አውስትራሊያ ሃሰተኛ የጋና ጋዜጠኞችን አባረረች

የጋና አትሌቶች

የፎቶው ባለመብት, Reuters

አውስትራሊያ የኮመንዌልዝ ስፖርታዊ ውድድርን ለመዘገብ ወደ አገሪቱ ያቀኑ 50 ሃሰተኛ ጋዜጠኞችን ልታባርር የቻለችው ግለሰቦቹ የቀረበላቸው ስፖርታዊ ጥያቄን መመለስ ባለመቻላቸው ነው።

እነዚህ ግለሰቦች ምንም እንኳ ሰነዶቻቸው እውነተኛ ቢሆን እንደ ስፖርት ጋዜጠኛ የቀረበላቸውንና በቀላሉ ሊመልሱት የሚገባቸውን ጥያቄ ባለመመለሳቸው ለጊዜው እንዲታሰሩ ከዚያም ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል።

የጋና ምክትል ስፖርት ሚኒስትር ፒየስ ኢናም ሃዲዲዝ ጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ ገልፀዋል።

ነገር ግን በመጀመሪያ ደረጃም እነዚህ ግለሰቦች ቪዛ እንዲያገኙ ሚኒስቴር የመስሪያቤታቸው እጅ አለበት የሚለውን ውንጀላ አስተባብለዋል።

ከተመላሾቹ መካከል ለአንድ የጋና ሬድዮ ጣቢያ ግለሰቦቹ ቪዛ እንዲያገኙ ለጋና ኦሊምፒክ ኮሚቴና ስፖርት ሚኒስቴር ከሁለት እስከ አምስት ሺህ ብር መክፈላቸውን የተናገረ ግለሰብ አለም ተብሏል።