በሶሪያ የኬሚካል መርማሪዎች ወደ ዱማ እንዲገቡ ሊፈቀድላቸው ነው

Two man sit on the back of a horse-drawn cart moving along a street, with ruined buildings stretching behind them Image copyright Reuters

በሶሪያ የኬሚካል ጦር መሳሪያ መርማሪዎች ጥቃቱ የደረሰበትን ቦታ እሮብ እለት ለመጎብኘት ፈቃድ እንዳገኙ ሩሲያ ገለጸች።

አለማቀፉ መርማሪ ቡድን ከባለፍው ቅዳሜ ጀምሮ ወደ ሃገሪቱ ቢገባም ዱማን ለመጎብኘት ግን ፈቃድ አለገኘም ነበር።

ከ 10 ቀናት በፊት የደረሰው ጥቃት አሜሪካ፤እንግሊዝ እና ፈረንሳይን ያስቆጣ ሲሆን ከሳምንት በኋላም የሶሪያ መንግስት ላይ ወታደራዊ የአየር ጥቃት ፈጽመዋል።

በሌላ በኩል ሶሪያና አጋሯ ሩሲያ ምንም አይነት የኬሚካል ጠቃት አልተፈጸመም በማለት ይከራከራሉ።

ከአለማ አቀፉ የኬሚካል መሳሪያዎች ተቆጣጣሪ ድርጅት የመጡት መርማሪዎች ዋና ከተማዋ ዳማስከስ የሚገኙ ሲሆን እስካሁን ምርመራውን ለመጀመር ፈቃድ እየጠበቁ ነበር።

እሮብ በቦታው የሚሲደርሱት ጠቃቱ ከተፈጸመ ከ 11 ቀናተ በሁዋላ ነው። ከአካባቢውም የአፈርና ሌሎች ናሙናዎች እንደሚሰበስቡና የኬሚካል መሳሪያዎች ጥቅም ላይ መዋል አለመዋላቸውን ያጣራሉ።

በአለማቀፉ የኬሚካል መሳሪያዎች ተቆጣጣሪ ድርጅት የአሜሪካ ልኡክ ግን መርማሪው ቡድን ከመድረሱ በፊት ሩሲያ በቦታው የነበሩ ማስረጃዎችን አጥፍታ ሊሆን ይችላል ሲል ቅሬታውን አስቀምጧል።

የሩሲያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ግን ጥቃቱ በደረሰበት ቦት ሃገራቸው ምንም አይነት ነገር እንዳለደረገችና የአሜሪካ፤ እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ውንጀላ መሰረተ ቢስ ነው ይላሉ።

የአሜሪካ ምንጮች እንደሚሉት ግን ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው ግለሰቦች ላይ የተወሰደው የሽንት እና የደም ናሙና ምርመራ ውጤት እንደሚያሳያው የኬሚካል ጥቃት ስለመድረሱ የሚያረጋግጥ ነው።