በዚህ ሳምንት አፍሪካ እንዴት ሰነበተች?...እነሆ ምላሹ በምስል

ዲክሞክራቲክ ኮንጎ ሪሊክ

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ አርብ ዕለት በመሬት መንሸራተት በወደመ የዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐበሊክ ክፍል አንዲት ሕፃን ስታልፍ ታይታያለች። ሃገሪቱ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ ደጋግሞ ይጎበኛታል

ሱዳን

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በተመሳሳይ ቀን በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ውስጥ አንድ ግለሰብ ዳቦ ሸምቶ ሲመለስ በካሜራ ዕይታ ውስጥ ገብቷል

ሊቢያ

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ በፈራረሰችው የሊቢያዋ ሻሃት ከተማ ሁለት ፈረሶች እረፍታቸውን ሲኮመኩሙ ፎቶ የተነሱት በተመሳሳይ ዕለተ አርብ ነው

አልጄሪያ

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ በሊቢያ ጎረቤት ሃገር አልጄሪያ ደግሞ እልም ባለው በረሃ ላይ እሁድ ዕለት በረዶ ጥሏል። መሰል ክስተት እዚህ ሥፍራ ላይ ሲከሰት በሦስት ዓመታት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ነው

ኬንያ

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በኬንያ መዲና ናይሮቢ የቻይና ምርት የሆኑ ጫማዎች እንዲህ ተደርድረው ይታያሉ። ኬንያ የቻይናን ምርት በገፍ ከሚጠቀሙ የአፍሪካ ሃገራት መካከል አንዷ ናት

ቤኒን

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ የአትላንቲክ ውቅያኖስ የሚያዋስናት ቤኒን ነዋሪዎች ሃገራዊውን የኤሊ ቀን ያከበሩትም በዚህ ሳምንት ነው

ግብፅ

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ የግብጿ ኮፕቲክ ቤተ-ክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ታዎድሮስ ሁለተኛ የገና ዋዜማን ምክንያት በማድረግ ቅዳሜ ዕለት የፀሎት ሥነ-ሥርዓት ሲመሩ

ኢትዮጵያ

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች የእየሱስ ክርስቶስን ልደት ታህሳስ 29 አክበረዋል። በላሊበላ በስተሰሜን የሚገኝ አንድ ምዕመንም በጧፍ ብርሃን መፅሐፍ ቅዱስ ሲያነብ በካሜራ ዕይታ ውስት ገብቷል

ላሊበላ

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ በላሊበላ ቤተ-አማኑኤል ቤተ-ክርስትያን የገና በዓልን እያከበሩ ያሉ ምእመናን የታዩትም በበዓለ ገናው ዋዜማ ነው

ተያያዥ ርዕሶች