ሲቲ ከዩናይትድ. . .የሳምንቱ ተጠባቂ ፍልሚያን ማን ይረታ ይሆን?

የላውሮ ግምቶች

ቅዳሜ

Image copyright BBC Sport

ኤቨርተን ከሊቨርፑል (08፡30 ከሰዓት)

ይህ ጨዋታ ለሊቨርፑል አሠልጣኝ ዩርገን ክሎፕ ተጫዋቾቹን የሚያውቅበት ይሆናል ይላል ላውሮ። ረቡዕ ከተጫወቱ በኋላ ድጋሚ ሲጫወቱ እንዴት እንደሚሆኑ የሚያይበት ይሆናል ይላል።

የፍልሚያዎች መደጋገም ተጫዎቾቹን ሊያደክማቸው ይችላል ሆኖም ግን ክሎፕ ሞሐመድ ሳላህን ደጋግሞ በማጫወት አደጋ ላይ ሊጥለው ይችላል፤ ከሲቲ ጋር ሲጫወቱ እንደገጠመው ጉዳት አይነት።

በሲቲ ብትንትናቸው የወጣው ኤቨርተኖች ወሳኝና መልስ የሚሰጡበት እንደሚሆን አልጠራጠርም ይላል።

የላውሮ ግምት: 1-1

Image copyright BBC Sport

በርንማውዝ ከክሪስታል ፓላስ

ባለፈው ሳምንት ጨዋታ ፓላስ በሊቨርፑል መሸነፋቸው የሚያሳዝን ነበር፤ ምክንያቱም ሳድዮ ማኔ በቀይ ሊወጣ በተገባ ነበር፤ ይህ ደግሞ ጨዋታውን በሙሉ ይቀይረው ነበር ይላል ላውሮ።

በርንማውዝ በየጊዜው እንዳዲስ ከሞት እየተነሱ ይመለሳሉ፤ በተለይ ከዋትፎርድ ጋር ያሳዩት ጨዋታ ላይ በአስራአንደኛው ሰዓት የአቻ ግብ ማስቆጠራቸው የሚገርም ነው።

የበርንማውዝ ጥሩ ጎን ሁሌም ዕድሎችን መፍጠር መቻላቸውና በግብ ማስከተላቸው ነው ይለናል ላውሮ።

የላውሮ ግምት: 2-1

Image copyright BBC Sport

ብራይተን ከሃደርስፊልድ

ብራይተን ባለፈው ከሌይስተር ጋር ባደረጉት ጨዋታ የተሰጣቸውን ፍፁም ቅጣት ምት መሳታቸውና ባዶ ለባዶ መለያየታቸው ጎድቷቸዋል።

ውጤቱ ደግሞ ከሃደርስፊለድ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ትንሽ ግፊት ሊፈጥርባቸው ይችላል የሚለው ላውሮ አክሎም ሃደርስፊልድ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ሁሉ አንድ ግብ ብቻ በማስቆጠራቸው ወደ ወራጅ ቀጣና እየተጠጉ ነው።

በዚህ ጨዋታ አቻ እንኳን ቢወጡ ሃደርሰፊልድ ትልቅ አቅም ይፈጥርላቸዋል ቢልም የሚያደርጉት ግን አይመስለኝም ይላል።

የላውሮ ግምት: 2-0

Image copyright BBC Sport

ሌይስተር ከኒውካስትል

ሰባተኘው ደረጃ ላይ ለሚገኘው ሌይስተር በርንሌይን ከኋላቸው እያሯሯጣቸው ይመስላል፣ ኒው ካስትል ደግሞ ከመጨራሻዎቹ ሶስት ቡድኖች መደብ ለመሸሽ እየታገሉ ነው ይላል ላውሮ።

ኒው ካስትል እንደሆን ከሜዳቸው ውጪ በሚጫወቱበት ጊዜ እንዳይሸነፉ ሆነው ቢቀርቡም ግን በቂ ግቦችን እያስቆጠሩ አይደለም የሚለው ላውሮ ሊዚያም ይመስለኛል ሌስተር የሚያሸንፈው ብሏል።

የላውሮ ግምት: 2-0

Image copyright BBC Sport

ስቶክ እና ቶተንሃም

ይሄ ጨዋታ ለስቶክ በጣም ወሳኝ ጨዋታ ነው። ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች አራት ግቦችን ብቻ ነው ማስቆጠር የቻሉት ያለው ላውሮ ከአጥቂዎቻቸው ተጨማሪ ግቦች ያስፈልጓቸዋል ይላል።

ሃሪ ኬን ከጉዳት ከተመለሰበት ጊዜ አንስቶ ለቶተንሃም ለ28 ዓመታት የጠበቁትን ድል መጎናጸፋቸው ትልቅ ነገር ነው ብሏል።

ከአንድ ሳምንት በኋላ ደግሞ ኬን ሙሉ ጤንኑቱን በሥልጠና ስለሚያረጋግጥ ቶተንሃም ግብ አያንሳቸውም ይለናል።

የላውሮ ግምት: 0-2

Image copyright BBC Sport

ዋትፈርድ ከበርንሌይ

ለ12 ጨዋታወች ያለ ድል የተጓዙት በርንለዮች አሁን በአንድ ጊዜ ሶስት ድሎች ተጎናጽፈዋል።

ከዌስት ብሮም ጋር ባደረጉት ጨዋታ ባርንስ በሚገርም ሁኔታ ከጭንቅላት በላይ የመታት ኳስ ግብ በመሆኗ ተፈሪነቱ እንደቀጠለ ነው።

ዋትፈርድ በሜዳቸው የሚያሳዩት ጨዋታ የሚገርም የነበረ ቢሆንም ግን በርንለይ በነፃነት እየተጫወቱ በመሆኑ የሚናቁ አይደሉም ይለናል ላውሮ።

ምንም ሆነ ምን ግን በዚህ ፕሪሚዬር ሊግ መጨረሻቸው የሚያምር ነው የሚሆነው ብሏል።

የላውሮ ግምት: 1-2

Image copyright BBC Sport

ዌስት ብሮም ከስዋንሲ

አላን ፓርዲው ሄደ ማለት ዌስት ብሮም በሁለት አሠልጣኞች ሥር አለፉ ማለት ነው። እነሱም ወደ ወራጅ ቀጣና እስኪዛውሩ ብዙ ጊዜ የሚፈጅባቸው አይመስልም ይላል ላውሮ።

ስዋንሲ በዚህ ጨዋታ ቢሸነፉ ግን ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት በካርሎስ ካርቫሃል ሥር ሆነው በመጥፎ ሁኔታ እንደሚጫወቱ አሳዩ ማለት ሲሆን ይህ ደግሞ የአሠልጣኙን ድክመት ያንጸባርቅባቸዋል።

የላውሮ ግምት: 2-1

Image copyright BBC Sport

ማንችስተር ሲቲ እና ማንችስተር ዩናይትድ

በብዙ ምክንያቶች ማንችስተር ሲቲ የሚጠበቅባቸውንና እስከዛሬ ያሳዩዋቸውን ውጤቶች ባላፈው ረቡዕ አላስመዘገቡም ነበር ይላል ላውሮ።

ፔፕ ጓርዲዮላ አንዳንድ ነገሮች ላይ ሳይሳሳት አይቀርም የሚለው ላውሮ ራሄም ስተርሊንግ ሙሉውን የፕሪምየር ሊግ ወቅት ጥሩ ሲጫወት ቆይቶ ለምን እንዳላሰለፈው ሊገባኝ አይችልም በማለት አስረድቷል።

የላውሮ ግምት: 1-1

እሁድ

Image copyright BBC Sport

አርሴናል ከውዝሃምፕተን (10፡00 ከሰዓት)

አርሴናል ሁለት ጨዋታዎችን ቢያሸንፉም አንኳን አርሴናል በመሆናቸው ብቻ ችግር ላይ ናቸው የሚለው ላውሮ አክሎ ከአሁን እሰከመጨረሻው ያሉትን ጨዋታዎች በሙሉ ቢያሸንፉም እንኳን ቀዶ ሕክምና ያስፈልጋቸዋል ይላል።

ሆኖም ግን ሳዉዝሃምፕተንን ያሸንፋሉ ይለናል።

የላውሮ ግምት: 2-0

Image copyright Getty Images

ቼልሲ ከዌስት ሃም (12፡30 ሰዓት)

የቼልሲን ጨዋታ ባየሁ ቁጥር አንቶኒዮ ኮንቴ በዚህ ፕሪምየር ሊግ መጫረሻ የሚለቅ ይመስለኛል ይላል ላውሮ።

ቼልሲ ከአሁን ወዲህ ወደ ቻምፕዮንስ ሊግ ይገባሉ ብሎ ማስብ ይብዳል ብሏል።

የላውሮ ግምት: 2-0

ተያያዥ ርዕሶች