የላውሮ የፕሪሚየር ሊግ እና ካራባኦ ዋንጫ ግምት

Arsenal v Man City Image copyright BBC Sport

ማንቸስተር ሲቲዎች አራት ዋንጫ ለማንሳት ያላቸው ተስፋ በኤፍ ኤ ካፕ በዊጋን ተሸንፈው ከወጡ በኋላ ህልም ሆኗል። የጋርዲዮላ ቡድን ካራባኦ ዋንጫን ማንሳት ይችላሉ?

የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን "ማንቸስተር ሲቲ በዊጋን መሸነፉን ሲያዩ አርሰን ቬንገር 'እንደዚህ ነው' ማለታቸው አይቀርም" ይላል።

ሳምንቱን እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግና እና ካራባኦ ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ ግምት እንደሚከተለው አቅርበናል።

ቅዳሜ

Image copyright BBC Sport

ሌስተር ከስቶክ

ስቶኮች ዘንድሮ ከሜዳቸው ውጭ መጥፎ ውጤት ነው ያላቸው። ከ13 ጨዋታዎች አንድ ሲያሸንፉ ሶስት አቻ ወጥተው በሌሎቹ ተሸንፈዋል።

ሪኣድ ማህሬዝ ለሌስተሮች ተመልሶ ሼፍልድን ኤፍ ኤ ካፑ ላይ እንዲያሸንፉ አግዟል። ቅዳሜም ይሳካላቸዋል ብየ አስባለሁ።

የላውሮ ግምት፡ 2-0

Image copyright BBC Sport

በርንማውዝ ከኒውካስትል

በርንማውዞች አንዳንድ ጥሩ ውጤቶችን ቢያስመዘግቡም በሃደርስፊልድ የተሸነፉበት ኣይነት መጥፎ ጨዋታም አሳይተዋል።

ኒውካስትሎች ደግሞ ማንቸስተር ዩናይትድን በማሸነፍ ሊጉ ምን ዓይነት የተለየ መሆኑን አሳይተዋል።

የላውሮ ግምት፡ 1-1

Image copyright BBC Sport

ብራይተን ከስዋንሲ

ብራይተኖቨች ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ጥሩ ውጤት ቢያስመዘግቡም ይህን ማስቀጠል ይኖርባቸዋል።

ስዋንሲዎች ይሸነፋሉ ስል ከደጋፊዎቻቸው መጥፎ ነገር ቢደርስብኝም ሊያመሰግኑን ይገባል። ምክንያቱም እንደዛ ስል ሁሌም ስዋንሲዎች ያሸንፋሉ። አሁን ግን ለስዋንሲ ደጋፊዎች መጥፎው ዜና አቻ ይወጣሉ ማለቴ ነው።

የላውሮ ግምት፡ 1-1

Image copyright BBC Sport

በርንሌይ ከሳውዝሃምፕተን

ሳውዝሃምፕተኖች በሊቨርፑል ከደረሰባቸው ሽንፈት ውጭ ውጤታማ መሆን እየቻሉ ነው።

በተቃራኒው ደግሞ በበርንሌይዎች ማሸነፍ የቻሉት ከአስራ አንድ ጨዋታ በፊት ከስቶክ ጋር በነበራቸው ጨዋታ ነው።

የላውሮ ግምት፡ 2-1

Image copyright BBC Sport

ሊቨርፑል ከዌስትሃም

ሁለቱም ቡድኖች ያለፈውን ሳምንት ጨዋታ ያልነበራቸው ሲሆን ሊቨርፑሎች ወደ ማርቤላ አቅንተው ነበር።

ቀያዮቹ ዘንድሮ በሜዳቸው አንፊልድ ያልተሸነፉ ሲሆን በሜዳቸው ማጥቃት ብቃታቸውም የታወቀ ነው።

የላውሮ ግምት፡ 3-0

Image copyright BBC Sport

ዌስት ብሮም ከሃደርስፊልድ

ዌስት ብሮምዎች ያሉበት ደረጃ ከቡድኑ ምላሽ የሚሰጥበት ነው። ድሉን በደንብ ይፈልጉታል።

ሃደርስፊልዶች ባለፈው በርንማውዝ ላይ ትልቅ ድል ቢያስመዘግቡም ከሜዳቸው ውጭ ግን ጥሩ ውጤት እያስመዘገቡ አይደለም።

የላውሮ ግምት፡ 2-0

Image copyright BBC Sport

ዋትፎርድ ከኤቨርተን

የሊጉን ግርጌ ስመለከት የዋትፎርዶች ጉዳይ ያሳስበኛል።

ኤቨርተኖችም ስኬታማ ጉዞ ላይ ባይሆኑም ባለፈው ሳምንት ፓላስን አሸንፈው ድል አስመዝግበዋል። በዚህኛውም ይሸነፋሉ ብዬ አላስብም።

የላውሮ ግምት፡ 1-1

እሁድ

Image copyright BBC Sport

ክሪስታል ፓላስ ከቶተንሃም

ክሪስታል ፓላሶች ካለፉት አራት ጨዋታዎች ሁለት ነጥቦችን ብቻ ያገኙ ሲሆን ከወራጅ ቀጠናም በአንድ ነጥብ ብቻ ርቀዋል።

ስፐርሶች በፕሪሚር ሊጉም ሆነ በሻምፒዮንስ ሊጉ ድንቅ ብቃት ላይ የሚገኙ ሲሆን ይህንን ከደገሙት ፓላሶችን ያሸንፋሉ።

የላውሮ ግምት፡ 0-2

Image copyright BBC Sport

ማንቸስተር ዩናይትድ ከቼልሲ

ማንቸስተር ዩናይትዶች በቂ የማጥቃት ፍላጎት የላቸውም። ኳስን በፍጥነት በመቀባበል እና ተጫዋቾችን በማለፍ ብዙ ተጫዋቾቻቸውን ወደፊት አያስኬዱም።

ቼልሲዎች ከባርሴሎና ጋር ምርጥ ብቃት ያሳዩ ምርጥ ተጫዋቾች ቢኖራቸውም አንድ ያልተስተካከለ ነገር ግን አለ።

ከባርሴሎና ጋር እንዳሳዩት አይነት ጨዋታ ይደግማሉ ብዬ አላስብም።

የላውሮ ግምት፡ 2-0

Image copyright BBC Sport

አርሴናል ከማንቸስተር ሲቲ (የካራባኦ ዋንጫ)

ማንቸስተር ሲቲዎች ይህን ጨዋታ ማሸነፋቸው ሶስት ዋንጫ ለማንሳት የተጣለባቸውን ግፊት እንዲቀንሱ ያደርጋቸዋል። እስካሁን ጥሩ ውድድር ጊዜ ቢያሳልፉም በዚህ ሳምንት ውቴታማ መሆን መቻላቸውን ማሳት የሚጀምሩበት ነው።

ዌምብሌይ ላይ ያሸንፋሉ? አዎ። በዊጋን ከደረሰባቸው ሽንፈት በኋላ ወደ ድል ይመለሳሉ። አርሴናልም ያስቆማቸዋል ብዬ አላስብም።

የላውሮ ግምት፡ 0-2