ብራዚል የቬንዝዌላን ዲፕሎማት አባረረች

ፕሬዝደንት ኒኮላስ ማዱሮ Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ የቬንዝዌላው ፕሬዝደንት ኒኮላስ ማዱሮ ብራዚል የሕግ የበላይነትን ጥሳለች ሲሉ ኮንነዋል።

ብራዚል የቬንዝዌላውን አንጋፋ ዲፕሎማት ጌራርዶ ዴልጋዶን በብራዚል ተቀባይነት የሌለው ግለሰብ ስትል አውጃለች።

ካናዳም የቬንዝዌላውን አምባሳደር እና ምክትላቸውን 'ከሃገር ላስወጣ' ነው ማለቷ ይታወሳል።

ካናዳ የቬንዝዌላን አምባሳደር አባረረች

ብራዚል ከዚህ ውሳኔ የደረሰችው ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ቬንዝዌላ የብራዚልን አምሳደር ከካራካስ ካባረረች በኋላ ነው።

ቬንዝዌላ አምባሳደሩን ያባረረችበትን ምክንያት ስታስረዳ፤ ብራዚል ግራ ዘመም የነበሩትን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዴልማ ሩሴፍ ያለ አግባብ ነው ክስ ቀርቦባቸው ከስልጣን እንዲወርዱ የተደረገው ትላለች።

ቬንዝዌላ በተደጋጋሚ ካናዳን በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ትገባለች በማለት ባሳለፈነው ሳምንት መጨረሻ የካናዳ አምባሳደርንም ከሀገር አስወጥታለች።

የካናዳዋ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ክርስችያ ፍሬላንድ በሰጡት መግለጫ ''እኛ ካናዳዊያን የዜጎቹን ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብት ነጥቆ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ከሚያሳጣ መንግሥት ጋር ወዳጅነት ሊኖረን አይችልም'' ሲሉ ተደምጠዋል።

የቬንዝዌላው አምባሳደር ከሃገር ውጪ መሆናቸውን እና ወደ ካናዳ እንዲገቡ አንደማይፈቀድላቸው እንዲሁም ምክትል አምባሳደሯ ካናዳን ለቀው አንዲወጡ እንደተነገራቸው የውጪ ጉዳይ ሚንስትሯ ጨምረው ተናግረዋል።

Image copyright Reuters

የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደርም በፕሬዝዳንት ማዱሮ ላይ ማዕቀቦችን ከመጣሉም በላይ ፕሬዘደንቱን ''አምባገነን'' ሲል መፈረጁ ይታወሳል።

የቬንዙዌላ ተቃዋሚዎች ፕሬዝደንት ማዱሮ እና የቀድሞ ፕሬዝደንት ሁጎ ቻቬዝ በሶሻሊስት ሥርዓተ-መንግሥታቸው የቬንዝዌላን ኢኮኖሚ ክፉኛ ጎድተዋል ሲሉ ድምጻቸውን ያሰማሉ።

የቬንዙዌላ መንግሥት በበኩሉ አሜሪካ በሃገራችን ላይ የጣለችው ማዕቀብ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መቀነስ ለኢኮኖሚ ድቀቱ ምክንያት ነው ይላሉ።

ቬንዝዌላ በዓለማችን ላይ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትን ካለባቸው ሀገራት አንዷ ስትሆን መድሃኒትን ጨምሮ መሰረታዊ የሚባሉ ሸቀጦች እጥረት በተደጋጋሚ ያጋጥማታል።

የፕሬዝደንት ማዱሮ የስድስት ዓመት የስልጣን ዘመን እአአ 2019 ይጠናቀቃል። ቢሆንም ተቃውሞ የበረታባቸው ማዱሮ በቀጣዩ ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ለተጨማሪ የስልጣን ዘመን እንደሚወዳደሩ አስታወቀዋል።

ማዱሮ ከጥቂት ቀናት በፊት የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ከሃገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ማገዳቸው ተዘግቧል።

ተያያዥ ርዕሶች