የሳምንቱ የጋሬት ክሩክስ ፕሪሚር ሊግ ቡድን

Jose Izquierdo Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ኢዝኩዌርዶ ከተሳተፈባቸው 5 ሊጎ ጎሎች አራቱ በሜዳቸው የተገኙ ናቸው

ፒየር-ኤመሪክ አውባመያንግ ለአርሴናል በተሰለፈበት የመጀመሪያ ጨዋታው ጎል አስቆጥሯል። ማንቸስተር ሲቲ በውድድር ዓመቱ ለአራተኛ ጊዜ ነጥብ ጥሏል። ቶተንሃም ከሊቨርፑል ጋር በነበረው ድራማ የተሞላበት ጨዋታ ሁለት ፍጹም ቅጣት ምቶችን አግኝቷል።

የቢቢሲው ስፖርት ጋዜጠኛ ጋሬት ክሩክስ የሳምንቱን ፕሪሚር ሊግ ምርጥ አስራ አንድ እንደሚከተለው አቅርቧል።

ግብ ጠባቂ - ኤደርሰን (ማንቸስተር ሲቲ)

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ በዘንድሮው ዓመት ከአምስት ጨዋታ በላይ ከተሰለፉ ግብ ጠባቂዎች ኤደርሰን ኳስ የማቀበል ችሎታው ከፍተኛ ነበር

ማንቸስተር ሲቲ ከበርንሌይ ጋር አቻ በወጣበት ጨዋታ የቤን ሚን ኳስ ያዳነበት መንገድ አስገራሚ ነበር።

ብራዚላዊው ግብ ጠባቂ ኳስ ይዞ ለሌሎች ተጫዋቾች ሲያቀብል ያለምንም ተጽዕኖ ነው።

ተከላካይ - ጃክ ስቴፈንስ (ሳውዝሃምፕተን)

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ጃክ ስቴፈንስ በእግር ኳስ ህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በተከታታይ ጨዋታዎች ጎሎችን አስቆጥሯል

በሳምንቱ አጋማሽ ጃክ ስቴፈንስ ምርጥ ኳስ ናት ብራይተን ላይ አስደናቂ ጎል ሆና የተቆጠረችው።

አልቢዮን ላይም ቢሆን ምርጥ ኳስ ከመረብ ለማሳረፍ ችሏል።

ተከላካይ - ቤን ሚ (በርንሌይ)

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ በዚህም ዓመት በሊጉ ቤን ሚ ከየትኛውም የበርንሌይ ተከላካይ በላይ ብዙ ኳሶችን ከጎል አካባቢ አርቋል

ቅዳሜ ዕለት የአሰልጣኛቸውን መልዕክት ለመተግበር ብዙ የበርንሌይ ተጫዋቾች ቢችሉም እንደ ቤን ሚ የተሳካለት የለም።

ተከላካዩ በራሱ ሜዳ ውጤታማ ከመሆኑም በላይ በማንቸስተር ሲቲ ሜዳም የቆሙ ኳሶች ላይ ስጋት ሲፈጥር ነበር።

ተከላካይ - ዳኒሎ (ማንቸስተር ሲቲ)

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ዳኒሎ በዘንድሮው ዓመት ሁለት ጎሎችን በሊጉ አስቆጥሯል

ዳኒሎ ብዙ የመስመር ተከላካይ መስመር ተጫዋቾች የማይጠቀሙበት ክፍተት ለማጥቃት ስራ ያውለዋል።

ይህንንም በመጠቀም የመታው ምርጥ ኳስ ኒክ ፖፕን አልፎ ከመረብ ላይ አርፏል።

አማካይ - ሄነሪክ ሚኪታሪያን (አርሴናል)

Image copyright PA
አጭር የምስል መግለጫ ሚኪታሪያን ለአርሴናል የፈጠራቸው ሶስት ዕድሎች ወደ ጎል ተቀይረዋል

ሚኪታሪያን ዶርትሙን፣ ማንቸስተር እንዲሁም አሁን በአርሴናል ከኤቨርተን ጋር በነበረው ጨዋታ ወድጄዋለሁ።

ከቡድን ጋር መዋሃድ ወራትን ቢፈልግም እሱ ግን ሰዓታት ብቻ በቅተውታል።

አማካይ - ማሪዮ ለሚና (ሳውዝሃምፕተን)

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ማሪዮ ለሚና በሊጉ መጀመሪያ ጎሉን ባለፈወ ቅዳሜ አስቆጥሯል

ይህ ተጫዋች መጫወት በሚገባው ቡድን ውስጥ እየተጫወተ አይደለም።

ምረጥ ብባል ማሪዮ ለሚና ለአርሴናል መጫወት ያለበት ተጫዋች ነው።

እንደኔ ከሆነ ቬንገር ከሳውዝሃምፕተን ቀድመው ለሚናን በክረምቱ ሊያስፈርሙ ይገባ ነበር።

አማካይ - አሮን ራምሴ (አርሴናል)

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ አሮን ራምሴ በሊጉ ሃትሪክ ሰራ 20ኛ ተጫዋች ሆኗል

ኤቨርተኖች ጥሩ ይሆናሉ ብዬ ብጠብቅም ይህ አልሆነም።

አሮን ራምሴም በደካማዎቹ ቶፊዎች ላይ ሃትሪክ ማስቆጠር ችሏል።

አማካይ - ፉሴኒ ዲያባቴ (ሌስተር)

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ዲያባቴ ለሌስተር ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል

ሌስተሮች አዲሱን ሪያድ ማህሬዝን አግኝተውታል።

ፉሴኒ ዲያባቴ ከፒተርብራ እና ስዋንሲ ጋር ያሳየው ብቃት ማህሬዝ ዋንጫ ባነሱበት ዓመት የነበረውን አቋም የሚመስል ነው።

አጥቂ - ሞሃመድ ሳላህ (ሊቨርፑል)

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሞሃመድ ሳላህ በ25 ሊጉ ጨዋታዎች 21 ጎሎችን ከመረብ አሳርፏል

ሊደነቁ የሚገባቸው ጎሎች አሉ። ሞሃመድ ሳላህ ቶተንሃም ላይ ያስቆጠራት ጎል ከእነዚህ መካከል ትመደባለች። በማራዶና ደረጃ ያለች ናት።

የመጀመሪያ ጎሉም ቢሆን ምርጥ ነበረች።

አጥቂ - ፒር-ኤመሪክ አውመያንግ (አርሴናል)

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ አውበመያንግ ከትልልቆቹ የአውሮፓ 5 ሊጎች በሜዳው 12 ጎሎችን አስቆጥሯል

ፒር-ኤመሪክ አውበመያንግ ኤቨርተን ላይ ያስቆጠራት ጎል ድንቅ ነበረች።

ሁለት አጥቂዎች በአንድ ቡድን ውስጥ አብረው እንደማይሰሩ በሚያምኑት የቬንገር ቡድን ውስጥ አልክሳንደር ላካዜት ተጠባባቂ መሆኑ እውን ነው።

አጥቂ - ጆሴ ኢዝኩዌርዶ (ብራይተን)

የጎል ማማር አሸናፊ ቢያደርግ ኖሮ ከዌስት ሃም ጋር በነበረው ጨዋታ ጆሴ ኢዝኩዌርዶ ያስቆጠራት አንዷ ትሆን ነበር።

ለማሸነፍ ግን ጎል ማስቆጠር እና ጎል አለማስተናገድ ያስፈልጋል።

ብራይተን ደረጃወን አሻሽሎ በሊጉ ይቆያል ብየ አስባለሁ።

ተያያዥ ርዕሶች