ከሰሜን ኮሪያ ጋር የሚኖኝ ውይይት ፍሬ አልባ ከሆነ 'ጥዬ እወጣለሁ'-ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጋር Image copyright Joe Raedle
አጭር የምስል መግለጫ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጋር

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር የሚያደርጉት ንግግር ፍሬ አልባ ከሆነ ጥለው እንደሚወጡ ተናገሩ።

ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሰሜን ኮሪያ ከኒውክሌር እንድትርቅ ለማድረግ ከባድ ግፊት መደረግ እንዳለበት ተስማምተናል ብለዋል።

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር በፍሎሪዳ ግዛት በሚገኘው የትራምፕ ሆቴል ውስጥ ለመምከር ተገኝተዋል።

ከዚህ ቀደም የሲ አይ ኤ ዳይሬክተር ማይክ ፖምፔዎ ወደ ሰሜን ኮሪያ ከኪም ጋር በድብቅ ለመገናኘት ተጉዘው እንደነበር ትርምፕ አምነዋል።

ፖምፔዎ ከኪም ጋር የነበራቸው ቆይታ በጥሩ ሁኔታ እንደተካሄደና ጥሩ መግባባትም ላይ መድረስ እንደቻሉ አሳውቀዋል።።

በሰሜን ኮሪያ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን ጉብኝት ሲደረግ እ.አ.አ. ከ 2000 ዓ.ም ወዲህ የመጀመሪያው ነው።

ትራምፕ በቀጣይ ሁለት ወራት ውስጥ ከሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር ፊት ለፊት ተገናኘተው ይወያያሉ ተብሏል። ይሁን እንጂ የስበሰባው ቦታ የት ሊሆን እንደሚችል የተገለጸ ነገር የለም።

ከአቤ ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ትራምፕ ከኪም ጋር የሚያደርጉት ንግግር ፍሬ አልባ ከሆነ ስብሰባውን ጥለው እንደሚወጡ አሳውቀዋል።

''ሰሜን ኮሪያ ኒዩክሊዬር መጠቀሟን እንድታቆም ለማድረግ የምናካሄደው ከፍተኛ ግፊት ይቀጥላል'' በማለትም ትራምፕ ተናግረዋል።

አክለውም ''ከዚህ በፊት እንደተናገርኩት ሰሜን ኮሪያ የኒውክሊዬር ማበልጸግ ስራዋም ብታቆም ለሰሜን ኮሪያ ብሩህም ሆነ ለመላው ዓለም መልካም ይሆናል'' ብለዋል።

አሜሪካ እና ጃፓን ''ነፃ፣ ፍትሃዊና ለሁለቱም የሚያገልግል የንግድ ስምምነት'' ላይ ለመድረስ ንግግር ስለመጀመራቸው ትራምፕ ተናግረዋል።

ትራምፕ ጃፓን እና ሌሎች የትራንስ ፓሲፊክ አባል አገራት አሜሪካ አልቀበልም ማለት የማያስችላትን የንግድ ስምምነት እስካላቀረቡላት ድረስ አገራቸው ትራንስ ፓስፊክን እንደማትቀላቀል ተናግረዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ