ሰሜን ኮሪያ የተቋረጠውን የስልክ ግንኙነት ጀመረች

South Korea Image copyright AFP

ሰሜን ኮሪያ በኪም ጆንግ ኡን ትዕዛዝ ከሁለት ዓመታት በፊት የዘጋችውን ከደቡብ ኮሪያ ጋር በአስቸኳይ የሚያገናናትን የስልክ መስመር መልሳ ከፈተች።

ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን በኩል ዛሬ (ረቡዕ) የተደረገው የስልክ ጥሪ እንደደረሳት አረጋግጣለች። የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከቀናት በፊት ከሶል ጋር መነጋገር እንደሚፈልጉ አሳውቀው ነበር።

ሰሜን ኮሪያ የስልክ መስመሯን ክፍት ያደረገችው ከደቡብ ኮሪያ ጋር በክረምት ስሚካሄደው ኦሊምፒክ ለመነጋገር ነው።

ሁለቱ ኮሪያዎች እንደ አውሮፓውያኑ ከ2015 ወዲህ በከፍተኛ ልዑክ ደረጃ ውይይት አድርገው አያውቁም። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር የሚያገናኛትን መስመር ስታቋርጥ የደቡብ ኮሪያን ጥሪም ለመመለስ ፍቃደኛ ሳትሆን ቆይታለች።

ደቡብ ኮሪያ የስልክ መስመሩን መከፈት ይፋ ያደረገችው በቴሌቪዥን ነው። ሰሜን ኮሪያም ከደቡብ ኮሪያ ጋር በቅንነትና በግልፅነት እንደምትወያይ አስታውቃለች።

የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ሙን ጃ ኢን ቃል አቀባይ የስልክ መስመሩ ዳግም ክፍት መደረጉ ትልቅ እርምጃ እንደሆነ ተናግረዋል።

"ይህ በማንኛውም ጊዜ መነጋገር የሚቻልበትን እድል ይፈጥራል"ብለዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ