ዶ/ር ደብረፂዮን ምክትል ርዕሰ-መስተዳደር ሆኑ

ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል Image copyright Facebook

በቅርቡ የህወሓት ሊቀመንበር እንዲሆኑ የተመረጡት ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ።

ህወሓት ባካሄደው ግምገማ ከድርጅቱ ሊቀ-መንበርነትና ከሥራ አስፈፃሚ አባልነታቸው የተነሱት አቶ አባይ ወልዱ ከትግራይ ክልል ርዕሰ-መስተዳደርነት ተነስተዋል።

የርዕሰ-መስተዳደሩን ቦታ መያዝ የሚገባው በክልሉ ምክር ቤቱ አባል በመሆኑ ዶክተር ደብረፂዮን ርዕሰ-መስተዳድር ሆነው መሾም ስላልተቻለ ነው በምክትል ርዕሰ-መስተዳደርነት የተሾሙት።

የክልኩ ምክር ቤት ምንጮች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ዶክተር ደብረፂዮን ምንም እንኳን ምክትል ርዕሰ-መስተዳደርነት ሆነው ቢሾሙም የርዕሰ-መስተዳደሩን ሥራ ሸፍነው ያከናውናሉ።

ዶክተር አዲስዓለም ባሌማም በቀድሞ የምክትል ርዕሰ-መስተዳደርነት ቦታቸው ላይ እንዲቀጥሉ መወሰኑን ተገልጿል።

ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በፌደራል መንግሥቱ ያላቸውን የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ሚኒስትርነት ቦታ በሌላ ሰው እንደሚተካ ይጠበቃል።

በተጨማሪም በጥቂት ወራት ውስጥ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቅ የማሟያ ምርጫ ላይ በመወዳደር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የክልሉን ምክርቤት አባልነት መቀመጫን ይይዛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ተያያዥ ርዕሶች