ድርጅታቸው በከሰረ በሳምንቱ ያረፉት ታዋቂው ባለሃብት

የድርጅቱ ምልክት ከሆነችው 'ጆፍሪ ቀጭኔዋ' ጋር ቻርልስ ላዛረስ Image copyright Toys R Us

'ቶይስ አር አስ' በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ድንበር ዘለል የሕፃናት መጫወቻ ዕቃዎች መደብር መሥራች የሆኑት ቻርልስ ላዛረስ በ94 ዓመታቸው ማረፋቸው ተሰምቷል።

ቻርልስ ላዛረስ በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ከነበረባቸው ወታደራዊ አገልግሎት እንደተመለሱ ነበር የልጆች መጫወቻ መደብር ከፍተው ወደ ንግዱ ዓለም የዘለቁት።

ነገር ግን ባለፈው ሳምንት በአሜሪካና እንግሊዝ ያሉ ግዙፍ መደብሮቻቸው በኪሳራ ምክንያት ሊዘጉ እንደሆነ ተነገረ። ይህ በሆነ በሳምንቱ ነው የባለቤትና መስራቹ ላዛረስ ሞት የተሰማው።

''ያሳለፍነው ሳምንት ለድርጅታችን እጅግ ከባድ ነበር። ከሁሉም በላይ ግን የመሥራቹ ላዛረስ ሞት ጥልቅ ሃዘን አስከትሎብናል'' በማለት ድርጅቱ በድረ ገፁ ላይ አስፍሯል።

ባለፈው ሐሙስ ነበር ድርጅቱ ''ባለተጠበቁ ምክንያቶች'' የሽያጭ መደብሮቹን ሊዘጋ እንደሆነ ያስታወቀው።

Image copyright Getty Images

በፈረንጆቹ 2008 ቻርልስ ላዛረስ 'አንትረፕረነር ማጋዚን' ለተሰኘው መጽሔት በሰጡት ቃለ መጠይወቅ ላይ ድርጅቱን ለመክፈት የተነሳሱት ከጦርነቱ ሲመለሱ ጓደኞቻቸው በሙሉ እንደተመለሱ የሚያደርጉትን ሲነግሯቸው የሁሉም ምኞት ተመሳሳይ ሆኖባቸው ነው።

ሁሉም እንደተመለሱ አግብተው፣ ልግ ወልደው የእራሳቸውን ቤተሰብ እንደሚያቋቁሙ ሲነግሯቸው ለልጆች የሚሆኑ ጠረጴዛና ወንበር የመሳሰሉ የግልጋሎት ዕቃዎችን ለመሸጥ ሃሳብ ሰጣቸው።

በዋሽንግተን ዲሲ ተመልሰውም ቻርልስ የአባተቸውን የቢስኪሌት ሱቅ ወደ ዕቃ መደብር ቀየሩት።

'ተይስ አር አስ'ን ሲጽፉም ሆነ በወቅቱ የነበራቸውን መደብር 'አር' የተሰኘችውን የእንግሊዘኛ ፊደል ገልብጠው ነበር። ምክንያቱንም ሲያስረዱ ልጅ የጻፈው እንዲመስል ነው ነበር ያሉት።

ቻርለስ ከመገልጌኣ ዕቃዎች ወደ መጫወቻችም መሸጥ ያለፉት የልጆች መጫወቻዎች ብዙም ስለማእቆዩ ለሽያጭ ጥሩ መሆኑን ተገንዝበው ነበር።

እሳቸው ይህን ድረጅት ከመክፈታቸው በፊት የልጆች መጫወቻ ገበያ ወቅታዊ ነበረ።

ቻርልስ በ1994 በድርጅቱ ውስጥ መሥራት ቃቆሙበት ጊዜ አንስቶ ድርጅቱ እየተቸገረ ነበር። የበይነ-መረብ ገበያዎች ሲከፈቱ ደግሞ በተለይ ደግሞ ወደ መደብሩ የሚሄዱ የቤተሰብ ቁጥሮች እየቀነሱ መጥተው ነበር።

ባለፈው ሳምንትም ድርጅቱ በአሜሪካና በእንግሊዝ የቀሯቸውን መደብሮች እንደሚዘጉ አሳወቀው ነበር።