አስደንጋጩ የመብራት ሂሳብ

ዶላር Image copyright Getty Creative Stock

በአሜሪካ ፔንሲልቫኒያ ግዛት 284 ቢሊዮን ዶላር የመብራት ሂሳብ ክፈይ ተብላ የተጠየቀችው ሴት በቢሊዮን ዶላር ክፈይ መባሏ በእጅጉ አስደንግጧታል።

ማሪ ሆሮማንስኪ ይህን የሚያክል ገንዘብ መጠየቋ ተአምር ሆኖባት እንደነበር ትናገራለች።

"የሂሳብ መጠየቂያውን ሳይ ማመን አልቻልኩም አይኔ ተጎልጉሎ ሊወጣ የደረሰ ነበር የመሰለኝ'' በማለት፤ ይህ ማናልባት ለገና ዛፍ በተጠቀሟቸው መብራቶች ምክንያት ሊሆን ይችላል ብላ እንዳሰበች ተናግራለች።

በመጨረሻ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት አቅራቢው ኩባንያ ነገሩ ስህተት እንደሆነና ትክክኛ ሂሳቡ 284 ዶላር ብቻ መሆኑን አስታውቋል።

የኩባንያው ቃል አቀባይ ስህተቱ እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ እንደማያውቁ ተናግረዋል።

"በኩባንያው ታሪክ የዚህ አይነት ከፍተኛ ሂሳብ አይቼ አላውቅም" በማለት ቃል አቀባዩ ማርክ ዱብሪን ለኤሪ ኒውስ ተናግረዋል።

ተጠቃሚዋ ማሪ ስህተቱ እንዲታረም ላደረገችው ጥረትም ኩባንያው እንደሚያመሰግናት ቃል አቀባዩ ገልፀዋል።

ተያያዥ ርዕሶች