የጋርት ክሩክስ የሳምንቱ ምርጥ ቡድን

የጋርት የሳምንቱ ምርጥ ቡድን

መጨረሻው መድረሱ አይቀርም ነበር ይህም በሊቨርፑል ተሳክቷል። እስከዛሬ ሳይሸነፍ የመጣው የማንቸስተር ሲቲ በአንፊልድ ስቴድየም በተካሄደው ጨዋታ ላይ 4-3 ተረትቷል።

ያለፈው ሳምንት መጨረሻ አራተኛውን ቦታ ለመያዝ ሲሯሯጡ ለነበሩት ቶተንሃሞችም ውጤቱ ጥሩ ነበር። በተለይ ኤቨርተንን 4-0 ከማሸነፋቸውም በላይ ሁለቱ ተቀናቃኞቻቸው ማለትም ቼልሲና አርሴናል ነጥብ ጥለዋል።

አርሴናሎች በሚያሳዝን ሁኔታ ከቦርንማውዝ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ላይ ተሸንፈዋል። ቼልሲም ጎል ለማግባት ሃሳብ ያጠራቸው ይመስል ከሌስተር ጋር 0 ለ 0 ጨዋታቸውን አጠናቀዋል።

ከሁሉም በላይ ግን ማሸነፍ በጣም ያስፈልጋቸው የነበሩት ዌስት ብሮም፣ ክሪስታል ፓላስና ዌስት ሃም ድል ተጎናጽፈዋል።

ጎል ጠባቂ - ዌይን ሔነሲ (ክሪስታል ፓላስ)

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ በተሳተፈባቸው ባለፉት አራት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች እንድም ጎል ሳይገባበት በመቆየቱ ስሙን አስመዝግበል

የዌልሱ ተጫወች በተሳተፈባቸው ባለፉት አራት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች እንድም ጎል ሳይቆጠርበት ቆይቷል፤ ይህም ከዚህ ቀደም የተጫወታቸው 18 ጨዋታዎች ተደምረው በአንድ አሻሽሎታል።

ለፓላስ በጣም ከባድና አስጨናቂ በነበረበትም ሰዓት ዌይን የሚያስገርም ድፍረት በማሳየት ጎሉን አጥብቆ ተከላክሏል። አሁን የእርሱ ተሳትፎ በተለይ ጎል ሳይቆጥርበት መቀጠል መቻሉ የቡድኑ ጠንካራ አካል አድርጎታል።

ተከላካይ - አንድሬያስ ክሪስተንሰን (ቼልሲ)

Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ክሪስተንሰን ምንም አንኳን ለ57 ደቂቃ ብቻ ቢጫወትም ከማንኛውም የቼልሲ ተጫዋች በላይ በመከላከል አምስት ኳሶችን አድኗል

ከሌስተር ጋር በተጫወቱበት ወቅት ክሪስተንሰን ምንም አንኳን ለ57 ደቂቃ ብቻ ቢጫወትም ከማንኛውም የቼልሲ ተጫዋች በላይ በመከላከሉ በኩል አምስት ኳሶችን አድኗል።

በክሎድ ፑዎል ሥር ሆኖ የተጠናከረው የሌስተር ቡድን ሰማያዊዮቹን እያጠቁ በነበሩበት ወቅት ነበር አንድሬያስ ክሪስተንሰን ጌሪ ካሂልን ተክቶ የገባው።

በሚገርም ሁኔታ ከጨዋታው ፍጥነት ጋር ራሱን አስተካክሎ ከመጫወቱም በላይ ከሪያድ ማሕሬዝን ጋር ተጠንቅቆ ሲጫወት ነበር።

ተከላካይ - ሔሪ ማጓየር (ሌስተር)

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ሔሪ ማጔርን ኳስ በማዳን የበለጠው አንድሬያስ ክሪስተንሰን ብቻ ነው እሱም በቼልሲና በሌስተር መካከል በተደረገው ጨዋታ በአንድ ነው የተለያዩት

ሔሪ ማጓየርን ኳስ በማዳን የበለጠው አንድሬያስ ክሪስተንሰን ብቻ ነው።

ሔሪ ማጓየር በዚህ ጨዋታ ለሌስተር የጀርባ አጥንት ሆኖ ያገለገለ ሲሆን አልቫሮ ሞራታን በአንድ በኩል ኤደን ሐዛርድን ደግሞ በሌላ በኩል ወጥሮ ይዟቸው ነበረ።

ተከላካይ - ጆኒ ኤቫንስ (ዌስት ብሮም)

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ከብራይተን ጋር በተደረገው ጫዋታ ላይ የመጀመሪኣውን ግብ ያስቆጠረው ጆኒ ኤቫንስ የዘንድሮን የፕሪምየር ሊግ ጨዋታውን በ20ኛው ሙከራ አሸነፈ

ስለጆኒ ኤቫንስ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ብዙ ቢወራም ግብ ሲያስቆጥር ያሳየው የደስታ አገላለጽ ባለበት በዌስት ብሮም ደስተኛ መሆኑን የሚያመላክት ነው።

አለን ፓርድዩ ለመግዛት ሲል መሸጥ ቢኖርበትም እንኳን ያሳየውን ጭፈራ ለተመለከተ የኤቫንስ መልቀቅ ከባድ ሊሆን ይችላል። ለቡድኑ ጥልቅ ፍቅር እንዳለው ያስታውቃል።

የኤቫንስ ዕጣ ፈንታ ምንም ይሁን ምን ለሥራው ባለው አክብሮት እንደምሳሌ ሊቀርብ የሚገባው ተጫዋች በመሆኑ ለጨዋታው ምስጋና ይገባዋል።

አማካይ ተጫዋች - ሄዩንግ-ሚን (ቶተንሃም)

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሰን ሄዩንግ-ሚን ለቶተንሃም በሜዳቸው በአምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ጎል ሲያስቆጥር ከዠርሜን ዴፎ ቀጥሎ ሁለተኛው ተጫዋች ሆኗል።

ሰን ሄዩንግ-ሚን ለቶተንሃም በሜዳቸው በአምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ጎል ሲያስቆጥር ከዠርሜን ዴፎ ቀጥሎ ሁለተኛው ተጫዋች ሆኗል።

ሶን ሄዩንግ-ሚን አንድ አስቆጠረ፣ አንድ ለጎል አመቻችቶ ሰጠ። ከኤቨርተን ጋር በተደረገው ጨዋታ ላይ ግቡ ቋሚ ገጭቶ ቢመለስበትም አጨዋወቱ ግን ውብ ነበር። ይህ የደቡብ ኮሪያ ተወላጅ ባለው ጉልበትና ቅልጥፍና የሚታወቅ ነው። ጋረት ክሩክስ ''በጣም የምወድለት ከልቡ መጫወቱንና ሁሌም ከከንፈሩ ፈገግታና ሳቅ ስለማይለየው ነው። የሶን ፈገግታ ብቻውን የዌምብሌይን ስቴድየም ያበራል'' ብሏል።

አማካይ ተጫዋች - አሌክስ ኦክስሌድ-ምበርሌይን (ሊቨርፑል)

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ኦክስሌድ-ቻምበርሌይን እስከዛሬ አሳይቶ በማያውቀው መልኩ በዚህ የፕሪምየር ሊግ ውድድር ዓመት ለሊቨርፑል ሶስት ግቦችን አስቆጥሯል።

ኦክስሌድ-ቻምበርሌይን እስከዛሬ አሳይቶ በማያውቀው መልኩ በዚህ የፕሪምየር ሊግ ውድድር ዓመት ለሊቨርፑል ሶስት ግቦችን አስቆጥሯል።

ጋርት ክሩክስ ''ይህ ተጫዋች በሊቨርፑል በተሰጠው የሥራ ድርሻ ተመቻችቶ ማየቴ ደስ ብሎኛል'' ብሏል። በመቀጠልም ''ሳውዝሃፕተንም አርሴናልም እያለ ከእርሱ ብዙ እጠብቅ ነበር'' ብሏል።

ከማንቸስተር ሲቲ ጋር በተጫወተ ጊዜ ግን በእራሱ የሚተማመን ተጫዋች ነበር። ከመተማመኑም የተነሳ ያለፍርሃት ከኬቪን ደብሮይን ጋር ተፎካክሮ ረትቶታል።

አማካይ ተጫዋች - ጀምስ ዋርድ ፕሮውስ (ሳውዝሃምፕተን)

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ጀምስ ዋርድ ፕሮውስ ዒላማቸውን ከጠበቁ ሁለት ሙከራዎች ሁለት ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

ጀምስ ዋርድ ፕሮውስ ዒላማቸውን ከጠበቁ ሁለት ሙከራዎች ሁለት ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

በአብዱላዬ ዱኩር ያስቆጠራት ጎል በዳኛው ስህተት ጸድቃለች። ግን ዳኛው ተጫዋቹ ኳሷን በእጁ መንካቱን አላዩም። ይህ ዓይነቱ አጋጣሚ ነው በቪዲዮ የሚታገዝ ዳኝነት ይኑር አይኑር የሚለው ክርክር እንዲነሳ የሚያደርገው።

አማካይ - ማኑዌል ላንዚኒ (ዌስት ሃም)

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ማኑዌል ላንዚኒ ሃደርስፊልድን 4 ለ 1 ባሸነፉበት ጨዋታ ሁለት ጎሎችን ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሪሚር ሊጉ ለማስቆጠር ችሏል።

ማኑዌል ላንዚኒ ሃደርስፊልድን 4 ለ 1 ባሸነፉበት ጨዋታ ሁለት ጎሎችን ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሪሚር ሊጉ ለማስቆጠር ችሏል።

ተጫዋቹ የዲሚትሪ ፓዬን በመተካት ላይ ይገኛል። ድንቅ ችሎታውን ያሳየው አርጀንቲናዊው አራተኛው ጎል ለማስቆጠር እና ማርኮ አርናውቶቪችን ለመርዳት ረዥም ርቀት የሮጠበት መንገድ አስገራሚ ነው።

አጥቂ - ማርኮ አርናውቶቪች (ዌስት ሃም)

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ አርናውቶቪች ባለፉት ሰባት ፕሪሚር ሊግ ጨዋታዎች በሰባት ጎሎች ላይ ተሳትፎ ነበረው። ባለፉት ጨዋታዎች እየተሻሻለም ይገኛል።

አርናውቶቪች ባለፉት ሰባት ፕሪሚር ሊግ ጨዋታዎች በሰባት ጎሎች ላይ ተሳትፎ ነበረው። ባለፉት ጨዋታዎች እየተሻሻለም ይገኛል።

አርናውቶቪች፣ ላንዚኒ እና አንዲ ካሮል በጋራ አንድ ላይ መሰለፍ ከጀመሩ ዌስት ሃም ጥሩ ተፎካካሪ ይሆናል።

አጥቂ - ሮቤርቶ ፊርሚኖ (ሊቨርፑል)

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ፊርሚኖ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ባደረጋቸው ስድስት ፕሪሚር ሊግ ጨዋታዎች በስድስት ጎሎች ላይ ተሳትፎ ነበረው።

ፊርሚኖ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ባደረጋቸው ስድስት ፕሪሚር ሊግ ጨዋታዎች በስድስት ጎሎች ላይ ተሳትፎ ነበረው።

የብራዚላዊው ኩቲንሆ ከሊቨርፑል ወደ ባርሴሎና ማቅናቱን ተከትሎም ብዙ ሃላፊነት ለመሸከም የተዘጋጀ ይመስላል።

አጥቂ - ሳዲዮ ማኔ (ሊቨርፑል)

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ማኔ አንፊልድ ላይ ባደረጋቸው 22 ጨዋታዎች ሽንፈትን አላስተናገደም።

ማኔ አንፊልድ ላይ ባደረጋቸው 22 ጨዋታዎች ሽንፈትን አላስተናገደም።

አጥቂው ያስቆጠረው ጎል ጨዋታው ለማንቸስተር ሲቲ ከባድ ያደረገች ነበረች። ተጫዋቹ ያለፈውን ዓመት ያህል ጎሎች ማስቆጠር ባይችል እንኳን በጠንካራ ሠራተኛነቱ ያካክሰዋል።