ከንቲባ ለመሆን ፈተናዎችን የሰበረች

ዛሂ ቤንካራ
አጭር የምስል መግለጫ ዛሂ ቤንካራ በአልጄሪያ ከንቲባ ሆነው ከተመረጡ 4 ሴቶች መካከል አንዷ ነች

አንዳንዶች በአልጄሪያ ሴቶች በሚኖሩበት ከተማ ከንቲባ ከመሆን ፕሬዝዳንት መሆን ይቀላቸዋል ይላሉ።

ዛሂ ቤንካራ ደግሞ ይህንን ከማንም በላይ ጠንቅቃ ታውቃለች። በሰሜን አፍሪካ ሃገራት በቅርቡ ከተደረጉ ምርጫዎች ከ 4 ሴቶች መካከል ከንቲባ ሆና የተመረጠች ነች።

የሷ ድል የበለጠ የሚያስደንቀው የምትኖርበት ከተማ ቺጋራ ባህሪይ ሲታይ ነው። በምስራቃዊ አልጄሪያ የምትገኘው ይህች ከተማ ባህል ስር የሰደደባት እና ሴቶች እንደዚህ አይነት ህዝባዊ ሃላፊነቶች ላይ እምብዛም የማይታዩባት ነች።

እዚህ ላይ ደግሞ እስላማዊ ለሆነ ፖለቲካ ፓርቲ መወዳደሯ ሲጨመር በዋናነት የለዘብተኞችን ድጋፍ ያሳጣታል። እንደዛም ሆኖ ማሸነፏ የበለጠ አስገራሚ ነው።

ይህች ሴት በአካባቢዋ ፕሮፌሰሯ እየተባለች ነው የምትጠራው፤ ያ ደግሞ ያላትን ተወዳችነት ያሳያል።

"የመረጡኝ ስለሚያቁኝ ነው። ለነሱ ያደረኩትን ያውቃሉ እናም ያምኑኛል"ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች።

በርግጥም የትምህርት ደረጃዋና የስራ ልምዷ መሳጭ ነው፤ ወ/ሮ ቤንካራ የመብት ተሟጋች ብቻ አይደለችም፤ በማህበረሰቡ ውስጥ የተቸገሩትን ትደግፋለች፤ በአካባቢዋ በሚገኝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትም ለአመታት እስላማዊ ሕግን ስታስተምርም ቆይታለች።

ይህ ግን በመማሪያ ክፍል ውስጥ ብቻ የተገደበ አልነበረም፤ በመስኪዶች፣ በበጎ አድራጎት ማህበራት እና በተለያዩ ማህበረሰብ ውይይቶች ላይ እስላማዊ ህግን፥ ትምህርት እና የሰው ልጅ እድገትን ታስተምራለች።

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በአልጄሪያ ከ1962 ጀምሮ ሴቶች በምርጫ መወዳደር እና ስልጣን መያዝ ይችሉ ነበር

በምርጫ ለመወዳደር ፍላጎት እንዳላት ስትገልፅ በማህበረሰቧ ውስጥ ቀድሞም የነበራት ድጋፍ እንዳለ ነበር።

"ዛሂ እንደማንኛዋም ሴት አይደለችም ከ 15 ወንዶች ትበልጣለች" ሲል ተናግሯል አንድ ደጋፊዋ።

የምትወዳደረው እስላማዊ ፓርቲን ወክላ መሆኑ እንደታወቀ ግን ምስሏ በማህበራዊ ድረ ገፅ በፍጥነት መሽከርከር ጀመረ፣ ከወግ አጥባቂዎች ከለዘብተኛ ፓርቲ ደጋፊዎችም ዘንድ የተለያዩ ነገሮች መሰንዘር ጀመሩ።

አንዳንድ ኃይማኖተኛ ያልሆኑ መራጮች ደግሞ በሂጃቧ መሳለቅ ጀመሩ፤ ሌሎቹ ደግሞ በተክለሰውነቷ።

ወ/ሮ ቤንካራ ከቁብም አልፃፈችውም። "ተሳዳቢ እና ግድ የማይሰጣቸው ሰዎች ለሰው ልጅ የሚያስፈልገው ነገር በምሰራው ስራ ብቁ ሆኜ መገኘቴ እና ለሰው ልጅ የማደርጋቸው ነገሮች ጥሩ መሆናቸውን ቀስ ብለው ይማራሉ፤ ይረዳሉም " ብላለች።

እሷ ይህንን ብትልም ጠንካራ ወግ አጥባቂዎች የመወዳደር ብቃቷን ይጠራጠራሉ።

"ፈጣሪ በሴቶች የሚመሩ ሕዝቦችን ረግሟል" ሲል አንድ ሰው ማህበራዊ ድረ ገፅ ላይ ፅፏል።

ሌሎች ደግሞ "ሴቶች ቤት ውስጥ መቆየት አለባቸው የሚለውን ከገሃነም የሚጠብቅሽን የነብያችንን አስተምህሮ ተላልፈሻል" ሲሉ ያስጠነቅቃሉ።

ወ/ሮ ባንካራ እነዚህን አስተያየቶችን ማየቷን እና ለመዋጋት መሞከሯን አልሸሸገችም።

"በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ረዥም ሰአት ወስጄ በእስልምና ሴቶችን ለመንግስት ስልጣን መምረጥ ስህተት ነው የሚሉትን ተከራክሬያለሁ" ብላለች።

" እንዲህ አይነት የተሳሳተ ሃሳብ የያዙ ሰዎችን እንዴት ማሳመን እነዳለብኝ አውቃለሁ፤ በርካቶቹም አእምሯቸውን ቀይረው በመጨረሻ ለኔ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።"

ለወ/ሮ ቤንካራ የሚታገሉ ሌሎችም አሉ።

"በሃገሬ ሕዝቦች አፈርኩ" ሲል አንዱ ፅፏል፤ "በጠንካራዋ ሴት ላይ ያልተገባ አስተያየት እየሰጣችሁ ነው። እናንተ በምግባራችሁ ብታንሱም እሷ ግን ጠንካራ፣ የተማረች አልጄሪያዊ ሙስሊም ናት። ለምን ግን ለሃገራችን የሚጠቅም ሃሳብ አታነሱም?''

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ እንደ ቤንካራ ያሉ ሴቶች ሌሎች የነሱን መንገድ እንዲከተሉ ያነሳሱ ይሆን?

ድጋፉ ደግሞ ማንነታቸው ከማይታወቁ የበይነ መረብ ሰዎች ብቻ አይደለም የሚመጣው።

የሐረካት ሙጅታማ ኢስሊም መሪ ሆነው አብደልማጂድ ሜንሳራ ጠንካራ ተወዳዳሪዎች እንዳሉባት ያውቃል።

"ጠንካራ ሰብዕና ያላት፣ ብቁ እና የተሰጠች ናት። የምትሰራውን ታውቃለች" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል።

እሷም እሱ ልክ እንደሆነ ታወቃለች፤ ሰዎች እንድትወድቅ ይፈልጋሉ እሷ ግን ፈፅሞ አስባው አታውቅም።

"ለደጋፊዎቼ ማረጋገጥ የምፈልገው እኔን በመምረጣቸው አለመሳሳታቸውን ነው" ትላለች "ሙስናን፣በስልጣን መባለግን እና አላግባብ መጠቀምን እዋጋለሁ። ሁሌም እንደማደርገው ለመረጠኝ ከተማ ሕዝብ እሰራለሁ። "