በኬንያ እንደ መነኩሴ የለበሰችው 35,000 ዶላር ዘረፈች

እንደ መነኩሴ የለበሱ ሴቶች
አጭር የምስል መግለጫ እንደ መነኩሴ የለበሱ ሴቶች

የኬንያ ፖሊስ እንደ መነኩሴ ለብሳ ከውጭ ምንዛሬ ቢሮ 35,000 ዶላር የዘረፈችውን ሴት እያደነ ነው።

መርማሪዎቹን ያስደነቃቸው ነገር ቢኖር የወንጀሉ ፍጥነት ነበር።

ይህንን ዝርፊያ ለማካሄድ ከ10 ደቂቃ በታች የፈጀ ሲሆን በር ላይ ያሉ የጥበቃ አባላት እንኳ ዝርፊያ መፈፀሙን አላወቁም ተብሏል።

በናይሮቢ ካረን በሚባለው ስፍራ ተጠርጣሪዋ ተፈትሻ ወደ የውጭ ምንዛሬ ቢሮ ስትገባ የሚያሳይ የሲሲቲቪ ካሜራ ምስል ተገኝቷል።

ከዛም ካዝናው ወዳለበት እና በብረት ፍርግርግ በር ወደተዘጋው ክፍል ከመግባቷ በፊት የምንዛሬ ቢሮ ሰራተኛዋን አነጋግራታለች።

ከአጭር ምልልስ በኋላ የድርጅቱ ሰራተኛ ካዝናውን ከፍተችላት፤ እንደ መነኩሴ የለበሰችው ዘራፊ ካዝናውን ሙልጭ አድርጋ ከመዝረፏ በፊት ሰራተኛዋ ወንበሩ ላይ ተደፋች። ቀጥሎ የተካሄደው ዝርፊያ በተረጋጋ ሁኔታ የተፈፀመ ነው።

በተመሳሳይም በሕዳር ወር በናይሮቢ ታሂካ በሚባል ስፍራ 30 ሜትር የውስጥ ለውስጥ መንገድ በመቆፈርና የባንኩ ካዝና የሚገኝበት ክፍል ውስጥ በመግባት 500,000 ዶላር ተዘርፎ ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች