የላውሮ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ የበዓል ሰሞን ጨዋታዎች ግምት

ላውሮ፡ ዌስትብሮም አርሴናልን ያሸንፋል Image copyright Mike Hewitt

የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ የበዓል ሰሞን ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻም ሲቀጥሉ ሊቨርፑል ከሌይስተር፣ ዩናይትድ ከሳውዝሃምፕተን፣ አርሴናል ከዌስትብሮም እና ሲቲ ከፓላስ የሚጠበቁ ፍልሚያዎች ናቸው። ለውሮ የሁሉንም ጨዋታዎች ግምት እንዲህ አስቀምጧል።

ዕለተ ቅዳሜ

ቦርንማውዝ ከኤቨርተን

ቦርንማውዝ ባለፈው ከዌስትሃም ጋር የነበረውን ጨዋታ በአቻ ውጤት ማጠናቀቁ ትንሽ አስገርሞኛል። አጨቃጫቂ የዳኝነት ውሳኔዎች የተላለፉበትም ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

ቢሆንም አቻ ለቦርንማውዝ መልካም ውጤት ነው ብዬ ነው የማስበው። ኤቨርተንም ወደ ዌስትብሮም ሜዳ አቅንቶ አንድ ነጥብ ይዞ መምጣት ችሏል። ሳም አላርዳየስ ቡድኑን ከያዙት በኋላ ከስድስት ጨዋታዎች 12 ነጥብ ማግኘት ችለዋል።

ቦርንማውዝ ከኤቨርተን ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ድል ይዞ እንደሚወጣ አስባለሁ።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 0

ቼልሲ ከስቶክ

Image copyright Getty Images

ስቶኮች በበዓል ሰሞን ጨዋታ ካደረጓቸው ጨዋታዎች እስካሁን አራት ነጥብ መሰብሰብ ችለዋል። ቢሆንም ከቼልሲ ጋር ከሚኖራቸው ጨዋታ ምንም ዓይነት ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አላስብም።

በተለይ በዚህ የውድድር ዘመን ቼልሲ በሜዳው ውጤት በመሰብሰብ የተሻለ ታሪክ አለው፤ በበርንሌይና ሲቲ ከመሸነፋቸው ውጭ።

የላውሮ ግምት፡ 3 - 0

ሃደርስፊልድ ከበርንሌይ

ይህ ጨዋታ በታጣም ደማቅ እንደሚሆን አስባለሁ። ምክንያቱም ሁለቱም ክለቦች ኳስ ይዘው ለመጫወት ወደ ኋላ አይሉም።

በርንሌይ ወደ ፕሪሚዬር ሊጉ ካደገ በኋላ ያደረገውን ነገር ሃደርስፊልድ መድገም አለበት ብዬ አስባለሁ።

የላውሮ ግምት፡ 1 - 0

ሊቨርፑል ከሌይስተር

Image copyright BBC Sport

የሳውዝሃምፕተኑ ቨርጂል ቫን ዳይክ በጥሩ የዝውውር መስኮት ሊቨርፑልን እንደሚቀላቀል ከተነገረ በኋላ የቀያዮቹ ደጋፊዎች ደስተኛ እንደሚሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ምክንያቱም ሊቨርፑል በተከላካይ ሥፍራ ላይ እንደ ቫን ዳይክ ያለ ጠንካራ ተጫዋች እንደሚያስፈልገው አያጠራጥርም።

ምንም እንኳን ሊቨርፑል ከስዋንሲ የነበረውን ጨዋታ በቀላሉ ቢያሸንፍም ሌይስተር ቀላል ተጋጣሚ ይሆናል የሚል እምነት የለኝም።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 0

ኒውካስል ከብራይተን

ኒውካስል ከሲቲ ጋር የነበራቸውን ጨዋታ በአብዛኛው በመከላከል አሳልፈዋል፤ ባይሳካላቸውም ቅሉ።

ከብራይተን ጋር በሚኖረው ጨዋታ ግን ለመከላከል ወስነው እንደማይገቡ እርግጠኛ ነኝ።

የላውሮ ግምት፡ 1 - 1

ዋትፎርድ ከስዋንሲ

ስዋንሲ ከሊቨርፑል ጋር በነበረው ጨዋታ ያሳየው አቋም እጅግ ደካማ ነበር። ስዋንሲ አሁን ባለው አቋም የዓለማችን ደካማው ቡድን ነው ብል ማንም አይቃወመኝም።

ዋትፎርድ ከአራት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ሌይስተርን በማሸነፍ ነቃ ብሏል። ቢሆንም ስዋንሲ ለዚህ ጨዋታ ተዳክሞ እንደማይቀርብ እገምታለሁ።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 0

ዩናይት ከሳውዝሃምፕተን

Image copyright BBC Sport

ሳውዝሃምፕተን ቫን ዳይክን ለሊቨርፑል የሸጠበትን 75 ሚሊዮን ዩሮ የሚጠጋ ገንዘብ በጥር ወር ሌሎች ተጫዋቾችን በመግዛት የተሻለ ሆኖ ይቀርብበታል ብዬ አምናለሁ።

የሞሪሲዮ ፔሌግሪኖ ቡድን ወደ ኦልድ ትራፎርድ ተጉዞ በራሱ የሜዳ ክልል ተጫውቶ ነጥብ ለማጋራት ይሞክራል ብዬ አስባለሁ። ይሳካል ብዬ ግን አልገምትም።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 0

እሁድ

ክሪስታል ፓላስ ከሲቲ

Image copyright BBC Sport

ክሪስታል ፓላስ ሲቲ ያስቆመዋል ብዬ አላስብም።

የሮይ ሆጅሰን ልጆች ቡድን ሲቲዎች ጎል እንዳያስቆጥሩ እንደሚያጨናንቁ ባምንም ሲቲ ቀዳዳ ፈልጎ ማስቆጠሩ አይቀሬ ነው።

የላውሮ ግምት፡ 0 - 3

ዌስትብሮም ከአርሴናል

Image copyright BBC Sport

ዌስትብሮም ምንም ጨዋታ ሳያሸንፍ እነሆ 18 ጨዋታዎችን ተጉዟል። ኤቨርተን ሊያሸንፉ የሚችሉበትን ወርቃማ ዕድልም አጥተዋል። ወጣም ወረደም በቅርቡ እንደሚሳላቸው አምናለሁ።

አርሴናል እያሳየ ካለው ወጣ ያልሆነ አቋም አንፃር ከዌስትብሮም ፈተና ይጠብቀዋል።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 1