የክረምት ኦሎምፒክ፡ በፒዮንግቻንግ 2018 የሚወዳደሩ አፍሪካዊያን እነማን ናቸው?

Nigeria's women's bobsleigh and skeleton team members Seun Adigun, Ngozi Onwumere, Akuoma Omeoga and Simidele Adeagbo attend a welcoming ceremony for the team in the Olympic Village in Pyeongchang

የፎቶው ባለመብት, Loic Venance/AFP

የምስሉ መግለጫ,

በክረምት ኦሎምፒክ ናይረጄሪያን የሚወክሉ ተወዳዳሪዎች

አርብ የካቲት 2 በሚጀምረውና በደቡብ ኮሪያዋ ከተማ ፒዮንግቻንግ በሚካሄደው የ2018 የክረምት ኦሎምፒክ ስምንት የአፍሪካ ሃገራት ተሳታፊ ይሆናሉ።

የአፍሪካ አህጉር ሞቃታማ ከመሆኗ የተነሳ የክረምት ኦሎምፒክ ውስጥ እንደሚካተቱት የበረዶ ሸርተቴ አይነት ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የአየር ንብረት የላትም።

ምንም እንኳን ይህ እንቅፋት ቢሆንም ስምንቱ ሀገራት ናይጄሪያ፣ ኤርትራ፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ማዳጋስካር፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሞሮኮ እና ቶጎ በፒዮንግቻንግ ውድድር ላይ ተወካይ ይኖራቸዋል።

እንደ ናይጄሪያ እና ኤርትራ ያሉ ሃገራት በውድድሩ ላይ ሲካፈሉ የመጀመሪያቸው በመሆን ታሪክ ይሰራሉ።

በፒዮንግቻንግ የክረምት ኦሎምፒክ ላይ የሚሳተፉ አፍሪካዊያንን እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል።

  • አክዋሲ ፍሪምፖንግ

    • እድሜ: 31
    • ሃገር: ጋና
    • ስፖርት: ስኬለተን (የበረዶ ሸርቴ ስፖርት አይነት)

    እውነታ፡ አክዋሲ ፍሪምፖንግ የጋናን ቦብስሌድ እና ስኬለተን ፌደሬሽንን በአውሮፓውያኑ በ2016 አቋቋመ።  

    ፍሪምፖንግ የአጭር ርቀት ሯጭ የነበረ ቢሆንም በጉዳት ምክንያት ፊቱን ወደ ሌላ ስፖርት አዙሯል።  

    በጣም ጠንካራ ተወዳዳሪ ለመሆን እና ስፖርቱን ለማወቅ ከአራት እስከ ስድስት ዓመት ሊፈጅ ይችላል። ምክንያቱም በጣም ፈጣን ስለሆነ አዕምሮህም ለመረዳት ሊከብደው ይችላል
  • ሳብሪና ሲማደር

    • እድሜ: 19
    • ሃገር: ኬንያ 
    • ስፖርት: የአልፓይን በረዶ ሸርተቴ 

    ሶስት ዓመት ሲሆናት ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ አውስትራሊያ ያቀናችው ሲማደር በአልፓይን የበረዶ ሸርተቴ ኬንያን በክረምት ኦሎምፒክ ላይ በመወከል የመጀመሪያዋ ናት።  

    የአልፓይን የበረዶ ሸርተቴ ተወዳዳሪ የሆነችውም በአውሮፓውያኑ 2013 ነው። ከዚህ ውደድር ሶስት ዓመታት በኋላም የምስራቅ አፍሪካ ሃገራትን በመወከል በኖርዌይ  

    በበረዶ ሸርተቴ ላይ ያለው ስሜት ፈጣን በመሆኑ የማበድ አይነት ስሜት ሊሰማህ ይችላል። ነጻ የመሆን ስሜት አለው ጊዜው ያንተ እንደሆነ የሚያሳይ ስሜትን ይፈጥራል። 
  • ሚያሊቲያና ክለርክ

    • እድሜ: 16
    • ሃገር: ማዳጋስካር
    • ስፖርት: የአልፓይን በረዶ ሸርተቴ 

    ሚያሊቲያና ክለርክ ከአልፓይን የበረዶ ሸርተቴ ጋር የተዋወቀችው የሶስት ዓመት ልጅ ሆና ፈረንሳይ ውስጥ ነው። ከወራት በፊት 16 ዓመት የሞላት ሲሆን ይህም በኦሎምፒኩ በዕድሜ ትንሽ ከሆኑ ተወዳዳሪዎች መካካል አንዷ ያደርጋታል።  

  • ሳሚር አዚማኒ

    • እድሜ: 40
    • ሃገር: ሞሮኮ
    • ስፖርት: ሃገር አቋራጭ የበረዶ ሸርተቴ 

    ሳሚር አዚማኒ የሃገር አቋራጭ የበረዶ ሸርተቴ መወዳደር ከመጀመሩ በፊት የአልፓይን የበረዶ ሸርተቴ ተወዳዳሪ ነበር። 

  • አዳም ላምሃሜዲ

    • እድሜ: 22
    • ሃገር: ሞሮኮ
    • ስፖርት: የአልፓይን በረዶ ሸርተቴ 

    ሞሮኮ ካናዳዊው አዳም ላምሃሜዲ በኦስትሪያው የወጣቶች የክረምት ኦሎምፒክ ላይ ሲያሸንፍ በውድድሩ ወርቅ ያገኘ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ለመሆን ችሏል።  

  • ሞሪያም ሴዩን አዲጉን

    • እድሜ: 31
    • ሃገር: ናይጄሪያ
    • ስፖርት: ቦብስሌይ (የበረዶ ሸርተቴ የስፖርት አይነት)

    ሴዩን አዲጉን የመጀመሪያውን የናይጄሪያ የቦብስሌይ ቡድንን አቋቁማለች። የቡድኑም መሪ ናት። 

    የቀድሞዋ አትሌት በአውሮፓውያኑ 2012 በለንደን የበጋ ኦሎምፒክ ላይ በ100 ሜትር መሰናክል ተሳትፋለች። 

    እውነት አይመስልም። ናይጄሪያ በክረምት ኦሎምፒክ ላይ ተሳታፊ አልነበራትም። ይህን በማየታቸውም ደስተኞች ናቸው።
  • አኩማ ኦሜጋ 

    • እድሜ: 25
    • ሃገር: ናይጄሪያ
    • ስፖርት: ቦብስሌይ (የበረዶ ሸርተቴ የስፖርት አይነት)

    አኩማ የመጀመሪያው የናይጄሪያ የቦብስሌይ ስፖርት ቡድን አባል ናት። 

    የጤና ባለሙያዎችንም የመቅጠር ኃላፊነቱም የእሷ ነው። 

  • ንጎዚ ኦንዉሜሬ

    • እድሜ: 26
    • ሃገር: ናይጄሪያ
    • ስፖርት: ቦብስሌይ (የበረዶ ሸርተቴ የስፖርት አይነት)

    ንጎዚ ኦንዉሜሬ ቀደም ሲል ሯጭ የነበረች ሲሆን ናይጄሪያን በአውሮፓውያኑ 2015ቱ የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ ወክላለች። 

  • ሲሚዴሌ አዲያግቦ

    • እድሜ: 36
    • ሃገር: ናይጄሪያ
    • ስፖርት: ስኬለተን

    ለዘጠኝ ዓመታት ከስፖርታዊ ውድድሮች ርቃ የቆየችው ሲሚዴሌ አዲያግቦ በናይጄሪያ የቦብስሌይ ስፖርት ቡድን ተነሳስታ የስኬለተን ተወዳዳሪ ለመሆን በቃች።  

    አዲያግቦ በዚህ ስፖርት በክረምት ኦሎምፒክ የተሳተፈች የመጀመሪያዋ ናይጄሪያዊት ናት።  

  • ኮኖር ዊልሰን

    • እድሜ: 21
    • ሃገር: ደቡብ አፍሪካ 
    • ስፖርት: የአልፓይን በረዶ ሸርተቴ 

    ኮኖር ዊልሰን በአሜሪካው ቬርሞንት ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና ትምህርቱን ተከታትሏል።  

  • ማቲልድ-አሚቪ ፔቲዥየ

    • እድሜ: 23
    • ሃገር: ቶጎ
    • ስፖርት: ሃገር አቋራጭ የበረዶ ሸርተቴ 

    ማትሊድ-አሚቪ ፔቲዥየ ቀደም ሲል ፈረንሳይ አገር አቋራጭ በረዶ ሸርተቴ ታዳጊ ቡድን አባል ነበረች። በኋላ ላይ ግን የተወለደችበት ሃገር ቶጎን ወክላለች።  

  • አሌሲያ አፊ ዲፖል

    • እድሜ: 22
    • ሃገር: ቶጎ
    • ስፖርት: የአልፓይን በረዶ ሸርተቴ 

    ምንም እንኳን ከቶጎ ጋር ትስስር ባይኖራትም በጣሊያን ተወልዳ ያደገችው አሌሲያ አፊ ዲፖል የምዕራብ አፍሪካዋን ሃገር መወከልን መርጣለች። 

    ተወዳዳሪዋ ለመጀመሪያ ጊዜ ቶጎን ወክላ የተወዳደረችው በአውሮፓዊያኑ 2014 በሶሺ የክረምት ኦሎምፒክ ነው። 

  • ሻኖን-ኦግባኒ አቤዳ

    • እድሜ: 21
    • ሃገር: ኤርትራ
    • ስፖርት: የአልፓይን በረዶ ሸርተቴ 

    አቤዳ በካናዳ ያደገ ሲሆን የበረዶ ሆኪ (የገና) ጨዋታ ተጫዋች ለመሆን ፍላጎት ቢኖረውም በረዶ ሸርተቴ ለእሱ ጥሩ ስፖርት መሆኑን ወላጆቹም ስላሰቡም ነው ስፖርቱን የተቀላቀለው። 

    ኤርትራን በክረምት ኦሎምፒክ በመወከልም የመጀመሪያው ኤርትራዊ ነው።  

    እንደእኔ ላሉ ኤርትራዊያን የበረዶ ሸርተቴ ተወዳዳሪ መሆን የተለመደ ባይሆንም ኤርትራዊያን ጀግና ህዝቦች ናቸው። አንድ ሰው ሲወዳደር ወይም በጥሩ ጎኑ ኤርትራን ሲወክል ካዩ ደስተኞች ይሆናሉ።

የፎቶ ባለቤት:

Matthias Hangst/Getty Images, Dimitar Dilkoff/AFP/Getty Images, Francois Xavier Marit/AFP/Getty Images, Shaun Botterill/Getty Images, Christophe Pallot/Agence Zoom/Getty Images, Alexander Hassenstein/Getty Images, ALEXANDER KLEIN/AFP/Getty Images, Dean Mouhtaropoulos/Getty Images, Courtney Hoffos