ውሃው ለተለያዩ አገልግሎቶች ስለሚውል ኬሚካል ደግሞ ተመራጭ አይደለም

እምቦጭ አረም ለኢትዮጵያ አዲስ አይደለም። በ1965 ዓ.ም በቆቃ ሐይቅ ላይ ተከስቶ ነበር። ችግሩ በጣና ከተከሰተ በኋላ ግን የተለያዩ ችግሮች ተደቅነዋል። "ድሮ ከአንድ ታንኳ 80 አሳ ይያዝ ነበር። አሁን ግን ከ15 አሳ በላይ አይገኝም" ሲል በጀልባ ሥራ የሚተዳደረው አባይነህ ምናለ ያለውን ችግር ይገልጻል።