የላውሮ የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ግምት

Man Utd v Liverpool Image copyright BBC Sport

ጥቅምት ላይ በአንፊልድ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ሊቨርፑል ተገናኝተው ያለምንም ጎል አቻ ሲለያዩ ጆሴ ሞውሪንሆ መከላከልን መሠረት ያደረገ አጨዋወትን መርጠዋል በሚል ተተችተዋል። ቅዳሜስ ይህ ይደገም ይሆን?

የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን "ሞውሪንሆ ጥንቃቄ የተሞላበት አጨዋወት አይመርጡም። ከመረጡ ግን ከደጋፊዎቻቸው ተቃውሞ ያስተናግዳሉ" ይላል።

"አውቶብሱን አቁመው ባይከላከሉም የሊቨርፑልን የአጥቂ መስመር ለመግታት ትክክለኛ መከላከል ሥራ ግን ይሠራሉ። ምክንያቱ ደግሞ ቡድኑ ተከላካይ ክፍል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጥሩ አይደለም።"

"በተጨማሪም ማንቸስተር በማጥቃቱ በኩል እንዲንቀሳቀስ በማስቻል ቡድኑ ሚዛኑን የጠበቀ እንዲሆን ያደርጋሉ።"

ላውሮ በኦሎድትራፎርድ የሚደረገው ጨዋታ 1 ለ 1 ይጠናቀቃል ይላል። እናንተስ በዚህ ትስማማላችሁ?

የላውሮ ግምት

ቅደሜ

ማን ዩናይትድ ከሊቨርፑል

ማንቸስተር ዩናይትድ በሁለት የሊጉ ተከታታይ ጨዋታዎች ከኋላ በመነሳት ማሸነፍ ችሏል።

ሊቨርፑሎች ውጤታማ ጉዞ ላይ ሲሆኑ ካለፉት አምስት ጨዋታዎች 13 ነጥቦችን መሰብሰብ ችለዋል።

የላውሮ ግምት: 1-1

Image copyright BBC Sport

ኤቨርተን ከብራይተን

ኤቨርተኖቸ በሜዳቸው ጠንካራ ናቸው።

ብራይተኖች ጥሩ አቋም ቢኖራቸውም ቅድሚያ የምሰጣቸው በሜዳቸው በመጫወታቸው ለኤቨርተኖች ነው።

የላውሮ ግምት: 2-0

Image copyright BBC Sport

ሃደርስፊልድ ከስዋንሲ

የስዋንሲው አሰልጣኝ ካርሎስ ካርቫልሆ ቡድናቸው ዌስትሃምን 4 ለ 1 አሸንፎ ያለውን ጥንካሬ አሳይቷል።

ሃደርስፊልዶች ደግሞ መጥፎ ጊዜ እያሳለፉ ሲሆን 4-5-1 አሰላለፋቸውም ብዙ ወደ ፊት እንዳይሄዱ አድርጓል።

የላውሮ ግምት: 1-1

Image copyright BBC Sport

ኒውካስል ከሳውዝሃምፕተን

ሳውዝሃምፕተኖች ብዙ ዕድል መፍጠር ባለመቻላቸው ነው በወራጅ ቀጠና አካባቢ የሚዋልሉት።

ኒውካስሎችም ባለፈው ሳምንት ከሊቨርፑል ጋር በነበራቸው ጨዋታ ጎል እንዳይቆጠርባቸው ብቻ የሚጫወቱ ይመስል ነበር።

የላውሮ ግምት: 2-1

Image copyright BBC Sport

ዌስት ብሮም ከሌስተር

አንድ ወቅት አብረውት ለሚጫወቱ ቡድኖች አስቸጋሪ የነበረው ዌስት ብሮም ምን እንደሆነ አላውቅም፤ አሁን ከዛ በተቃራኒ ነው።

ሌስተሮች ደግሞ ያለፉትን አምስት ጨዋታዎች ማሸነፍ ባይችሉም ሰባተኛ ሆነው ለማጠናቀቅ ዕድል አላቸው።

የላውሮ ግምት: 0-2

Image copyright BBC Sport

ዌስት ሃም ከበርንሌይ

ከዋርት በኋላ ብርንሌዮች ባለፈው ሳምንት ኤቨርተንን ማሸነፋቸው ትልቅ ውጤታቸው ነው።

በአሁኑ ወቅት ከዌስት ሃም ምን እንደሚጠበቅ እርግጠኛ ስላልሆንኩኝ ጨዋታው አቻ ይጠናቀቃል ብዬ እገምታለሁ።

የላውሮ ግምት: 1-1

Image copyright BBC Sport

ቼልሲ ከክሪስታል ፓለስ

ዊልፍሬድ ዛሃ ባልተሰለፈባቸው ሶስት ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላሶቸ የተሸነፉ ሲሆን አስደሳቹ ዜና ተጫዋቹ ከጉዳት መመለሱ ነው።

ባለፉት ሁለት ሳምንታት ቼልሲ በማንቸስተር ቡድኖች በተከታታይ ተሸንፏል። በዚህ ጨዋታ ግን ያንሰራራል የሚል እምነት አለኝ።

የላውሮ ግምት: 2-0

እሁድ

Image copyright BBC Sport

አርሴናል ከዋትፎርድ

በዘንድሮው ዓመት በሜዳቸው አርሴናልን ካሸነፉ ቡድኖች ዋትፎርድ አንደኛው ሲሆን ይህ ግን ኤምሬትስ ላይ አይሳካም።

መድፈኞቹ አሁንም ጨዋታዎችን ማሸነፍ ይችላሉ።

የላውሮ ግምት: 3-0

Image copyright BBC Sport

በርንማውዝ ከቶተንሃም

ቶተንሃሞች ከጁቬንቱስ ከቻምፒዮምስ ሊጉ ውጭ የሆኑበት መንገድ ሊያበሳጫቸው ይችላል። ምክንያቱም ለዚህ የሚያበቃ ስህትት አልሰሩም።

ብርንማውዞች ሌስተርን ለማሸነፍ ከጫፍ ደርሰው ሪያድ ማህሬዝ ባለቀ ሰዓት ባስቆጠራት ጎል አቻ ወጥተዋል። ይህ ግን ከቶተንሃም ጋር የሚሆን አይመስለኝም።

የላውሮ ግምት: 0-2

ሰኞ

Image copyright BBC Sport

ስቶክ ከማን ሲቲ

የስቶክ ችግር ያልተፈታ ሲሆን ባለፈው ሳምንትም አቻ ወጥተዋል። አሁንም ጎል ማስቆጠር እየቻሉ አይደለም።

ፔፕ ጋርዲዮላ በሜዳቸው ያለመሸነፍ ጉዟቸው በባሴል የተቋጨ ቢሆንም አሁንም ምንም የሚያሰጋቸው ነገር የለም።

የላውሮ ግምት: 0-2