የጋሬት ክሩክስ የሳምንቱ ምርጥ ቡድን፡ አጉዌሮ፣ ሳላህ፣ ቻምበርሌይን፣ ኮምፓኒ

ማንቸስተር ሲቲዎች አርሴናልን 3 ለ 0 በማሸነፍ በፔፕ ጋርዲዮላ ስር የመጀመሪያ ዋንጫቸውን አንስተዋል። ማንቸስተር ዩናይትዶችም ቼልሲን 2 ለ 1 በማሸነፍ በሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተመልሰዋል።

እነማን በሳምንቱ ምርጥ ቡድን ውስጥ የሚያካትታቸውን አቋም አሳዩ?

የእግር ኳስ ተንታኙን የጋሬት ክሩክስን የሳምንቱን ምርጥ ቡድን እንደሚከተለው አቅርበናል።

ግብ ጠባቂ - ክላውዲ ብራቮ (ማን ሲቲ)

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ,

በማንቸስትር ግብ ጠባቂዎች የሊግ ዋንጫ ታሪክ ብራቮ ምንም ጎል ያልተቆጠረበት መጀመሪያው ግብ ጠባቂ ነው

አንድ ቡድን ሁለተኛ ግብ ጠባቂውን በሊግ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ ሲያሰልፍ መደናገጥ ሊፈጠርበት ይችላል። ብራቮ ከአርሴናል ጋር ነበረውን ጨዋታ ያስተናገደበት መንገድ ድንቅ ነበር።

ተከላካይ - ኤሪክ ዳየር (ቶተንሃም)

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ,

ከክሪስታል ፓላስ ጋር በነበረው ጨዋታ ዳየር ኳሶችን በመቀማት እና በመስጠት ከየትኛውም የቡድኑ ተጫዋቾች የበለጠ ነው

ኤሪክ ዳየር እንደዚህ ዓይነት ድንቅ አቋም ሲያሳይ የተመለከትኩት ከረዥም ጊዜ በኋላ ነው። ክሪስቲያን ቤንቴኬን እና አሌክሳንደር ሶርሎትንም በደንብ ተቋቁሟል።

ተከላካይ - ቨረጂል ቫን ዳይክ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ,

ቫን ዳይክ ከዌስት ሃም ጋር በነበረው ጨዋታ 10 የአየር ላይ ኳሶችን መቀማት ችሏል

ማንቸስተር ዩናይትዶች በሜዳቸው አሰልቺ ጨዋታን ሲጫወቱ በተቃራኒው ሊቨርፑሎች አንፊልድ ላይ አስደሳች ነበሩ። ቡድኑ ለረዥም ጊዜ ያጣውን በተከላካይ መስመር ላይ ያለ አለመረጋጋት ቫን ዳይክ አሳክቶታል።

ተከላካይ - ቪንሰንት ኮምፓኒ (ማን ሲቲ)

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ,

የትኛውም ማን ሲቲ ተጫዋች በካራባኦ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታው ላይ ከኮምፓኒ በላይ ኳስ የማራቅ ስራ አልሰራም

ከተደጋጋሚ ጉዳት በኋላ ቪሰንት ኮምፓኒ ዋንጫ ባነሳው የማንቸስተር ሲቲ ቡድን ውስጥ ተካቷል። ከተደጋጋሚ ጉዳቶች በኋላ በዚህ መሰሉ የዋንጫ ጨዋታ ላይ መሰለፍ ከሚገባቸው ተጫዋቾች መካከል አንዱ ኮምፓኒ ነው።

አማካይ - ሞሃመድ ሳላህ (ሊቨርፑል)

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ,

ሳላህ በዘንድሮው ዓመት በ31 ጎሎች ላይ ቀጥታ ተሳትፎ ነበረው

ሳልመርጠው ማለፍ አልችልም። ሞሃመድ ሳላህ ለሊቨርፑል በስድስት ተከታታይ ጨዋታዎች ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

አማካይ - አሌክስ ኦክስላዴ ቻምበርሌይ (ሊቨርፑል)

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ,

ሊቨርፑል ዌስትሃምን ባሸነፈበት ጨዋታ ቻምበርሌይን ከየትኛው ተጫዋች የበለጠ ዕድሎችን ፈጥሯል

አሁን መሳካት ጀምሯል። አሌክስ ኦክስላዴ ቻምበርሌይ ተጫዋች መምሰል ጀምሯል። ይህ ተጫዋች ትልልቅ መድረኮችን አይፈራም።

አማካይ - ዊሊያን (ቼልሲ)

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ,

ዊሊያን ዘንድሮ 12 ጎሎችን በሁሉም ውድድሮች አስቆጥሯል

ይህ ተጫዋች በሳምንቱ አጋማሽ ከባርሴሎና እንዲሁም ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋርም ድንቅ ነበር። አንቶኒዮ ኮንቴ ግን አልተሳካላቸውም። አሰልጣኙ ጥሩ ያልነበረውን አልቫሮ ሞራታን ትተው ኮከባቸወን ኤዲን ሃዛርድን ቀይረውታል።

አማካይ - አንድሪው ሮበርትሰን (ሊቨርፑል)

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ,

አንድሪው ሮበርትሰን በውድድር ዓመቱ ለሁለተኛ ጊዜ ለጎል የሚሆን ኳስ አቀብሏል

ባለፉት 14 የሊቨርፑል ጨዋታዎች በ13ቱ መሰለፉ ስለተጫዋቹ ብዙ ይመሰክራል። ከዌስት ሃም ጋር በነበረው ጨዋታ ያሻግራቸው የነበሩት ኳሶች ድንቅ ነበሩ።

አጥቂ - ሰርጂዮ አጉዌሮ (ማን ሲቲ)

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ,

ሰርጂዮ አጉዌሮ በአውሮፓዊያኑ 2018 ካደረጋቸው 13 ጨዋታዎች 15 ጎሎችን አስቆጥሯል

አርሴናሎች በካራባኦ ዋንጫ ፍጻሜ ከፍተኛ ሽንፈት ያተናገዱ ሲሆን ይህ ደግሞ የጀመረው ሰርጂዮ አጉዌሮ ሽኩርዳን ሙስታፊ ካለፈበት መንገድ ነው። አጥቂዎች ተከላካዮችን የሚፈሩበትን ጊዜ አስታውሳለሁ። የዛኔ ምን ይፈጠራል?

አጥቂ - ሮሜሉ ሉካኩ (ማን ዩናይትድ)

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ,

ከመስከረም ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ሉካኩ ጎል አስቆጥሮ ለጎል የሚሆን ኳስ ያቀበለው

ማንቸስተር ዩናይትዶች ውጤት እያስመዘገቡ ቢሆንም በሜዳቸው የሚያሳዩት ጨዋታ የሚስብ አይደለም። ደጋፊዎቹም በዚህ እየተበሳጩ ነው። ከቼልሲ ጋርም ተመሳሳይ የነበረ ሲሆን ሉካኩ ነው የደረሰላቸው።

አጥቂ - ግሌን ሙራይ (ብራይተን)

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ,

ዘንድሮ ሶሰት እንግሊዛዊያን ብቻ ናቸው ከሙራይ በላይ ጎሎችን ያስቆተሩት

ብራይተኖች ከስዋንሲ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ሦስት ወሳኝ ነጥቦችን ወስደዋል። የ34 ዓመቱ አጥቂ ግሌን ሙራይ ግብ ፊት ያለው መረጋጋት ብራይተኖች ለሁለተኛ ዓመት በሊጉ እንዲቆዩ ሊያደርጋቸው ይችላል።