ሊቨርፑል ከሲቲ. . .ማን ያሸንፍ ይሆን?

ሊቨርፑል ከሲቲ Image copyright Stu Forster

የፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎችን ግምት በየሳምንቱ የሚያስቀምጠው የቢቢሲ ስፖርት ተንታኙ ማርክ ላውረንሰን ሊቨርፑል ከሲቲ የሚያደርጉትን ተጠባቂ ጨዋታ ጨምሮ የፍልሚያዎቹን ግምት እንዲህ አስቀምጧል።

ቅዳሜ

ቼልሲ ከሌይስተር

Image copyright BBC Sport

ጉዳት ላይ የሚገኘው ጄሚ ቫርዲ ለዚህ ጨዋታ ብቁ እንደሚሆን አስባለሁ፤ ሌሎቹም ተጫዋቾች ጥሩ የእረፍት ጊዜ እንደነበራቸው እገምታለሁ።

ቼልሲ በተቃራኒው በጣም ሩጫ የበዛበት ሳምንት አሳልፏል። ቢሆንም ጨዋታው በቼልሲ ሜዳ ስለሆነ ትንሽ ቀለል ሊል እንደሚችል ነው የኔ ግምት።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 0

ክሪስታል ፓላስ ከበርንሌይ

ምንም እንኳ በርንሌይዎች አካሄዳቸው ጥሩ ቢሆንም እንቅፋት አላጣቸውም። ከማንቸስተር ዩናይት ጋር በነበራቸውን ጨዋታ ባለቀ ሰዓት በተቆጠረባቸው ጎል ነጥብ ለመጋራት ተገደዋል፤ ሊቨርፑሎችም ባለቀ ሰዓት በተቆጠረ ጎል ነጥብ ነጥቀዋቸዋል።

ክሪስታል ፓላስም በሜዳው ቀላል ቡድን አይደለም፤ ቢሆንም እኔ ግምቴ ለበርንሌይ ነው።

ላውሮ ግምት፡ 1 - 2

ሃደርስፊልድ ከዌስትሃም

የዌስትሃም አሰልጣኝ ዴቪድ ሞዬስ በጣም ጥሩ አቋም ላይ ናቸው።

ሃደርስፊልድን በሜዳው ማሸነፍ የቻሉት ሲቲ፣ ቼልሲና ቶተንሃም ብቻ ናቸው። ቢሆንም ዌስትሃም ይህን ጨዋታ ይሸነፋል ብዬ አልገምትም።

የላውሮ፡ 1 - 1

ኒውካስል ከስዋንሲ

የኒውካስሉ አሠልጣኝ ራፋኤል ቤኒቴዝ ብዙ ቢጥሩም ቀጣዩ ወር ለእርሳቸው ቀላል እንደማይሆን ግልፅ ነው። ምንም ትግል ውስጥ ቢሆኑም እንኳ ከስዋንሲ በተሻለ የመውረድ ተስፋቸው የለመለመ እንደሆነ አስባለሁ።

ስዋንሲም አዳዲስ ተጫዋቾች ማሟላት ያለበት ቢሆንም በዚህ አጭር ጊዜ ያን ያህል ለውጥ የሚያመጣ ተጫዋች ያገኛሉ ብዬ አላምንም።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 0

ዋትፎርድ ከሳውዝሃምፕተን

ሳውዝሃምፕተን ቫን ዳይክን በሸጡበት ገንዘብ ተጫዋቾችን በማዛወር ለውጥ ማምጣት አለባቸው ባይ ነኝ። ያለዛ የመውረድ ዕጣ ሊገጥማቸው ይችላል።

ዋትፎርድም ቢሆን ተደላድሎ የተቀመጠ ቡድን አይደለም።

የላውሮ ግምት፡ 1 - 1

ዌስትብሮም ከብራይተን

ዌስትብሮም ከነሃሴ ጀምሮ አንድም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለም። ቢሆንም ትግላቸውን አላቆሙም፤ ይህ ጨዋታ ምናልባትም ያንን የሚያሳኩበት ይሆናል ብዬ እገምታለሁ።

ብራይተንም ቢሆኑ ከወገብ በታች በላይ ያሉ ስለሆኑ መታገል ይኖርባቸዋል።

የላውሮ ግምት፡ 1 - 0

ቶተንሃም ከኤቨርተን

Image copyright BBC Sport

ቶተንሃም ካለፉት ስምንት ጨዋታዎች በሲቲ ብቻ ሲሸነፉ ከዌስትሃም ጋር ነጥብ ተጋርተዋል። ሌሎቹን ግን በድል መወጣት ችለዋል።

አላርዳይስ ቶተንሃምን ባለማንቀሳቀስ ነጥብ ሊያስጥሉ እንደሚሞክሩ ባስብም አይሳካለቸውም ባይ ነኝ።

ላውሮ ግምት፡ 2 - 0

ሁድ

ቦርናማውዝ ከአርሴናል

Image copyright BBC Sport

አርሴናል በዚህም ጨዋታ ሶስት ነጥብ ይዞ ይወጣል ብዬ አላምንም። ምንም ዓይነት ወጥ አቋም እያሳየም አይደለም።

ጨዋታው ጥሩ ፍልሚያ እንደሚታይበት አስባለሁ።

የላውሮ ግምት፡ 1 - 1

ሊቨርፑል ከሲቲ

Image copyright BBC Sport

ምንም እንኳ ሲቲዎች በጣም ጥሩ አቋም ላይ ቢሆኑም ይህ ጨዋታ ሊከብዳቸው እንደሚችል ነው የኔ ግምት።

ሲቲዎች በዩናይትድና በቼልሲ ሜዳ ሄደው ቢያሸንፉም ሊቨርፑል ሜዳ ላይ ሁኔታዎች ቀላል አይሆኑም።

የላውሮ ግምት፡ 1 - 1

ሰኞ

ማንቸስተር ዩናይትድ ከስቶክ

Image copyright BBC Sport

ስቶኮች አሁን ላይ ያለ አሠልጣኝ ነው ያሉት። አሠልጣኝ ኖራቸውም አልኖራቸውም ከዩናይት ጋር ባለው ፍልሚያ ምንም ዓይነት ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አላምንም።

ዩናይትዶች ጥሩ ጨዋታ እያሳዩ በማሸነፍ ላይ ናቸው። ሰኞ ዕለት ይህ እንደሚቀጥል አምናለሁ።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 0