የ16 ዓመቱ ሶማሊያዊ ኮሚሽነር ሆኖ እንዲሠራ ጥያቄ ቀረበለት

ፈይዛል አብዱላሂ ኦማር Image copyright Faysal Abdullahi Omar
አጭር የምስል መግለጫ ኦማር የሥራ ቅጥር ደብዳቤው ከደረሰው በኋላ ትምህርት ቤት መሄድ አንዳቆመ ይናገራል

የ16 ዓመቱ ሶማሊያዊ ታዳጊ በሃገሪቱ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ የምክትል ኮሚሽነር ቦታ ቢሰጠውም ለደህንነቱ በመስጋት እንዳልተቀበለ ተነግሯል።

ፈይዛል አብዱላሂ ኦማር የተባለው ታዳጊ በደቡብ ምስራቋ ሂርሻቤሌ ግዛት ዋና የሆነችው የጆውሃር ከተማ ምክትል ኮሚሽነር እንደሆን ነበር የተሾመው።

የሁለተኛ ደረጃ ተማሪው ኦማር ለቢቢሲ እንደተናገረው የአልሸባብ ታጣቂዎች ዒላማ ሊያደርገጉት እንደሚችሉ በመስጋት ነው ስልጣኑን መቀበል ያልፈለገው።

ኦማር ይህ ሥልጣን እንደሚሰጠው በቅድምያ የተነገረው ምንም ነገር እንዳልነበረም አሳውቋል። ይህ የተወሰነው በጎሳ መሪዎቹ ቢሆንም እሱ ግን ትምህርቱ ላይ ማተኮር አንደሚፈልግ ይናገራል።

''አሁን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን እያጠናቀቅኩኝ ነው። ከጥቂት ወራት በኋላ ደግሞ ዩኒቨርሲቲ ገብቼ የወደፊት ኑሮዬን መገንባት እፈልጋለሁ'' በማለት ለቢቢሲ ሶማሊ ተናግሯል።

የሹመት ደብዳቤው ከደረሰው በኋላ ባሉት ቀናት ትምህርት ቤት እንዳልሄደም ተናግሯል።

የኦማርም ቤተሰቦች በተሰጠው ሥልጣን ደስተኛ አልነበሩም። የማህበረሰቡ አባላት ግን ሥለልጣኑን አንዲቀበልና ለአካባቢው ወጣቶች ምሳሌ እንዲሆን እየገፋፉት ነው።

''ብዙ ሰዎች ስልጣኑን እንድይዝ ይገፋፉኝ ነበር'' ሲል ኦማር ይናገራል።

ጆውሃር ከሞጋዲሹ በስተሰሜን የምትገኝ ሲሆን በሶማሊያ መንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለች ከተማ ናት። በአካባቢዋ ያሉ መንደሮች በሙሉ ግን ግን በአልሸባብ ቁጥጥር ሥር ናቸው።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት የፓርላማ አባልትና የክልል ሚኒስትሮች በታጣቂዎቹ መገደላቸው ይታወሳል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ