አፍሪካን በምስል፡ ከ2017 መጨረሻ እስከ 2018 መባቻ

እነሆ ያለፈውን ሳምንት የሚዳስሱ ምስሎች ከተለያዩ የአፍሪካ ቦታዎች የተሰባሰቡበት ዐምድ፡

ዚምባብዌ

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ቪክቶሪያ ሀይቅ አካባቢ የተሰባሰቡ የዚምባብዌ ሰዎች አዲስ ዓመትን ሲቀበሉ...

ኬንያ

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በኬንያ መዲና ናይሮቢም ነዋሪዎች መሃል ከተማ በመሰባሰብ እኩለ ሌሊት ላይ 2018ን ሲቀበሉ ታይተዋል

ደቡብ አፍሪቃ

Image copyright AP
አጭር የምስል መግለጫ በደቡብ አፍሪካዋ ጆሃንስበርግ ከተማ 2018ን ለመቀበል የወጡ ሰዎች በተንቀሳቃሽ ስልካቸውን ትዝታን ሲቀርፁ ተስተውለዋል

ከደቡብ አፍሪካ ሳንወጣ. . .

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ በ2018 የመጀመሪያው ቀን ደቡብ አፍሪካውያን ወደ ደርባን የባህር ዳርቻ በመሄድ ዓመቱን እንዲህ ተቀብለውታል

ናይጄሪያ

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ዕለተ ሰኞ በፈረንጆቹ ጥር 1/2018 አቡጃ ያሉ ናይጄሪያውያን ሕፃናት እንዲህ ሲቦርቁ በካሜራ ዕይታ ውስጥ ገብተዋል

ኢትዮ-ጅቡቲ

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ረቡዕ ዕለት የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ጣቢያ ሠራተኞች ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ጅቡቲ የሚያቀናውን ባቡር የመጀመሪያ ጉዞ በማስመልከት የተነሱት ፎቶ

በግብፅ በረሃ

Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ በተመሳሳይ ቀን ኤርትራዊያን ስደተኞች እስራኤልን ከግብፅ በሚያዋስነው በረሃ አካባቢ ሺሻ ሲያጨሱ. . .

ሱዳን

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ እሁድ ዕለት 62ኛውን የሱዳን ነፃነት ቀን በማስመልከት የሱዳኑ ፕሬዚደንት ኦማር አል-ባሽር ለህዝባቸው ንግግር አድርገው ነበር

ላይቤሪያ

Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ በአዲሱ ዓመት ዋዜማ በላይቤሪያ ዋና ከተማ ሞኖሮቪያ የሃገሪቱ ዜጎች የፕሬዚደንታዊ ምርጫውን ውጤት ሲታዘቡ ነበር። ምርጫውን የቀድሞው እግር ኳሰኛ ጆርጅ ዊሃ ማሸነፉ አይዘነጋም