የፕሪሚየር ሊግ ግምቶች፡ የሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታዎች ግምት

Liverpool v Tottenham Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ ሊቨርፑል ከቶተንሃም

አዲስ የሚመስለው የአርሴናል አጥቂ መስመር በመጪው ቅዳሜ ከኤቨርተን ጋር በሚደረገው ጨዋታ የመጀመሪያ ተሳትፎ ያደርጋል። ግን የቀድሞ አጥቂያቸው መነጋገሪያ ይሆን ይሆን?

የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን "ቲዮ ዋልኮት ለአዲሱ ክለቡ ሁለት ጎሎችን ካስቆጠረ በኋላ ከቀድሞ ክለቡ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ በትኩረት ይመለከተዋል" ይላል።

ላውረንሰን ሳምንቱን መጨረሻ የፕሪሚር ሊግ ጨዋታዎች ግምት እንደሚከተለው አስቀምጧል።

ቅዳሜ

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ በርንሌይ ከማንቸስተር ሲቲ

በርንሌይ ከማንቸስተር ሲቲ

ባለፈው ረቡዕ በርንሌይዎች ባለቀ ሰዓት ከኒውካስትል ጋር አቻ መሆን ቢችሉም ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም።

ከማንቸስተር ጋር መከላከልን መሠረት ባደረገ አጨዋወት ነጥብ ለመጋራት ይሞክራሉ። ሆኖም የሊጉ መሪዎች ቡድኖችን ለማስከፈት የሚያስችላቸው ብዙ መንገዶች ስላሏቸው ይህ ለበርንሌይዎች ፈተና ይሆናል።

የላውሮ ግምት፡ 0 - 2

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ በርንማውዝ ከስቶክ

በርንማውዝ ከስቶክ

በርንማውዞች ባለፈው ረቡዕ ቼልሲን ከማሸነፋቸውም በላይ አጨዋወታቸው ጥሩ ነበር።

በማጥቃት ላይ የተመሠረተ አጨዋወት ከተከተሉ በርንማውዞች ነጥብ እንደሚያገኙ ሁሌም አምናለሁ።

የላውሮ ግምት፡ 1 - 1

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ ብራይተን ከዌስት ሃም

ብራይተን ከዌስት ሃም

ዌስትሃሞች ከፕሪስተን ያስፈረሙት አጥቂ ጆርዳን ሁጊል ምን አይነት ተጽዕኖ እንደሚኖረው ማየት ያጓጓል።

ከኢንተር ያስፈረሙት ጆአኦ ማሪኦም ጥሩ ተጫዋች ይመስላል። ሆኖም በጉዳት እየተቸገረ የሚገኘውን የዴቪድ ሞዬስን ሙሉ ቡድን ለማየት ጊዜ ይፈልጋል።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 1

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ ሌስተር ከስዋንሲ

ሌስተር ከስዋንሲ

ሪያድ ማህሬዝ ወደ ማንቸስተር ሲቲ ሊያደርገው የነበረው ዝውውር ባይሳካም ክረምት ላይ ሌስተርን የሚለቅ ይመስለኛል።

ስዋንሲዎች ባለፈው ማክሰኞ አርሴናልን ከማሸነፋቸውም በላይ አጨዋወታቸው ድንቅ ነበር።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 0

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ ማንቸስተር ዩናይትድ ከሃደርስፊልድ

ማንቸስተር ዩናይትድ ከሃደርስፊልድ

ባለፈው ሃደርስፊልዶች ማንቸስተር ዩናይትድን ሲያሸንፉ ጨዋታውን ተከታትዬው ነበር።

ማንቸስተሮች ባለፈው ረቡዕ ከቶተንሃም ጋር መጥፎ ውጤት ቢያስመዘግቡም ኦልድ ትራፎርድ ላይ የጆሴ ሞውሪንሆ ቡድን ያለፈውን ሽንፈት ለመቀልበስ እንደሚጫወት አምናለሁ።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 0

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ ዌስት ብሮም ከሳውዝሃምፕተን

ዌስት ብሮም ከሳውዝሃምፕተን

በውድድሩ መጀመሪያ ላይ ከነበረኝ ግምት በተቃራኒው እነዚህ ሁለት ቡድኖች በሊጉ ግርጌ ከሚገኙ ሶስት ቡድኖች ውስጥ ናቸው።

ዌስት ብሮሞች ይህን ጨዋታ ያሸንፋሉ ብዬ እገምታለሁ።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 1

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ አርሴናል ከኤቨርተን

አርሴናል ከኤቨርተን

አንድሬ ካንቼልስኪ ሃይብሪ ላይ ባለቀ ሰዓት ካስቆጠራት የ1996 ድል በኋላ ኤቨርተን አርሴናልን በሜዳው አሸንፎ አያውቅም።

ቶፊዎች በሳምንቱ አጋማሽ ሌስተሮችን ቢያሸንፉም አርሴናልን ግን ያሸንፋሉ ብዬ አልገምትም።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 0

እሁድ

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ ክሪስታል ፓላስ ከኒውካስትል

ክሪስታል ፓላስ ከኒውካስትል

ኒውካስትሎች በዝውውር መስኮቱ ኢስላም ስሊማኒን እና የክንፍ ተጫዋቹ ኬኔዲን ማስፈረም ችለዋል።

ፓላሶች ሳይቸገሩ የሚያሸንፉ ይመስለኛል።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 0

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ ሊቨርፑል ከቶተንሃም

ሊቨርፑል ከቶተንሃም

ሊቨርፑሎች በየትኛውም መንገድ ሃደርስፊልድን ማሸነፍ የሚጠብቁት ውጤት ነበር። ጎል ሳይቆጠርባቸው፤ የተከላካይ መስመሩ ስህተት ሳይፈጥር እና በቂ ዕድል በመፍጠር ማሸነፍም ችለዋል።

ስፐርሶች ደግሞ በጥሩ አቋም ላይ መሆናቸውን ከማንቸስተር ጋር በነበረው ጨዋታ አስመስክረዋል። በማንቸስተር ሲቲ ባለፈው ታህሳስ ሸንፈት ካስተናገዱ በኋላም አልተሸነፉም። ይህ አቋማቸው እንደሚቀጥል እጠብቃለሁ።

የላውሮ ግምት፡ 1 - 1

ሰኞ

Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ ዋትፎርድ ከቼልሲ

ዋትፎርድ ከቼልሲ

ቼልሲዎች በበርንማውዝ በተሸነፉበት ጨዋታ እጅግ ደካማ ነበሩ። አንቶኒዮ ኮንቴ ቡድኑን ከያዙት በኋላ እንዲህ አይነት አቋም አሳይተው አልተሸነፉም።

ዋትፎርዶች ሁለት ጨዋታ የሚሸነፉ ከሆነ ራሳቸውን በወራጅ ቀጠና ውስጥ ያገኛሉ። ወደ ላይ ለመውጣትም ሊከብዳቸው ይችላል። በዚህ ምክንያትም ሊጠነቀቁ ይገባል።

የላውሮ ግምት፡ 0 - 2

ተያያዥ ርዕሶች