በሶሪያ ግጭት የቱርክ ኃይሎች ላይ ከባድ ጥቃት ተሰነዘረ

turkish force

በሰሜናዊ ሶሪያ አፍሪን ስምንት የቱርክ ወታደሮች ሲገደሉ 13 ደግሞ ቆስለዋል።

የቱርክ ሰራዊት የኩርድ ተዋጊዎችን መፋለም ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እንዲህ ያለ ከባድ ጥቃት ደርሶበት አያውቅም።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ካውንስል ደግሞ በምሥራቃዊው የሃገሪቱ ክፍል ጎታ እየደረሰ ያለው ሰብአዊ ቀውስ ላይ ዛሬ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ ውይይት እንዲካሄድ ጥሪ ያቀረበችው እንግሊዝ ስትሆን በጎታ እየደረሰ ያለው የሰብአዊ ቀውስ ችላ መባሉንና በተደጋጋሚ የህክምና ተቋማት ላይ ጥቃት መሰንዘሩን አውግዛለች።

በአማፅያን ቁጥጥር ስር በሆነችውና ከደማስቆ ቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ጎታ ላይ በሶሪያ መንግሥትና በአጋሮቹ የቦምብ ድብደባ ከ580 ሰዎች በላይ ተገድለዋል።

393 ሺህ ንፁሃን ዜጎች ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ሲወድቁ ብዙዎችም ለምግብና ለመድሃኒት እጥረት ተጋልጠዋል።

የቆሰሉ ወታደሮችን ለመርዳት ቱርክ ሄሊኮፕተሮችን የላከች ሲሆን የጦር ኃይሉ ስለጥቃቱ የገለፀው ትናትና ነበር።