ካናዳ የቬንዝዌላን አምባሳደር አባረረች

ፕሬዝዳንት ማዱሮ

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ,

ፕሬዝዳንት ማዱሮ በቀጣዩ የፈረንጆቹ ዓመት በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

ካናዳ የቬንዝዌላውን አምባሳደር ዊልመር ባሪኤንቶስ ፈርናንዴዝ እና ምክትላቸውን አንጄላ ሄሬራ ከሀገር ላስወጣ ነው አለች።

የካናዳ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሯ ክርስችያ ፍሬላንድ ሀገራቸው ከዚህ ውሳኔ የደረሰችው ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ የካናዳ ዲፕሎማቶች ከካራካስ መባረራቸውን ተከትሎ ነው ብለዋል።

ቬንዝዌላ በተደጋጋሚ ካናዳን በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ትገባለች ስትል ከሳታለች።

ካናዳ በበኩሏ የፕሬዝዳንት ማዱሮ መንግስት የሰብዓዊ መብት አያያዙ አስከፊ ነው ስትል ትወቅሳለች።

''እኛ ካናዳዊያን የዜጎቹን ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ ምብት ነጥቆ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ከሚያሳጣ መንግሥት ጋር ወዳጅነት ሊኖረን አይችልም'' ሲሉ የካናዳው የውጪ ጉዳይ ሚንስትሯ ክርስችያ ፍሬላንድ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

የፎቶው ባለመብት, Ronald Grant

የምስሉ መግለጫ,

በመጠናቀቅ ላይ ባለው 2017 በነበሩ ጸረ-መንግሥት ተቋሞዎች ከ120 ሰዎች በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል።

በመጠናቀቅ ላይ ባለው 2017 በነበሩ ጸረ-መንግሥት ተቃውሞዎች ከ120 ሰዎች በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል።

የቬንዝዌላው አምባሳደር ከሀገር ውጪ መሆናቸውን እና ወደ ካናዳ እንዲገቡ አንደማይፈቀድላቸው እንዲሁም ምክትል አምባሳደሯ ካናዳን ለቀው አንዲወጡ እንደተነገራቸው የውጪ ጉዳይ ሚንስትሯ ጨምረው ተናግረዋል።

የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደርም በፕሬዝዳንት ማዱሮ ላይ ማዕቀቦችን ጥሏል እንዲሁም ''አምባገነን'' ሲል ፈርጇቸዋል ማዱሮን።

የቬንዙዌላ ተቃዋሚዎች ፕሬዝደንት ማዱሮ እና የቀድሞ ፕሬዝደንት ሁጎ ቻቬዝ በሶሻሊስት ሥርዓተ-መንግሥታቸው የቬንዝዌላን ኢኮኖሚ ክፉኛ ጎድተዋል ሲሉ ድምጻቸውን ያሰማሉ።

ቬንዝዌላ በዓለማችን ላይ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትን ካለባቸው ሀገራት አንዷ ስትሆን መድሃኒትን ጨምሮ መሰረታዊ የሚባሉ ሸቀጦች እጥረት በተደጋጋሚ ያጋጥማታል።

የፕሬዝደንት ማዱሮ የስድስት ዓመት የስልጣን ዘመን እአአ 2019 ይጠናቀቃል። በቀጣዩ ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ለተጨማሪ የስልጣን ዘመን እንደሚወዳደሩ አስታወቀዋል።

ከጥቂት ቀናት በፊትም የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ማገዳቸው ተዘግቧል።