ ጠቋሚ መረጃዎችን መሰረዝ ይችላሉ። በተጨማሪም ''ኦን ዘ ዌስት ባስኬት በተን'' የሚለውን በመጫን ካደረጓቸው ጉዞዎች ውስጥ ወይም ደርሰውባቸው ከነበሩ ስፍራዎች መካከል መርጠው መሰረዝ ይችላሉ።