ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ስደተኞችን የማስጠለሉን ሃሳብ እንደተዉት አስታወቁ

እስራኤል ስደተኞችን የማስጠለሉን መርሃ ግብር አነሳች

የፎቶው ባለመብት, EPA

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በተደረገ ስምምነት መሠረት ስደተኞችን ከሃገሯ የማስወጣቱን መርሃ ግብር እንዳቋረጠች አስታውቃ የነበረችው ሃገራቸው ሃሳቧን እንደቀየረች አስታወቁ።

አብዛኛዎቹ ስደተኞች እንደሚኖሩባት የሚነግርላት የቴል-አቪቭ ከተማ ነዋሪዎችን ካናገርኩ ወዲህ ነው ሃሳቤን የቀየርኩት ሲሉ ቤኒያሚን ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ሰርጎ ገቦችን ከሃገር ለማስወጣት ሁሉንም አማራጭ እንጠቀማለን" ሲሉም ተደምጠዋል።

30 ሺህ እንደሚደርሱ ከሚገመቱት ስደተኞቹ አብዛኛዎቹ ኤርትራውያንና ሱዳናውያን እንደሆኑም ዘገባው አትቷል።

ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በተደረሰው ስምምነት መሠረት 16 ሺሕ ያህል ስደተኞች በአንዳንድ የምዕራቡ ዓለም ሃገራት እንደሚጠለሉ እንዲሁም 18 ሺህ ያህል ደግሞ በእስራኤል ቋሚ የነዋሪነት መታወቂያ እንደሚሰጣቸው ተነግሮ ነበር።

ከጥቂት ወራት በፊት ነበር የእስራኤል መንግሥት አፍሪካውያን ስደተኞች 5 ሺህ ዶላር ተሰጥቷቸው ወደ ሶስተኛ የአፍሪካ ሃገር እንዲሸጋገሩ የሚያስገድድ ህግ አውጥቶ የነበረው።

ፍቃደኛ ያልሆኑ ስደተኞች ወደ እስር ቤት እንደሚወረወሩ የሚያስገድደውን ህግ የእስራኤል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለተወሰነ ጊዜ ያህል ሥራ ላይ እንዳይውል እንዳገደው ይታወሳል።

ትላንት የተደረሰው ስምምነት ተግባራዊ ቢሆን 18 ሺሃ ያህል ስደተኞች በ5 ዓመት ጊዜ ውስጥ ወደ ጀርመን፣ ካናዳና ጣልያን ይሸጋገሩ ነበር።