ዴ ሂያ፣ ሲልቫ፣ አሊና ማኔ ከሳምንቱ ምርጥ 11 መካከል ናቸው

ቅዳሜ እና አሁድ ከተከናወኑት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች መካከል መሃመድ ሳላህ 29ኛ ግቡን ባስቆጠረበት ጨዋታ ሊቨርፑል ማሸነፍ ችሏል።

ሊቨርፑልን ጨምሮ ሌይስተር፣ ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ኒው ካስትል፣ በርንሌይ፣ ዌስት ሃም፣ አርሴናል፣ ማንችስተር ሲቲ እና ቶተንሃም ድል ቀንቷቸዋል።

የኳስ ተንታኙ ጋርዝ ክሩክስ እስቲ አስገራሚ ፍልሚያዎችን ካየንበት ያለፈው ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር ነጥረው የወጡ ምርጥ 11 ተጫዋቾችን እንመልከት ይለናል።

ግብ ጠባቂ - ዴቪድ ዴያ (ማንችስተር ዩናይትድ)

ሃገሩ ሰፔን ከአርጀንቲና ጋር በነገራት ፍልሚያ አንድ ጎል የተቆጠረበት ዴ ሂያ ክለቡ ዩናይትድ ከስዋንሲ ጋር በነበረው ጨዋታ ግን አልተበገረም።

የመጀመሪያዋን ኳስ ሲመልስ እጆቹ ከወርቅ የተሠሩ ሳይሆኑ አይቀርም እያልኩ ሳስብ ነበር።

ሁለተኛው ደግሞ ይበልጥ ያስደንቅ ነበር፤ ምክንያቱም ወደ ጎል ሳይጠጋ ነበር ኳሷን ያያት።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ተከላካይ - ዴቪንሰን ሳንቼዝ (ቶተንሃም)፣ ጃን ቬርቶገን (ቶተንሃም)፣ ቪንሰንት ኮምፓኒ (ማንችስተር ሲቲ)

የፎቶው ባለመብት, .

ዴቪንሰን ሳንቼዝ

ህዩጎ ሎሪስ ባጠፋው ጥፋት የመጀመሪያ ጎል የተቆጠበረት ቶተንሃም ጨዋታው በሽንፈት ሊያጠናቅቅ ይችላል ተብሎ ቢሰጋም፤ እንደ ወትሮው የሳንቼዝ ብቃት ግን በጣም የሚያስገርም ነበር። በከባድና አስቸጋሪ ጨዋታዎች ላይ ሳይረበሽ መጫወትን ልምድ ሳያደርገው አይቀርም።

ጃን ቬርቶንገን

ከሎሪስ ጥፋት ቀጥሎ ቶተንሃሞች እንዲያገግሙ በመርዳተት በኩል ከቼልሲ ጋር ባደረጉት ጨዋታ የቬርቶንገን ተሳትፎ ወሳኝ ነበር ።

ቪንሰንት ኮምፓኒ

ልክ እንደ ቡድኑ ኮምፓኒ ሙሉ ጨዋታውን ምንም ሳይጎዳ ጨርሷል። ይህ ደግሞ ማንችስተር ሲቲን የፍልሚያው አሸናፊዎች ሊያደርጋቸው እንደሚችል አያጠራጥርም።

በዚህ ሳምንት መርሃ ግብር ከማንችስትር ዩናይትድ ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ ከእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ይልቅ የሆሊውድ ፊልም ሊያስመስለው ይችላል። ካሸነፉና ዋንጫውን ካነሱ የካምፓኒ በጨዋታው ላይ መገኘት የበለጠ ያሸበረቀ ያደርገዋል።

አማካይ - ጄ ሊንጋርድ (ማንችስተር ዩናይትድ)፣ ክርስቲያን ኤሪክሰን (ቶተንሃም)፣ ዴቪድ ሲልቫ (ማንችስተር ሲቲ) እና ዴሌ አሊ (ቶተንሃም)

የፎቶው ባለመብት, .

ጄሲ ሊንጋርድ

ይህ ወጣት በሩስያው ዓለም ዋንጫ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ከቋሚ 11 ጋር መሰለፍ ይኖርበታል። የማንችስተር ኃላፊ ጆዜ ሞሪንዮ ሊንጋርድን እየቆጠቡ ይመስላል።

ሊንጋርድ ደረማምሶ እራሱን ከቋሚዎቹ ጋር ከማሳለፉም ባሻገር ጨዋታዉን በቁጥጥሩ አድርጓል።

ከስዋንሲ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ዩናይትድ ያስገቧቸው ግቦች በሙሉ የሊንጋርድ እግር አለባቸው።

ክርስቲያን ኤሪክሰን

የዚህ ተጫዋች ብቃት ከዚህ በላይ ሊሻሻል የሚችለው ዋንጫ ቢጨመርለት ብቻ ነው። ኤሪክሰን በጣም ጥሩ ከመሆኑም ባሻገር ጨዋታውን በጥሩ ግቦች እያሳረገ ይገኛል።

ከቼልሲ ጋር ባደረጉት ጨዋታ የለጋት ኳስ ዊሊ ካባዬሮን በ20 ሜትር ርቀት በላይ ነበር ያለፈችው።

ዴቪድ ሲልቫ

ሲቲዎች እስካሁን ካደረጓቸው 38 ጨዋታዎች አንዴ ብቻ ነው የተሸነፉት።

የኤቨርተኑ ግብ ጠባቂ ጆርዳን ፒክፎርድ ኳሷን ለማዳን እያርበደበደው እንኳ ሲልቫ በመርፌ ቀዳዳ ኳስ ለአጋሮቹ ሲያሳልፍ ነበር።

ዴሌ አሊ

የቶተንሃሙ አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ዴሌ አሊ ክህሎቱን እንዲያንፀባርቅ ረድተውታል። ከቼልሲ ጋር ባደረጉት ጨዋታ የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ ብዙ ያልነበረው አሊ በሁለተኛው ግማሽ ግን ጨዋታውን አጋግሏል።

አጥቂ መስመር - ሳድዮ ማኔ (ሊቨርፑል)፣ ማርኮ አርኖቶቪች (ዌስት ሃም)፣ ሊሮይ ሳኔ (ማንችስተር ሲቲ)

የፎቶው ባለመብት, .

ሳድዮ ማኔ

የሊቨርፑሉ አሠልጣኝ ዩርገን ክሎፕ ሳድዮ ማኔ ከጄምስ ማካርተር ጋር በ16 ከ50 ውስጥ ያደረገው መነካካት ፍፁም ቅጣት ምት ያሰጣል ብሎ እንደወሰነ ግራ ያጋባል።

ቢሆንም ማኔ በጨዋታው ላይ የነበረው እንቅስቃሴ በጣም ግሩም ነበር።

ማርኮ አርኖቶቪች

ማርክ ሂዩዝ የስቶክ አሠልጣኝ በነበረበት ወቅት ማርኮ አርኖቶቪችን ሲተቸው እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ግን አጥቂዎች የሚተቿቸውን አሠልጣኞች ለመበቀል እንቅልፍ አይይዛቸውምና አርኖቶቪችም ይህንኑ ነው ያደረገው።

ኦስትሪያዊው ከሳውዝ ሃምፐተን ጋር ባደረገው ፍልሚያ ሂዩዝን የሚያሸማቅቅ ብቃት አሳይቶናል።

ሊሮይ ሳኔ

ጀርመን ከብራዚል ጋር ስትጫወት ሳኔ ከቋሚ ተሰላፊዎቹ ጋር ሆኖ ያሳየው ጨዋታ የሚገርም ነበር።

ሳኔ ጎል ለማስቆጠር አራት ደቂቃ ብቻ ነበር የፈጀበት፤ አፈፃፀሙ በጣም የሚገርም ነበር።