የጋሬት ክሩክስ የሳምንቱ ምርጥ ቡድን

ማንቸስተር ሲቲዎች ሌስተርን ሲያሸንፉ ሰርጂዮ አጉዌሮ አራት ጎሎችን አስቆጥሯል።

ኒውካስትል በአስገራሚ ሁኔታ ማንቸስተር ዩናይትድ በማሰነፍ ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት ችሏል።

በሳምንቱ ሊጉ ጨዋታዎች እነማን በሳምንቱ ምርጥ ቡድኑ ውስጥ ሊገቡ ይገባቸዋል? ጋሬት ክሩክስ የፕሪሚር ሊጉን ምርት ቡድን እንደሚከተለው መርጧል።

ግብ ጠባቂ - ማት ሪያን (ብራይተን)

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ማት ሪያን ከስቶክ ጋር በነበረው ጨዋታ አንድ ፍጹም ቅታት ምት አድኗል

ማት ሪያን ድንቅ በሆነ መልኩ ፍፁም ቅጣት ምት አድኗል።

ቻርሊ አዳም ምርጥ ኳስ ቢመታም የብራይተኑ ግብ ጠባቂ ጠንካራ እጆች ቡድኑ ከስቶክ ጋር ነጥብ እንዲጋራ አስችሎታል።

ተከላካይ - ፓብሎ ዛባሌታ

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ዛባሌታ ቡድኑ ዌስትሃም ዋትፎርድ ባሸነፈበት ጨዋታ ብዙ ተሳኩ ኳሶችን ከቡድን አጋሮቹ በላይ አቀብሏል

ዛባሌታ ከማንቸስተር ሲቲ ቢለቅም አሁንም ድንቅ አቋሙን አብሮት ነው።

አርጀንቲናዊው ከዋትፎርድ ጋር በነበረው ጨዋታ ጠንካራ ሆኖ ነው ያመሸው።

ተከላካይ - ቨረጂል ቫን ዲይክ (ሊቨርፑል)

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ቫን ዲይክ ቡድኑ ከሳውዝሃምፕተን ጋር በነበረው ጨዋታ ከቡድን አጋሮቹ በበለጠ ብዙ ኳሶችን አድኗል

ቀላል ባይሆንም ቨረጂል ቫን ዲይክ በሊቨርፑል ቤት ውጤታማ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለኝም።

ወደ ቀድሞ ክለቡ ሳውዝሃምፕተን ተመልሶ ይህን የመሰለ ብቃቱን ማሳየቱ ምን ያህል አዕምሮ ጥንካሬ እንዳለው ያሳያል።

ተከላካይ - ያን ቬርቶገን (ቶተንሃም)

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ቬርቶገን ዘጠኝ ኳሶችን ከአርሴናል ጋር አድኗል

ከአጣማሪው ቶቢ አልደዊርድ ጋር ለረዥም ጊዜ ባይጫወትም ያን ቬርቶገን ከአርሴናል ጋር ያለእሱም ጠንካራ ሆኖ አምሽቷል።

አልደዊርድን ሳይጨምር ከሁሉም የቶተንሃም ተከላካዮች ዘንድሮ ወጥ አቋም ያሳየው ቬርቶገን ነው።

አማካይ - ጆሴ ኢዝኩዌርዶ (ብራይተን)

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ካለፉት ሰባት ብራይተን ጎሎች ኢዝኩዌርዶ በአራቱ ላይ ቀጥታ ተሳትፎ ነበረው

ኢዝኩዌርዶ ከስቶክ ጋር በነበረው ጨዋታ ጎል አስቆጥሯል።

አሁን አሁን ከሊጉ ህይወት ጋር እየተላመደ የሚመስል ሲሆን ለዚህም የሚመጥን ችሎታ ባለቤት ነው።

አማካይ - ጊልፍ ሲጉርድሰን (ኤቨርተን)

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሲጉርድሰን ከክሪስታል ፓላስ ጋር ባደረጋቸው ያለፉት ስድስት ጨዋታዎች በሰባት ጎሎች ላይ ተሳትፏል

ጊልፍ ሲጉርድሰን ከአርሴናል ጋር በነበረው ጨዋታ ባይሰለፍም ከዋይኒ ሩኒ ጋር በመሆን ፓላሶች ላይ እንዲያሸንፉ አግዟል።

ዘንድሮ ኤቨርተኖች ከሜዳቸው ውጭ ጥሩ ባለመሆናቸው አላርዳይስ ጉዲሰን ፓርክ ጠንካራ ቤታቸው መሆኑን ጠቁመዋል።

አማካይ - ኬቪን ደ ብሩይን (አማካይ)

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ደ ብሩይን በሊጉ በአንድ ጨዋታ ሶስት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል ሶስተኛው ማንቸስተር ሲቲ ተቻዋች ለመሆን ቅቷል

ኬቪን ደ ብሩይን ከሌስተር ጋር በነበረው ጨዋታ ሶስት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ማቀበሉ ሁሉንም ታሪክ አይገልጽም።

ሁሉም ትውልድ በአንድ ድንቅ አማካይ የታደለ ነው። ማንቸስተር ሲቲ ሊጉን ዋንጫ በአንድ እጁ ከወዲሁ ለመያዙ ደ ብሩይን አንድ ምክንያት ነው።

አማካይ - ማርኮ አርናቶቪች (ዌስት ሃም)

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ባለፉት ዘጠኝ ሊጉ ጨዋታዎች አርናቶቪች በአስር ጎሎች ላይ ተጽዕኖ ነበረው

ሁሉም ተጫዋቾች መወደደን የሚፈልጉ ሲሆን ማርኮ አርናቶቪችም ከዚህ የተለየ አይደለም።

ደጋፊዎች ግን የአርናቶቪችን የሚወዱት አይመስልም ምክንያቱም ብቃቱ የሌሎች ክቦች ትኩረት ሊያደርገው ስለሚቸል ነው።

አጥቂ - ሃሪ ኬን (ቶተንሃም)

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ አርሴናል ላይ በተከታታይ አራት ጨዋታዎች ጎሎችን በማስቆጠር ኬን ሁለተኛ ተጫዋች ነው

ሃሪ ኬን አርሴናል ላይ ማሸነፊያዋን ጎል በጭንቅላቱ ያስቆጠረበት መንገድ ድንቅ መሆኑ አያጠራጥርም።

በጠባብ ቦታዎች ላይ ኳስ በመያዝ የቡድኑ ተጫዋቾችን ወደ ጨዋታ የማስገባት ችሎታውም ግሩም ነው።

አጥቂ - ሰርጂኦ አጉዌሮ (ማንቸስተር ሲቲ)

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ አጉዌሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትሃድ በተካሄዱ ሰባት ተከታታይ ጨዋታዎች ጎል ማስቆጠር ችሏል

ይህ ተጫዋች የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ ካልተመረጠ በሂደቱ ላይ በጣም ችግር አለ ማለት ነው።

ደ ብሩይን፣ ሞሃመድ ሳላህና ሃሪ ኬን ቢፎካከሩትም ሁሉም ግን ባለፉት አምስት ዓመታት ወጥ አቋም አላሳዩም።

አጥቂ - ሞሃመድ ሳላህ (ሊቨርፑል)

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሳላህ በዘንድሮው ዓመት በ29 ጎሎች ላይ ተሳትፎ አድርጓል

በዚህ ወቀት ሞሃመድ ሳላህን የሚያቆም የለም። ከሳውዝሃምፕተን ጋር ከእረፍት በፊት ብቻ ለጎል የሚሆን ኳስ አቀብሎ ጎል ማስቆጠርም ችሏል።

ሳላህ ድንቅ ስራ በሰሩት በነኬኒ ዳግሊሽ፣ ኬቪን ኪጋን እና ጆን ባርነስ ተርታ የሚሰለፍ ነው።