ፕሪሚየር ሊግ ግምት፡ የላውሮ የሳምንቱ ሊግ ጨዋታዎች ግምት

ስዋንሲዎች ካለፉት 10 ጨዋታዎች አራት ነጥቦችን ብቻ ነው መሰብሰብ የቻሉት። ራሳቸውን በማሻሻል ላይ ከሚገኙት ክሪስታል ፓላሶች ጋር በሚኖራቸው ጫወታ ይህንን መጥፎ ጉዞአቸውን ይገቱ ይሆን?

የቢቢሲው የስፖርት ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን ጨዋታውን ክሪስታል ፓላስ 2 ለ 1 ያሸንፋል ሲል ግምቱን ያስቀምጣል። በዚህ ይስማማሉ?

የላውሮን የሳምንቱን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል።

አርብ

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ አርሴናል ከ ሊቨርፑል

አርሴናል ከ ሊቨርፑል

ባለፉት አራት ጨዋታዎች እነዚህ ሁለት ቡድኖች እርስ በእርስ ሲገናኙ ብዙ ጎሎችን አስቆጥረዋል። ይህኛውም ከዚህ የተለየ አይደለም።

እንደሌሎች ትልልቅ ጨዋታዎች ውጤቱ አቻ እንደሚሆን ብገምትም ብዙ ጎሎች እንደሚቆጠሩ አምናለሁ።

የላውሮ ግምት: 2-2

ቅዳሜ

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ ኤቨርተን ከ ቼልሲ

ኤቨርተን ከ ቼልሲ

ኤቨርተን በሳም አላርዳይስ ስር እየተሻሻለ ሲሆን ይህ ጨዋታ ደግሞ ትልቁ መፈተኛቸው ነው።

ያለአጥቂያቸው አልቫሮ ሞራታ የሚጫወቱት ቼልሲዎች አሁንም ከባድ እንደሚሆኑ አምናለሁ።

የላውሮ ግምት: : 0-2

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ ብራይተን ከ ዋትፎርድ

ብራይተን ከ ዋትፎርድ

ዋትፎርዶች አጀማመራቸው ጥሩ ቢሆንም ካለፉት አምስት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ ነው ያገኙት።

ብራይተኖች ከዋትፎርዶች በአራት ነጥብ ዝቅ ብለው የሚገኙ ሲሆን ጨዋታውንም ያሸንፋሉ ብዬ አስባለሁ።

የላውሮ ግምት: 2-0

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ ማንቸስተር ሲቲ ከ በርንማውዝ

ማንቸስተር ሲቲ ከ በርንማውዝ

በርንማውዝ በካራባኦ ዋንጫ በተከላካዮች ስህተት ባለቀ ሰዓት በቼልሲ በተቆጠረበት ጎል የተሸነፈ ሲሆን ሲቲን ያቆማል ብዬ አላስብም።

ሲቲ በገና ሰሞን ጨዋታዎች ካሉበት ተጋጣሚዎች አንጻር ነጥብ የሚጥል አይመስልም።

የላውሮ ግምት: 3-0

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ ሳውዝሃምፕተን ከ ሃደርስፊልድ

ሳውዝሃምፕተን ከ ሃደርስፊልድ

ሃደርስፊልዶች በዚህ ሳምንትም ሦስት ነጥብ የሚያገኙ አይመስለኝም።

ከሴንት ሜሪ ስታዲም ግን ነጥብ ይዘው ይመለሳሉ።

ሳውዝሃምፕተኖች ከዘጠኝ ጨዋታዎች አንዱን ብቻ ነው ማሸነፍ የቻሉት።

የላውሮ ግምት: : 1-1

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ ስቶክ ከ ዌስት ብሮም

ስቶክ ከ ዌስት ብሮም

እነዚህ ሁለት ቡድኖች ለማሸነፍ ከፍተኛ ግፊት ውስጥ ገብተዋል።

ይህ ጨዋታ በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል ብዬ አስባለሁ። ጨዋታው 1 ለ 1 የተጠናቀቅ ሲሆን ምርጥ ጨዋታ ይሆናል ብዬ ግን አላስብም።

የላውሮ ግምት: 1-1

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ ስዋንሲ ከ ክሪስታል ፓላስ

ስዋንሲ ከ ክሪስታል ፓላስ

ስዋንሲዎች በተከታታይ አሰልጣኞችን እየቀያየሩ ነው።

ስዋንሲዎች ጥሩ አስተዳደር ያላቸው ቢሆንም አሁን ግን ይህን የሚገልጽ ነገር አይታይም።

የላውሮ ግምት: 1-2

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ ዌስት ሃም ከ ኒውካስትል

ዌስት ሃም ከ ኒውካስትል

ራሳቸውን በማሻሻል ላይ ከሚገኙ ቡድኖች መካከል ዌስት ሃም አንዱ ነው።

በዚህ ጨዋታ ግን ሊጠነቀቁ ይገባል። ምክንያቱም ኒውካስትል በመጥፎ ጊዜ ላይ ስለሚገኝ ይህንን ለመቀየር ይታገላል።

ዴቪድ ሞዬስ የራቃቸውን በራስ መተማመን ያገኙት ይመስላል። ኒውካስትሎች ደግሞ የቼልሲውን ኬኔዲን በውሰት በመውሰድ ራሳቸውን በማጠናከር ላይ ይገኛሉ።

የላውሮ ግምት: 2-0

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ በርንሌይ ከ ቶተንሃም

በርንሌይ ከ ቶተንሃም

ቶተንሃሞች ባለፈው ሳምንት በማንቸስተር ሲቲ የተሸነፉ ሲሆን ከእነሱ በላይ ካሉ ቡድኖች ጋር ውጤት ለማስመዝገብ እየተቸገሩ ይገኛሉ።

በርንሌይዎች ጥሩ ጊዜ በማሳለፍ ላይ ይገኛሉ።

የላውሮ ግምት: 0-2

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ ሌስተር ከ ማንቸስተር ዩናይትድ

ሌስተር ከ ማንቸስተር ዩናይትድ

ማንቸስተር ዩናይትዶች በካራባኦ ዋንጫ መሸነፋቸው ባለፈው ዓመት ያነሱትን የኮሙኒቲ ሽልድ፣ የሊግ ካፕ እና የዩሮፓ ሊግ እንደማያነሱ ያረጋገጠ ነው።

ፕሪሚየር ሊጉንም ሆነ ሻምፒዮንስ ሊጉን ያሸንፋሉ ብዬ አላስብም። ይህ ደግሞ የተወሰነ ጫና ያሳድርባቸዋል።

በካራባኦ ዋንጫ በማንቸስተር ሲቲ የተሸነፉት ሌስተሮች ለሞሪንሆ ቡድን ትልቅ ፈተና እንደሚሆኑ እገምታለሁ።

የላውሮ ግምት: 0-2