የ2018 ኩምላ ዱሞር ሽልማት፡ ቀጣዩን የፍሪካ ኮከብ ጋዜጠኛ ፍለጋ

Komla Dumor

ቢቢሲ የአፍሪካን ኮከብ ጋዜጠኛ የሚፈልግበት የ2018 የቢቢሲ ዎርልድ ኒውስ ኮምላ ዱሞር ሽልማት ዘንድሮ አራት ዓመት ሞላው።

ከአፍሪካ አዲስ ችሎታ በሚፈልገው እና በሚያበረታታው የሽልማት ውድድር ላይ በአህጉሪቱ የሚገኙ ጋዜጠኖች እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

አሸናፊ የሚሆነው/ምትሆነው ለንደን በሚገኘው ቢቢሲ ዋና መስሪያ ቤት ዕውቀት እና ልምድ እንድታገኝ/እንዲያገኝ ይደረጋል።

ምዝገባው ከዛሬ ጀምሮ ክፍት ይሆናል።

ሽልማቱ በ41 ዓመቱ በድንገት ህእወቱ ያለፈውን ጋናዊውን የቢቢሲ ጋዜጠኛ ኮምላ ዱሞርን ለመዘከር የተጀመረ ነው።

ዘንድሮው ውድድር የሚጀምረው ከጋና ዋና ከተማ አክራ ይሆናል።ሽልማቱ ምርጥ ስራ ላበረከቱ በአፍሪካ ለሚኖሩ እና ለሚሰሩ ጋዜጠኞች የሚሰጥ ነው። ጠንካራ ጋዜጠኝነት ችሎታ፣ በስርጭት ወቅት ጥሩ መሆንና ምርጥ በሆነ መንገድ የአፍሪካን ታሪክ መግለጽን ከመጠየቁም በላይ ለወደፊቱ ተንካራ ጋዜጠኛ ለመሆን ህልምና አቅም ያላቸው ሊሆኑ ይገባል። ።

በለንድን ከቢቢሲ ጋር ከሚኖር ቆይታ በተጨማሪ አሸናፊው/ዋ በአፍሪካ በመዘዋወር እንዲሰራ/እንድትሰራ በማድረግ ስራው በአህጉሪቱም ሆነ በመላው ዓለም እንዲሰራጭ ይደረጋል።

አጭር የምስል መግለጫ የ2017ቷ አሸናፊ አሚና ዩጉዳ በቢቢሲ ቆይታዋ ስለ አካባቢ ጉዳኦች ስትዘግብ ቆይታለች

የውድድሩ ቀደምት አሸናፊዎች ናንሲ ካኩንጊራ ከኡጋንዳ እና ሁለቱ ናይጄሪያዊያን ዲዲ አኪንዬሉር እና አሚና ዩጉዳ ይገኙበታል።

አሚና ለዋና ሪፖርትዋ ሳይንቲስቶች ሊጠፋ ይችላል ስላሉለት በአፍሪካ ትልቅ ስለሆነው ቪክቶሪያ ሃይቅ ስጋቶች ከዩጋንዳ ዘግባለች።

"የ2017 የቢቢሲ ዎርልድ ኒውስ ኮምላ ዱሞር ሽልማት አሸናፊ መሆን አንደ አዲስ ስራዬን እንዲሰማኝ አድርጓል። ዓለም አቀፍ መድረክ ማግኘት፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ መታወቅ እንደአዲስ ስራ እንደጀመርኩ እንዲሰማኝ አድርጓል" ብላለች አሚና።

"በስልጠና ወቅት የእውነታን፣ ሚዛናዊነትንና እና አለማዳላትን ጥቅም ተረድቻለሁ። ከዚህ በተጨማሪ አፍሪካ ታሪኮችን እንዴት ለዓለም ማቅረብ እንደሚቻል ተገንዝቤያለሁ።

"ኩምላ አህጉሪቱን በዓለም ደረጃ ያቀረበበት መንገድ ያኮራናል። እህም እንዲቀጥል ማገዝ በመቻሌ ኩራት ይሰማኛል።"

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
የ2018 ኩምላ ዱሞር ሽልማት፡ ቀጣዩን የአፍሪካ ኮከብ ጋዜጠኛ ፍለጋ

አሚና በ2018ቱ መከፈቻ ስነስርዓት ላይ ከቢቢሲ ዎርልድ ሰርቪስ ግሩፕ ዳይሬክተር ጀሚ አንገስ ጋር ትገኛለች።

ከመክፈቻው በፊትም እንዲህ ብሏል፡

"የኮምላ ሃገር በሆነችው በጋና ከዘመዶቹ እና ጓደኞቹ ጋር ስራውን በመዘከር ቀጣዩን ኮከብ ጋዜጠኛ ለማግነት በሚደረገው ስነስርዓት ላይ መገኘቴ ለኔ ክብር ነው።

"ናንሲ፣ ዲደ እና አሚና የቀደሙ ሶስት አሸናፊዎች ናቸው። አህጉሩን በጥልቀት በመረዳት እና ኬአካባቢው ታዳሚ ጋር እንዴት ጋር ያለወ ግንኑንት እንዴት እንደሚጠናከር በማሳት ችሎታ እንዳላቸውም አሳይተዋል።

" ሌላ ባለተሰጽኦ ጋዜጠኛ ከአህጉሩ እየፈለግን ነው። እንኳን የ2018 የቢቢሲ ዎርልድ ኒውስ ኮምላ ዱሞር ሽልማት አሰናፊ ሆናችሁ ለማለትም ተዘጋጅተናል።"