የላውሮ የፕሪሚየር ሊግ ግምቶች

ከዓለም አቀፍ የወዳጅነት ውድድሮች በኋላ ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቅዳሜ እና እሁድ ቀጥሎ ይካሄዳል።

የ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክሪስታል ፓላስን ከሊቨርፑል በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀምራል።

የቢቢሲው የስፖርት ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን የጨዋታዎቹን ግምት እንዲህ ያስቀምጣል።

ቅዳሜ

Image copyright BBC Sport

ክሪስታል ፓላስ ከ ሊቨርፑል (8:30)

ከወዳጅነት ጨዋታዎች በፊት ክሪስታል ፓላሶች ሃደርስፊልዶችን በሜዳቸው ላይ 2 ለ 0 ያሽነፉበት ውጤት በውድድር ዘመኑ ካስመዘገቡት ጣፋች ድሎች መካከል አንዱ ነው።

አሁንም ከወራጅ ቀጠናው ለማምለጥ ፓላሶች ነጥቦችን መሰብሰብ አለባቸው። ከሊቨርፑል በሚኖራቸው ጨዋታም ይህንኑ ማድረግ ይችላሉ ይላል ላውሮ።

የላውሮ ግምት፡ ክሪስታል ፓላስ 1 - 1 ሊቨርፑል።

Image copyright BBC Sport

ብራይተን ከ ሌስተር ሲቲ (11፡00)

ሌስተሮች ከኤፍኤ ካፕ ቢሰናበቱም በፕሪሚየር ሊጉ ሰባተኛ ደረጃን ይዘው ለመጨረስ ከበርንሌይ እና ኤቨርተን ጋር ብርቱ ፉክክር እያደረጉ ነው። ይህም ሳውዝሃምፕተን ኤፍኤ ካፕን የማያሸንፍ ከሆነ ሌስተሮችን የአውሮፓ ሊግ ተሳታፊ ያደርጋል።

ስለዚህ ቀበሮዎቹ ለማሸነፍ ብዙ ምክንያቶች አላቸው።

ብራይተኖችም ቢሆኑ በማንችስተር ዩናይትድ ተሸንፈው ከኤፍኤ ካፕ ውድድር ተሰናብተዋል። በፕሪሚየር ሊጉ የቅደመ ጨዋታም በኤቨርተን ተሸንፈዋል። ብራይተኖች ከሌስተር የሚያደርጉት ጨዋታ በሜዳቸው እንደመከናወኑ መጠን የተሻለ ውጤት ያስመዘግባሉ።

የለውሮ ግምት፡ ብራይተን 1-1 ሌስተር።

Image copyright BBC Sport

ማንስተር ዩናይትድ ከ ስዋንሲ (11፡00)

የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቾች ባለፉት ቀናት በተካሄዱት የወዳጅነት ጨዋታዎች ላይ ያሳዩት እንቅስቃሴ ጥሩ የሚባል ነበር። ሮሜሎ ሉካኩ እና ፖል ፖግባ ለቤልጅየም እና ፈረንሳይ ጎሎችን ማስቆጠር መቻላቸው ለማንችስተር ዩናይት መልካም ዜና ነው።

ስዋንሲም ቢሆን በካርሎስ ካርቫለሃል ስር ሆኖ ከአሥር ጨዋታ በሁለቱ ብቻ መሸነፋቸው ጥሩ የሚባል ሪከርድ ነው። ይሁን እንጂ ማንችስተር ዩናይትድን በሜዳው መቋቋም የሚችሉ አይመስለኝም።

የላውሮ ግምት፡ ማንችስተር ዩናይትድ 2 - 1 ስዋንሲ።

Image copyright BBC Sport

ኒውካስትል ከ ሃድርስፊልድ (11፡00)

ኒውካስትል ዩናይትዶች በሴንት ጀምስ ፓርክ ያደረጉትን ሁለት ያለፉ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ ችለዋል። በፕሪሚየር ሊጉ ለመቆየት ይህን ጨዋታ ማሸነፋቸው ወሳኝ ነው።

የኒውካስትል ደጋፊዎች በፕሪሚየር መቆየታቸውን ማረጋገጥ ስለሚፈልጉ ቡድናቸው ይህን ጨዋታ እንዲያሽንፍ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ሃደርስፊልዶች በሳለፈነው ወር የተሸለ ቀርጽ ይዘው ይጫወቱ ነበር። በክሪስታል ፓላስ በሜዳቸው መሸነፋቸው የቡድኑ ስሜት እንዲወርድ አድርጎታል።

የላውሮ ግምት፡ ኒውካስትል 2-0 ሃድርስፊልድ።

Image copyright BBC Sport

ዋትፎርድ ከ ቦርንዝማውዝ (11፡00)

በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ሁለቱም ቡድኖች በ36 ነጥቦች በጎል ክፍያ ተበላልጠው ቦርንዝማውዝ 10ኛ ዋትፎርድ ደግሞ 11ኛ ላይ ይገኛሉ። ቡድኖቹ ለመሸናነፍ የሚያደርጉት ጥረት ከፍተኛ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ዋትፎርዶች በሜዳቸው እንደመጫወታቸው የተሻለ ዕድል ቢኖራቸውም አቋማቸው ስለሚዋዥቅ ውጤቱን መገመት ከባድ ነው።

ዋትፎርዶች በአርሰናል እና በሊቨርፑል በሰፊ የጎል ልዩነት ሽንፈትን አስተናግደው ነበር። አሁንም ቢሆን ሊሽነፉ እንደሚችሉ ይገመታል።

የላውሮ ግምት፡ ዋትፎርድ 1- 2 ቦርንዝማውዝ።

Image copyright BBC Sport

ዌስት ብሮም ከ በርንሌይ (11፡00)

የዌስት ብሮም አሰልጣኝ አለን ፓርዲው በቦርንማውዝ የደረሰበትን ሸንፈት ተከትሎ በፕሪሚየር ሊጉ የመቆየት የመጨረሻ ዕድላቸው ላይ አንዳሉ ተናግረው ነበር።

ፓርዲው ይህን ይበሉ እንጂ በፕሪሚየር ሊጉ የመቆየታቸው ነገር የከተመለት ይመስላል።

ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት ቢያንስ 10 ነጥቦች ያስፈልጋቸዋል። በፕሪሚያርሊጉ የቀሯቸው ጨዋታዎች ሰባት ብቻ ናቸው። ለዌስት ብሮም በፕሪሚየር ሊጉ የመቆየት ጉዳይ ትልቅ የቤት ሥራ ነው።

በሌላ በኩል በርንሌዎች ሰባተኛ ደረጃን ለመያዝ እየተፋለሙ ናቸው፤ ምናልባትም የአውሮፓ ሊግ ተሳታፊ ለመሆን።

ዌስት ብሮሞች የመጨረሻዎቹን የፕሪሚየር ሊግ ሳምንቶች እንዴት እንደሚወጡት እንመለከታለን።

የላውሮ ግምት፡ ዌስት ብሮም 1-1 በርንሌይ።

Image copyright BBC Sport

ዌስት ሃም ከ ሳውዝሃምፕተን (11፡00)

በቀደሞው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ዌስት ሃም በሜዳው በበርንሌይ 3 ለ 0 ተሸንፎ ነበር። ዌስት ሃሞች ተሻሽለው ይቀርባሉ ወይ የሚለው ጥያቄ የበርካቶች ነው።

ይህ ጨዋታ ለሁለቱም ቡድኖች እጅግ ወሳኝ ነው።

የላውሮ ግምት፡ ዌስት ሃም 2-1 ሳውዝሃምፕተን።

Image copyright BBC Sport

ኤቨርተን ከ ማንችሰተር ሲቲ (1:30)

ኤቨርተኖች ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ ቢችሉም፤ ማንችስተር ሲቲን የማሽነፈ አቅም ያላቸው ግን አይመስለኝም።

ሲቲዎች ይህን ጨዋታ እና በቀጣይ ማንችስተር ዩናይትድን በሜዳቸው አስተናግደው ካሸነፉ የውድድር ዘመኑ አሸናፊ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ።

ሲቲዎች ከኤቨርተን ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ሊያሸንፉ ይችላሉ። ይሁን እንጂ ሞሪኒዮ ተሸንፈው ሲቲዎች ሻምፒየን እንዲሆኑ የሚፈቅዱላቸው አይመስለኝም።

የላውሮ ግምት፡ ኤቨርተን 0 - 2 ማንችስተር ሲቲ።

እሁድ

Image copyright BBC Sport

አርሰናል ከ ስቶክ (9:30)

አርሰናል በሜዳውም ይሁን ከሜዳው ውጪ፤ ከታላላቅም ይሁን ከየትኛውም ዓይነት ቡድን ጋር ሲጫወት፤ ውጤቱን መገመት ከባድ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ጨዋታ እንደሚያሸንፉ እርግጠኛ ነኝ።

ስቶክ ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት ጥረት ሊያደርጉ ይችላሉ። ይሁን እንጂ አርሰን ዌንገር በቀላሉ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ይገመታል።

የላውሮ ግምት፡ አርሰናል 3-0 ስቶክ

Image copyright BBC Sport

ቸልሲ ከ ቶተንሃም (12፡00)

ቸልሲ ከቶተንሃም ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ያለው ትልቁ ዕድል ይህ ነው። ቸልሲ ከቶተንሃም በልጦ ለመጨረስ ከፈለገ ይህን ጨዋታ ማሸነፍ ግድ ይለዋል።

ድንቅ ጨዋታ እንደሚያሳዩ እምነት አለ።

ይህን ጨዋታ ቸልሲ ሊያሸንፍ እንደሚችል ይገመታል።

የላውሮ ግምት፡ ቸልሲ 2-0 ቶተንሃም

ተያያዥ ርዕሶች