ፍቅርና ጋብቻ በቀይ ሽብር ዘመን

በገነት አባት ቤት እንግዳና ቄስ ባለበት ከአይናለም ጋር ቃል ሲገቡ

የፎቶው ባለመብት, Vintage Addis Ababa

ፍቅር ተስፋ በሌለባቸው ቦታዎችም ያብባል

ለአይናለምና ለገነትም ይህ ነበር የሆነው። እ.አ.አ በ1978 በኢትዯጵያ ታሪክ ከባድ የቀይ ሽበር ወቅት ተጋቡ።

የደም መፋሰሱ ከጋብቻቸው ከዓመት በፊተ የጀመረ ሲሆን፤ እሱም መንግሥቱ ኃይለማሪያም ሥልጣን ይዞ ጠላቶቹን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳበት ጊዜ ነበር። .

ሥልጣን በተቆጣጠረበትም ጊዜ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ሞቱ ደግሞም በሺህ የሚቆጠሩ ለመፈናቀል ተገደው ነበር።

ይህ ግን አይናለምንና ገነትን ከአዲስ አበባ ወጣ ብላ በምትገኘው በሰንዳፋ የጋብቻ ቃላቸውን ከመቀያየር አላገዳቸውም ነበር።

ለዚህ ታስበው የተወሰዱት ፎቶግራፎች ከ Vintage Addis Ababa ሲሆን በልዩ ሁኔታዎች ላይ ሰዎች እንዴት እንደሚኖሩ ማሳያ እንዲሆን ታስቦ በቤተ-መዛግብት የተቀመጡ ነበሩ።

ረዥሙ የመጠናናት ጊዜ

እ.አ.አ በ1973 ነበር፤ ወጣቶቹ የተዋወቁት በአንድ ሰፈር ይኖሩ ስለነበር ነው።

በዓመቱ ደርግ መንግሥት ወደ ሥልጣን ሲመጣ ለመንግሥቱ ኃይለማሪያም የሥልጣን ጥርጊያ መንገድ አመቻቸ።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ,

እ.አ.አ በ2008 በሌለበት መነግሥቱ ኃይለማሪያም ሞት ተፈርዶበታል። እሱ በዚምባብዌ ነው የሚኖረው።

ይህን ተከትሎ የተከሰተው ግርግር ሳያስቡት ሕይወታቸውን አንጠልጥሎ አስቀረው።

አይናለም ገነትን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እንደጨረሰች ለማግባት አቅዶ ነበር።

ሆኖም ግን እ.አ.አ በ1978 የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ተይዛ ለሦስት ወራት ታሰረች።

"በደርግ ስር መኖር ቀላል አልነበረም" ትላለች ገነት። በመቀጠልም "ያለው ፍራቻ ሙሉ ሰው ከመሆን ያደናቅፈን ነበር" ብላለች።

የደርግ ሥርዓት የታሰረን ሰው ቤተሰብ እንዲጠይቅ ባይፈቅድም፤ አይናለም ግን በየተወሰነ ቀናት ገነትን ያያት ነበር።

የአብዮቱ ጠባቂ ስለነበር ሌሎች ተቃዋሚዎች ስለግንኙነታቸው ቢያውቁ ለሕይወቷ ያሰጋ ስለበር በጣም ይጠነቀቅ ነበር።

"ሰላም መባባልም ሆነ መነጋገር አንችልም ነበር። ጥበቃዎቹ እንደምንተዋወቅ ሊያውቁብን ይችሉ ነበር። ሆኖም ግን ግቢው ውስጥ ባየሁት ቁጥር ደስ ይለኝ ነበር" ትላለች።

ገነት ታስራ የነበረ ቢሆንም የጋብቻቸው ፎቶግራፎች ግን የጉስቁልና አንዳች ምልክት የላቸውም።

ጉልበት ተሳመ

የሠርጋቸውን ዕለት በኢትዮጵያ ባህል መሠረት ጀመሩት።

አይናለም ገነትን ከቤተሰቦቿ ቤት ወደ እራሱ ቤት ለመውሰድ ከመሄዱ በፊት የእናቱን ጉልበት ስሞ ነበር ከቤቱ የወጣው።

የፎቶው ባለመብት, Vintage Addis Ababa

በቤቱ ደጃፍ ላይም ጎረቤትና ጓደኞቹ ሊሸኙት ተሰብስበው ነበር።

የፎቶው ባለመብት, Vintage Addis Ababa

የፎቶው ባለመብት, Vintage Addis Ababa

ጥቁር ሱፍ አንገትን በሚሸፍን ነጭ ሹራብ የለበሰው አይናለም ገነትን ለማምጣት ወደ ተዘጋጀችው ቼቭሮሌት አቀና ።

የፎቶው ባለመብት, Vintage Addis Ababa

ቀለበቶቻቸውን ፒያሳ ከሚገኘው አፍሪካ ወርቅ ቤት የገዙት ሙሽሮች ከሰዓት በኋላ በገነት አባት ቤት ቄስ ፊት ቃል ገቡ።

ከተጋበዙት 300 ሰዎችም ራቅ ብለው ሙሽሮቹ ፎቶግራፍም ለመነሳት ችለው ነበር።

የፎቶው ባለመብት, Vintage Addis Ababa

ለገነት በሚያሳዝን ሁኔታ ግን አይናለም እ.አ.አ በ2008 ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። እሷ ግን አብረው ያሳለፉትን ጊዜያት በጣም እንደምትወድና እንደምትናፍቅ ትናገራለች።

"ያፈቀርኩትን ሰው ነበር ያገባሁት፣ ያሳደግሁትም ከልቤ የምወዳቸውን ልጆች ነው" ትላለች።

የፎቶግራፎቹ መብት ሙሉ በሙሉ የVintage Addis Ababa ነው።