የሳምንቱ የፕሪሚየር ሊግ ግምቶች

ኦልትራፎርድ ላይ ባለፈው ጥር ማንቸስተር ዩናይትድ እና በርንሌይ ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት ሊጠናቀቅ ነው ሲባል ባለቀ ሰዓት ሊንጋርድ ያስቆጠራት ጎል ባለሜዳዎቹን አሸናፊ አደርጋለች። በመጪው ቅዳሜ ተርፍ ሙር ላይ ምን አይነት ውጤት ይመዘገባል?

የቢቢሲው የስፖርት ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን "በሊጉ ስድስት ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻሉት በርንሌይዎች ውጤት እየራቃቸው ነው" ይላል።

ቅዳሜ

Image copyright BBC Sport

ብራይተን ከ ቼልሲ

ቼልሲ በቅጣት ላይ የሚገኙት አልቫሮ ሞራታ እና ፔድሮ የማይሰለፉለት ይሆናል።

በዚህ ምክንያት እና በሜዳቸው እንደመጫወታቸው ብራይተኖች ከዚህ ጨዋታ ነጥብ ይዘው የሚወጡ ይመስላሉ።

የላውሮ ግምት፡ 1-1

Image copyright BBC Sport

አርሴናል ከ ክሪስታል ፓላስ

የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት አርሴናል ተጫዋች ለማስፈረም ስራ የሚበዛበት ይመስላል። ከሚወጡት ተጫዋቾች አንጻር እንማንንን እንደሚያስፈረም ወደፊት ይታያል።

ፓላሶች ባለፉት 12 ሊግ ቸዋታዎች አንድ ጊዜ ብቻ የተሸነፉ ሲሆን ይህም በአርሴናል ነው።

የላውሮ ግምት፡ 2-0

Image copyright BBC Sport

በርንሌይ ከ ማንቸስተር ዩናይትድ

አሌክሲ ሳንቼዝ ለማንቸስተር ዩናይትድ ከፈረመ ለዚህ ጨዋታ ሊደርስ እችላል።

ካልሆነም መፈረሙ ብቻውን ቡድኑን መንፈስ የሚያነቃቃ ነው።

በዚህ ሁሉ የዝውውር ወሬ ውስጥ ተጫዋቹ ችሎታ ጥያቄ ውስጥ አልገባም።

ዋናው ነገር ግን የገንዘብ ጉዳይ ነው።

የላውሮ ግምት፡ 0-2

Image copyright BBC Sport

ኤቨርተን ከ ዌስት ብሮም

የአጥቂ ችግራቸውን ለመቅረፍ ኤቨርተኖች ሴንክ ቶሱንና ቲዮ ዋልኮትን አስፈርመዋል።

ዌስትብሮሞች ከነሐሴ በኋላ በፕሪሚየር ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ማሸነፍ ችለዋል።

የላውሮ ግምት፡ 1-1

ሌስተር ከ ዋትፎርድ

ዋትፎርዶች በአስር ሊግ ጨዋታ ያሸነፉት ባለፈው ጥር 1-0 ከመመራት ሌስተርን ያሸነፉበት ጨዋታ ነው።

ቀሪዎቹ በሳምንቱ አጋማሽ የኤፍኤ ካፕ ጨዋታ ቢኖርባቸውም ጫና የሚያሳድርባቸው አይደለም።

የላውሮ ግምት፡ 2-0

ስቶክ ከ ሃደርስፊልድ

ስቶኮች ፖል ላምብርትን መቅጠር ቢችሉም የደጋፊዎቻቸውን ግን ፍላጎት ማሟላት አልቻሉም።

ጨዋታው ውጤት እያጣ ከሚገኘው ሃደርስፊልድ ጋር መሆኑ ለአሰልጣኙ ጥሩ ነው።

የላውሮ ግምት፡ 2-0

ዌስት ሃም ከ በርንማውዝ

ዌስትሃሞች በኤፍኤ ካፕ ከሽሪውቤሪ ጋር እስከመጨረሻው ታግለው ቢያሸንፉም በሊጉ ውጤታማ መሆን ጀምረዋል።

በርንማውዞች በበኩላቸው በኤፍኤ ካፕ ሽንፈትን አስተናግደዋል።

የላውሮ ግምት፡ 2-0

Image copyright BBC Sport

ማንቸስተር ሲቲ ከ ኒውካስትል

"ሊቨርፑል ፈጣን የማጥቃት እንቅስቀሴን ተጠቅሞ ማንቸስትር ሲቲን ያሸነፈበትን ጨዋታ ራፋ ቤኒቴዝ ይደግሙታል ብዬ አላስብም።"

"በሊቨርፑል የደረሰባቸው ሽንፈት የማንቸስተር ሲቲውን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላን ያስጨንቃል ብዬ አላስብም። ይህ ጨዋታም ወደ ማሸነፍ የሚመለሱበት ይሆናል" ይላል ላውሮ።

የላውሮ ግምት፡ 3-0

እሁድ

ሳውዝ ሃምፕተን ከ ቶተንሃም

እየተሻሻሉ የሚገኙት ቶተንሃሞች በማንቸስትር ሲቲ ከደረሰባቸው ሽንፈት በኋላ ማግኘት ከሚገባቸው 15 ነጥቦች 13ቱን መሰብሰብ ችለዋል።

ሳውዝሃምፐተኖች በበኩላቸው ባለፉት 10 ጨዋታዎች አንዱንም ማሸነፍ አልቻሉም።

የላውሮ ግምት፡ 0-2

Image copyright BBC Sport

ሰኞ

ስዋንሲ ከ ሊቨርፑል

ባለፈው ሳምንት ማንቸስትር ሲቲን ካሸነፉ በኋላ ሊቨርፑሎች ነጥብ መጣልን አይቀበሉትም።

ስዋንሲዎች ሊፈትኗቸው ይሞክራሉ። የሊቨርፑልን ያህል የአጥቂ አቅም ከሌላቸው ግን ውጤታማ አይሆኑም

የላውሮ ግምት፡ 0-2