የአሜሪካ ኢንተለጀንስ መሥሪያ ቤት አለቃ ዩናይትድ ስቴትስ ግንኙነቱ የሚያስከትለውን መዘዝ ተገንዝባለች ብለዋል

ህዋሶንግ 15 ሚሳይል የ ኮርያን ሕዝብ ጦር ኃይል 70ኛ ዓመት ለማክበር በአደባባይ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሰሜን ኮርያ የኒውክሊዬር መሣሪዎቿን አፋጥናለች

የሲአይኤ ዳይሬክተር የሆኑት ማይክ ፖምፔዎ ትራምፕ ከሰሜን ኮረያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር ለመገናኘት መወሰናቸው የሚያስከትለውን መዘዝ ይረዳሉ በማለት ተናግረዋል።

አለቃ ፖምፔዎ እሁድ ለፎክስ ኒውስ በሰጡት ቃል ፕሬዚዳንት ትራምፕ ''ትርዒት ለማሳየት ሳይሆን ሥራ ለመሥራት ነው የሚሄዱት'' ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ እንደተናገሩት ወደፊት የሚካሄደው ስበሰባ 'ለዓለም ትልቅ ነገር' ሊያስከትል ይችላል።

ተቺዎች ግን የግንኙነቱ ውጤት አመርቂ ካልሆነ ሁለቱ ሃገራት ከዚህ ቀደም ከነበሩበት በተባባሰ ሁኔታ ላይ ሊገቡ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

ከዚህ በፊት በሥልጣን ላይ ያለ ማንኛውም የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የሰሜን ኮርያን መሪ አግኝቶ አያውቅም።

እንደዚህ ዓይነቱን ስብሰባ ፒዮንግያንግ ብትፈለገውም እውን ሊሆን ይችል የነበረው ግን ሰሜን ኮርያ ብዙ ለውጦችን ካሳየች ብቻ እንደነበር ሲነገር ቆይቷል።

እንደተነገረው ከሆን ፕሬዚዳንት ትራምፕ የስብሰባው ጥያቄ ባለፈው ሐሙስ ከሰሜን ኮርያ መልዕክተኞች እንደቀረበላቸው መቀበላቸው በርካቶችን አስገርሟል።

ሰሜን ኮሪያ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ትክክለኛ መሥፈርቶች ከቀረቡ የኒውክሊዬር መሣሪያ ግንባታን ለመተው ዝግጁ መሆኗን ስታሳውቅ ነበር።

ሰሜን ኮሪያ እ.አ.አ ከ2003 ጀምሮ እራስዋን ከኒውክሊዬር መሣሪዎችን ያለማስፋፋት ስምምነት ማስወጧቷ የሚታወስ ነው።

እንደ አቶ ፖምፔዎ ለሆነ ግን የትራምፕ አስተዳደር ከሰሜን ኮርያ ጋር ለመነጋገርና ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ ዝግጁ ነው።

ኪም ጆንግ ኡን በሁኔታው ሊጠቀም ይችላል የሚል ፍራቻ

በዩናይትድ ስቴትስ ያሉት ሁለቱም ዋነኛ የፖለቲካ ምድቦች በታሰበው ስብስባ መስጋታቸውን በማሳወቅ ላይ ናቸው።

የሪፐብሊካን ሴኔተር ኮሪ ጋርድነር "ቋሚና ማረጋገጫ ያለው የኒውክሊዬር ማቀጠጥ መታየት አለበት" ይላሉ፤ ጄፍ ፍሌክ የተሰኙት ሌላ የሪፐብሊካን አባል ደግሞ የኒውክሊዬር ማቋረጡ ሂደት ላይሳካ እንደሚችል ተናግረዋል።

Image copyright AFP

የዴሞክራቶቾ ሴኔተር ኤሊዛቤት ዋረን ''ፐሬዚዳንታችን እንዲሳካላት እፈልጋለሁ ምክንያቱም እሱ ተሳካለት ማለት አሜሪካ ተሳካላት ማለት ሰለሆነ ይህ ደገሞ ምድራችን ስጋት ላይ አትወድቅም ማለት ነው'' ብላለች።

በፔንሲልቬንያ ግዛት ባለፈው ቅዳሜ በተካሄደው ሰልፍ ላይ የተገኙት ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸው ሰሜን ኮሪያ 'ሰላም ትፈልጋለች' ሲሉ ተደምጠዋል።

አክሎም ኒውክሊዬር የማቋረጥ ፍላጎት ካላሳዩ ጊዜ ሳይፈጅ ስብሰባውን ለቀው እንደሚወጡም ነግሯቸዋል።

ምንም እንኳ ትራምፕ ከኪም ጋር ለመገናኘት የቸኮሉ ቢመስሉም ዘግይተው የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ሰሜን ኮሪያ በጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት አስተያየት አልሰጠችም።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ