የአፍሪካ የሳምንቱ ውሎ በፎቶዎች

በዚህ ሳምነት ከተለያዩ አፍሪካ አገራት የተገኙ ምርጥ ፎቶዎች

Pupils write on their notebook as they attend class at a primary school in Pikine, on the outskirts of Dakar, on January 30, 2018. Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ተማሪዋ በሴኔጋሏ መዲና ዳካር የአንደኛ ደረጃ ትምህርቷን በጥሞና እየተከታተለች ነው። አገሪቷ አለም አቀፍ የለጋሾችን ስብሰባ እያካሄደችም ነው። ይህ ስብሰባ በታዳጊ ሀገራት የተማሪዎችን ቁጥር ለመጨመር 'ቢሊዮን ዶላር' የተባለ እቅድ አካል ነው።
Kunle Tejuoso, owner of The Jazz Hole organizes bookshelves on January 30, 2018. The Jazz Hole is an independent record and book store in Lagos. Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ የፈረንሳይቷ ጋዜጠኛ የናይጀሪያዋን ደራሲ ቺማማንዳ አዲቼን በናይጀሪያ ውስጥ ቤተ-መፃህፍት አለ ወይ ብላ መጠየቋ ናይጀሪያዎችን አናዷል። በሌጎስ የሚገኘው የ'ጃዝ ሆል' መፃህፍት ቤትም እንዳለ ማሳያ ነው።
Opposition supporters demonstrate with a fake money with the face of presidential candidate Raila Odinga prior to his mock 'swearing-in' on January 30, 2018 at Uhuru Park in Nairobi, Kenya Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በዚህ ሳምንት ማክሰኞ በኬንያ የዋነኛው ተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ የህዝብ ፕሬዚዳንት ነኝ ሲል አውጇል። አንደኛው ደጋፊም ምርጫውን ቢያሸንፍ ኖሮ በገንዘቡ ላይ ያለው የፕሬዚዳንት ምስል እንዲህ ይቀየር ነበር በሚልም አሳይቷል።
Algerian doctors and dentists who are completing their residency stage of their studies stage a sit-in outside the Mustapha Bacha hospital in Algiers, on January 30, 2018, as part of a two-month-long strike protesting against compulsory civil service. Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በዚሁ ቀንም በአልጀሪያዋ መዲና አልጀርስ ሁለት ወር በቆየው አስገዳጅ አገልግሎት መስጠት ተቃውሞ ቀጥሏል።
India's Jyoti Amge (R), the world's shortest woman poses for a picture with Sultan Kosen of Turkey, the world's tallest man, at the site of the Pyramids of Giza in Egypt on January 26, 2018, with the Sphinx and the Pyramid of Khafre (also known as Chephren) seen in the background Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ከጥቂት ቀናት በፊት የአለም አጭሯ ህንዳዊዋ ጆይቲ እንዲሁም የአለም ረዥሙ ቱርካዊው ኮሰን በግብፅ ተገናኝተው እንዲህ ፎቶ ተነስተዋል።
A Tunisian child takes a selfie with French President Emmanuel Macron during a ceremony in memory of the victims of a deadly Islamic State group attack in 2015 at Tunis" Bardo Museum on February 1, 2018. Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ቱኒዝያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉትን የፈረንሳዩን ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ብዙዎች ፎቶ ሲነሱ ነበር።
Retired Jamaican Olympic and World champion sprinter Usain Bolt poses for a selfie with spectators as he arrives for the PUMA School of Speed Athletic event at the Ruimsig Stadium in Roodepoort, Johannesburg, on January 29, 2018 Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በተመሳሳይም በደቡብ አፍሪካዊቷ ከተማ ጆሃንስበርግ ሰኞ ብቅ ያለው ታዋቂው ጃማይካዊ ሯጭ ዩዜይን ቦልት ጋር ፎቶ ለመነሳት ብዙዎች ሲረባረቡ ነበር።
Morocco's Zakaria Hadraf (C) is tacked by Libya's Meftah Taqtaq (R) during the semi-final football match in the African Nations Championship between Morocco and Libya at the Mohammed V Casablanca Stadium on January 31, 2018 Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ የእግር ኳስ አፍቃሪ የሆነው ቦልት በዚህ ሳምንት ሞሮኮ ላይ እየተደረገ ያለውን የቻን ውድድር ላይ ባለመገኘቱ እንዳዘነ ጥርጥር የለውም። ፎቶው ላይ የሚታየው የሞሮኮው ተጫዋች ዛካሪያ ሀድራፍ በሊቢያው ተጫዋች ሲጠለፍ ነው።
A woman walks along a beach at sunset in Grand Bassam, Ivory Coast, 27 January 2018 Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ እሁድ እለት አይቮሪኮስት በሚገኘው የግራንድ ባሳም ፀጥ ረጭ ባለው ባህርዳርቻ እያመራች ያለችው ይህች ሴትዮ በጥሞና ነበር።
The moon rises over Kadam mountain in Nakapiripirit town, northeastern Uganda, on January 31, 2018, during the lunar phenomenon referred to as the "super blue blood moon" Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ እሮብ ዕለት የነበረችውን ደማቅ ጨረቃ አይታችኋት ይሆን? በሰሜናዊ ምስራቅ ኡጋንዳ አካባቢ በምትገኘው ናካፒሪፒሪት ከተማ በሚገኘው ካዳም ተራራ ደማቅ፣ ሰማያዊና ቀላ ያለች ጨረቃ ብዙዎችን አስደምማለች።

ምስሎቹ የተገኙት ከአጃንስ ፍራንስ ፕሬስና ከሮይተርስ ነው።

በቢቢሲ ዙሪያ