አንድነትን የሚያወድሰው ግጥሟ ለእስር የዳረጋት ገጣሚ

የገጣሚዋ ናሲማ ኮራኒ ስራዎች የሶማሊያ ታላቅነትን እና ሶማሌላንድ ከሶማሊያ ጋር መዋሃድ ላይ የሚያተኩሩ ናቸው። Image copyright Human Rights Centre Somaliland
አጭር የምስል መግለጫ የገጣሚዋ ናሲማ ኮራኒ ስራዎች የሶማሊያ ታላቅነትን እና ሶማሌላንድ ከሶማሊያ ጋር መዋሃድ ላይ የሚያተኩሩ ናቸው።

ሶማሊላንድ የመንግሥትን ስም አጉድፋለች ያለቻት ገጣሚ ላይ የሶስት ዓመት እስር ፈረደች።

የገጣሚዋ ናሲማ ኮራኒ ስራዎች የሶማሊያ ታላቅነትን እና ሶማሌላንድ ከሶማሊያ ጋር መዋሃድ ላይ የሚያተኩሩ ናቸው።

በእነዚህ ከሶማሊያ ጋር አንድ መሆንን በሚሰብኩ ስራዎቿና ሶማሌላንደ አንድ የሶማሊያ ክልል እንደሆነች በመናገሯ ነው የተወነጀለችው።

ገጣሚዋ የታሰረቸው ከሶስት ወራት በፊት ሞቃዲሾን ጎብኝታ ስትመለስ ነው።

የሶማሌላንድ ሰብአዊ መብት ማእከል የሶማሊላንድ መንግሥት ገጣሚዋን ከእስር እንዲለቅና ሰብአዊ መብትን እንዲያከብርም ጠይቋል።

የማእከሉ ዳይሬክተር ጉሌድ አህመድ ጃማ የገጣሚዋ ክስና እስራት እጅግ አሳሳቢ መሆኑን በዚህም መጨነቃቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል።

"ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በሶማሊላንድ ህገ-መንሥስት የተጠበቀ መብት ነው። ስለዚህም መንግስትን የምንጠይቀው የአገሪቱን ህገ-መንግሥት እንዲያከብር ነው"ብለዋል።

በሶማሊላንድ በተመሳሳይ ክስ በርካታ አርቲስቶችና ጋዜጠኞች መታሰራቸው ይነገራል።

ከአስከፊ የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ ሰሜን ምእራብ ሶማሊያ ከቀሪው ሶማሊያ በመነጠል ራሷን ሶማሊላንድ ስትል ራሷን የቻለች አገር መሆኗን እንዳወጀች ይታወሳል።

ቢሆንም ግን እንደ አውሮፓውያኑ 1991 ነፃ አገር መሆኗን ያወጀችው ሶማሊያ እስከ አሁን በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና አላገኘችም።

ሶማሊላንድ 3.5 ሚሊዮን ዜጎች እንዳላት ይገለፃል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ