ታሚል ናዱ፡ በታዳሽ ሃይል ቀዳሚ መሆን የቻለችው የህንዷ ግዛት

የፎቶው ባለመብት, Alamy
ታሚል ናዱ ከንፋስ የምታገኘውን የሃይል መጠን በእጥፍ ልታሳድግ ነው
በደቡባዊ ህንድ የምትገኘው ታሚል ናዱ ግዛት በንፋስ ሃይል ከዓለም ቀዳሚ ልትሆን እንደሆነ አንድ ሪፖርት ይፋ አደረገ።
መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው የኢነርጂ፣ የኢኮኖሚክስ እና ፋይናንስ ጥናት ኢንስትቲትዩት ግምት ከሆነ በአውሮፓዊያኑ 2027 ከግማሽ በላይ የሚሆነው የግዛቲቱ አካል በዋነኝነት ከፀሐይ እና ከንፋስ ሃይል ያገኛል።
ግዛቲቱ በአሁኑ ወቅት ከንፋስ ሃይል ብቻ የምታመርተው የሃይል መጠን 7.85 ጊጋ ዋት ሲሆን ይህም ከስዊድን ወይንም ከዴንማርክ የሚበልጥ ነው።
ይህ አሃዝ በቀጣዮቹ አስር ዓመታት በእጥፍ የሚያድግ ሲሆን ከፀሐይ የሚገኝ ሃይል ደግሞ በስድስት እጥፍ አድጎ 13.5 ጊጋ ዋት ይደርሳል።
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ህንድ ከዓለማችን ቀዳሚ የድንጋይ ከሰል አምራቾች አንዷ ናት
ይህ ከተሳካ ደግሞ ታሚል ናዱ ከምታመርተው ሃይል 67 በመቶ የሚሆነው ከታዳሽ ሃይል ይሆናል። ይህን ለማድረግ ግን ግዛቲቱ የሃይል ዘርፉን ልታዘምን ይገባል።
የታሚል ናዱ ግዛት ህዝብ ብዛት ከአውስትራሊያ በሶስት እጥፍ የሚበልጥ ሲሆን ግዛቲቱ ኢኮኖሚም ከሲሪላንካ እና ዩክሬይን ጋር የሚስተካከል ነው። ይህም የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ ካርቦን ልቀትን መቀነስ እንደሚቻል ማሳያ ነው።
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ወደ 300 ሚሊዮን የሚጠጉ ህንዳዊያን አሁንም ኤሌክትሪክ አያገኙም
አብዛኛው የግዛቲቱ ዕድገት በታዳሽ ሐይል ላይ መሰረት ያደረገ ነው። ከፀሐይ እና ከንፋስ ሃይል ለማግኘት የሚያስፈልገው ወጪ እቀነሰ መጥቶ አካባቢን ከሚጎዱት እና እንደ ድንጋይ ከሰል ካሉት ሃይል ምንጮች ጋር እየተቀራረበ ነው።
የድንጋይ ከሰል ሃይል ለማመንጨት የሚያስፈልገው ዋጋ ከፀሐይ ወይም ከንፋስ በሁለት እጥፍ ይበልጣል። ምንም እንኳን በገንዘቡ በኩል ጥሩ ባይሆንም ታሚል ናዱ በአሁኑ ወቅት 22.5 ጌጋ ዋት ሃይል ከድንጋይ ከሰል ታመርታለች።
የፎቶው ባለመብት, Alamy
ከድንጋይ ከሰል ሃይል ለማምረት የሚያስፈልገው ዋጋ ከንፋስ ለማምረት ከሚያስፈልገው በሁለት እጥፍ ይበልጣል
ሌሎች እክሎችም ግን አሉ። ከንፋስ ሃይል ማመንጨት የሚቻለው ከግንቦት እስከ ጥቅምት ባለው ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜም የሚገኘው ሃይል ከፍተኛ አይደለም።
ምክንያቱም ትርፍ የሆነውን ሃይል ወደ ሌላ በቦታ ለመላክ የሚያስችል መሠረተ ልማት ባለመኖሩ ከሌሎች የሃይል አማራጮች የሚመረተውን ሃይል መጠን ይቀንሳሉ።
ይህ ማለት ደግሞ ግዛቲቱ ሃይል በሚያንሳት ወቅት ከሌሎች ቦታዎችም በርካሽ ማግኘት አትችልም ማለት ነው።