ሥራቸውን የጨረሱ መንኮራኩሮች መጨረሻቸው የት ነው?

የቲያንጎንግ መንኩራኩር Image copyright china manned space engineering

የቻይናው ቲያንጎንግ - 1 የጠፈር ጣቢያ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ሲሆን እንደ ቀድሞ መንኮራኩሮች ራቅ ያለ ስፍራ ሳይሆን በያዝነው የአውሮፓውያን አዲስ ዓመት ወደ ምድር ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ከምድር 2700 ኪሜ ርቆ በጥልቅ ውቅያኖስ ላይ በአውትራሊያ፣ ኒው ዚላንድ እና ደቡብ አሜሪካ መካከል የሚገኝ አንድ ሥፍራ አለ።

ይህ ሰው በማይደርስበት የውቅያኖስ ጥግ የሚገኝ ሥፍራ ታዲያ የሳተላይት ባለሙያዎችም ትልቅ ትኩረት ስቧል። ምክንያቱም በምድር ዙሪያ የሚዞሩት ሳተላይቶች የሚያርፉት በዚያ ቦታ ነውና።

ከጠፈር የሚመለሱ አነስተኛ መጠን ያላቸው ሳተላይቶች የሚቃጠሉ ሲሆን ትልልቆቹ ግን ስብርባሪያቸውም ቢሆን መሬት ሊደርስ ይችላል። ሰው በሚኖርባቸው አካባቢዎች ተከስክሰው ጉዳት እንዳያደርሱ በሚል ሰው የማይደርስበት የውቅያኖስ ክፍል ላይ እንዲወደቁ ይደረጋል።

የይህ ቦታ ከጠፈር ለሚመለሱ ሳተላይቶቹ የቀብር ስፍራቸው ነው። እስካሁን ከ260 በላይ የሚሆኑ ሳተላይቶች ቀብራቸውን እዚህ ሥፍራ የፈፀሙ ሲሆን አብዛኛዎቹ ደግሞ የሩሲያ ንብረት ናቸው።

በአውሮፓውያኑ 2001 በአካባቢው የተበታተነ አንድ 120 ቶን የሚመዝን ሳተላይትን ስብርባሪ አንዳንድ አሳ አስጋሪዎች ሰማይ ላይ እንዳዩት ተናግረው ነበር።

Image copyright Getty Images

በዓመት ውስጥ ብዙ ጊዜ ወደ ዓለም አቀፍ የጠፈር ምርምር ጣቢያ ዕቃዎችን የሚያጓጉዝ ሳተላይት የጣቢያውን ቆሻሻ ይዞ በዚህ ቦታ ይቃጥላል።

ቁጥጥር ስለሚደረግበትም በዚህ ምክንያት ማንም ላይ ጉዳት አይደርስም። በአካባቢው ያለው ውሃ ለአሳ የሚሆን ምግብ ስለማይዝ የአሳ ማስገር ስራ አይከናወንም። ይህንን ማንም ያልደረሰበትን ቦታ ወደ ፊት በዓለም አቀፉ የስፔስ ጣቢያ የሚጎበኝ ነው።

አሁን ያለው ዕቅድ በውቅያኖስ የማይደረስበት ሥፍራ ላይ ሳተላይቶችን በተጠና መልኩ ከስራ ውጭ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። አንዳንድ ጊዜ ከምድር ያሉ ተቆጣጣሪዎች ከሳተላይቶቹ ጋር ግንኙነታቸው ከተቋረጠ ሳተላይቱን ወይንም የጠፈር ጣቢያውን በደቡባዊ ፓስፊክ እንዲወድቅ ማድረግ አይቻልም።

Image copyright NASA

ይህ ነገር 36 ቶን በምትመዝነዋና በደቡብ አፍሪካ በአውሮፓውያኑ 1991 የተከሰከሰችው 'ሳልየት 7' እና በ1979 አውስትራሊያ የወደቀችው 'አሜሪካን ስካይ ላብ' ላይ አጋጥሟል። እስከሚታወቀው ድረስ ምድር ላይ ያለ ሰው በሳተላይት ስብርባሪ ስለመጎዳቱ ምንም መረጃ የለም።

ከመስከረም 2018 ጀምሮ ባሉት አራት ወራት የቻይናዋ ቲያንጎንግ - 1 ወደ ምድር ትመለሳለች። ይህች የመጀመሪያዋ የቻይና ሳተላይት በ2011 ነነበር እንድትመነጠቅ የተደረገው።

የቲያንጎንግ - 1 በድጋሚ ወደ ዑደቱ ከመግባቷ በፊት ከጥቅም ውጭ እየሆነች ነው። ሆኖም ከቻይና መሃንዲሶች ቁጥጥር ውጭ በመሆኑ አቃጥለው በደቡባዊ ፓስፊክ እንዲከሰከስ ለማደረግ አልቻሉም።

ሰሳተላይቷ ከመቃጠሉ ጥቂት ሰዓታቶች በፊት በእርግጠኝነት የምትወድቅበትን ቦታ መለየት ባይቻልም ቦታው ከሰሜናዊ ስፔን እስከደቡባዊ አውስትራሊያ ያለውን ቀጠና ያካልላል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ