ለልጇ የምታነብለት መጽሐፍ ያላገኘችው እናት እራሷ ፃፈች

ለልጇ የምታነብለት መጽሐፍ ያላገኘችው እናት እራሷ ፃፈች

ጃኔት ኩዋኬ ለሁለት ዓመት ልጇ ካዮዴ የምታነብለት መጻሕፍት ፍለጋ በአቅራቢያዋ የሚገኙትን መደብሮች አሰሰች። በለንደን የምትኖረው የቀድሞ አጭር ርቀት ሯጯ ምንም ሳታገኝ ስትቀር ቀበሮው ፌሚ የተሰኘ ገጸባህሪ ፈጠረች።