አፍሪካን በፎቶ በዚህ ሳምንት

ስለአፍሪካ እና አፍሪካዊያን የሚያሳዩ የሳምንቱ ምርጥ ፎቶዎች

ደቡብ አፍሪካዊው ጥልቅ ዋናተኛ ማክሰኞ በደርባን በሚገኝ የአሳ ማርቢያ ገንዳ ውስጥ እንደ ገና አባት ለብሶ ሰቲንግ ሬይ የተሰኘውን የአሳ ዝርያ ሲመግብ Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ማክሰኞ እለት በደቡብ አፍሪካ ደርባን በሚገኝ የዓሳ ማርቢያ ገንዳ ውስጥ ጠላቂ ዋናተኛው እንደ ገና አባት ለብሶ ሰቲንግ ሬይ የተሰኘውን የአሳ ዝርያ ሲመግብ
ይህ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ከሱማሊያ በረሃብ እና በግጭት ምክንያት የተሰደዱ 34000 ሶማሊያውያንን የሚገኙበት ሲሆን ከኢትዮጵያ ድንበር በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። በመጠለያ ጣቢያው ከሚገኙ ስደተኞች መካከል 67% የሚሆኑት እድሜያቸው ከ 18 ዓመት በታች ነው። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ማክሰኞ ዕለት ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ወጣት ሴቶች መረብ ኳስ ሲጫወቱ
ግብፃዊው አካል ጉዳተኛ ሞሀመድ አዜማ በካይሮ በተደረገው የመጀመሪያ የእግር ኳስ ግጥሚያ እየተጫወተ Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ የግብፅ አካል ጉዳተኞች እግር ኳስ ቡድን ቅዳሜ ዕለት በካይሮ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደረጉት እነዚህ ተጫዋቾች አንድ ቀን ለአለም ዋንጫ ለመድረስ ተስፋ አድርገዋል
ዕረቡ እለት ኬኒያዊው የማሳይ ጎሳ አባል ጎረምሳ ወደ ወጣትነት እድሜ መሻገሩን ለማሳየት አንድ ወር የፈጀ የግርዘት በዓልን ካሳለፈ በኋላ ከጫካ እንደወጣ Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ዕረቡ ዕለት ኬኒያዊው የማሳይ ጎሳ አባል ጎረምሳ ወደ ወጣትነት እድሜ መሻገሩን ለማሳየት ከተገረዘ በኋላ ከጫካ እንደወጣ . . .
እነዚህ ግርዘት የተፈፀመላቸው የማሳይ ወጣቶች ያደኗቸውን ወፎች ከባህላዊ አልባሳት ጋር ለብሰው ወደ የአገር ሽማግሌዎች ቡራኬ ለመቀበል ሲሄዱ-ኬንያ Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ እነዚህ ታዳጊዎች ባህላዊ አልባሳት ለብሰው የአገር ሽማግሌዎችን ቡራኬ ለመቀበል ሲሄዱ
በአይቮሪ ኮስት ዋና ከተማ አቢጃን በተደረገ 8ኛው የአፍሪካውያን ሞዴሎች አውደ-ርዕይ ሽልማት ስነ ስርአት ላይ ቻዳዊቷ ሞዴል ብሪጌት በአበባ ቅርፅ የተሰራ ልብስ ለብሳ Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ዕረቡ እለት በአይቮሪ ኮስት ዋና ከተማ አቢጃን በተደረገ የአልባሳት ትዕይንት የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ ቻዳዊቷ ሞዴል ብሪጌት በአበባ ቅርፅ የተሰራ ልብስ ለብሳ
በናይጄሪያ የንግድ ከተማ ሌጎስ ከሰኞ ዕለት ጀምሮ የገና በአልን በማስመልከት ሕንፃዎችና መንገዶች በመብራት አሸብርቀዋል Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በናይጄሪያዋ የንግድ ከተማ ሌጎስ ከሰኞ ዕለት ጀምሮ የገና በዓልን በማስመልከት ሕንፃዎች በመብራት አሸብርቀዋል

ምስሎቹ ከ AFP፣ EPA እና Reuters የተወሰዱ ናቸው

ተያያዥ ርዕሶች